በሽምግልና የሚደራጅ ክልል የዎላይታን ጥያቄ አይቀለብሰውም!!!

Wolaita Today

በዶ/ር ብስራት ኤልያስ

በህገ መንግስት የተደነገገውን በክልል የመደራጀት መብት ለጠየቀው ዎላይታ ለማሸማቀቅ ሆን ተብሎ በአሃዳዊያን ጠንሳሽነት በየሚድያና በተለያዩ ዜዴዎች የተደረገው የማሸማቀቅና የማዳፈን ድራማ ይብቃ።

የደኢህዴን ጥናት፣ የ80 ሰላም አምባሳደር፣ በግለሰቦች ቡድን፣ የፌዴረሽን ጥናት ኮሚቴ፣ የሽማግሌ ስምምነት ወዘተ…በተለየ ሁኔታ ዎላይታን ነጥለው አንዳንድ የደቡብ ብሔሮች ሆድ አደር ካድሬና አሃዳዊያን ሚድያ ዘመቻ፣ ተመሳሳይ ቋንቋ ተናጋርዎችን በማደራጀት በመድረክና በየሚድያዎቻቸው ዘመቻ፣ አግላይነት ዘመቻ፣ የጥላቻ ዘመቻና አብረን አንሆንም በሉ ድራማ ወዘተ የተፈበረከ በደቡብ አሮጌ ካድሬና ራሳቸውን የለውጥ ቡድን ብለው የሰየሙ ለውጥ የማይፈልጉ የማዕከላዊ መንግስት ድራማ ጊዜ ከመግዛት ውጪ የህዝብን አጀንዳ አልቀየረውም።

ዎላይታን ከየትኛውም ክልላዊና አገራዊ ጉዳዮች ከውሳኔ ሰጭነት ያገለለ መንግስታዊና ድርጅታዊ አሠራር እየተጠናከረ ተዘርግቷል። አሁን ደግሞ ህዝብ ለህዝብ የተጣላ በማስመሰል ለእርቅ የሚባል ሌላ ድራማ እየተደገሰ እንደሆነ ይሰማል። ዎላይታ ከማንም ጋር ለእርቅ የሚያካህድ ጥልም የጋራ አደረጃጀት የሚወስን ፍላጎትም የለም።

የአጎራባች ዞኖች አንድያውቁ የሚንፈልገው ነገር ብኖር ዎላይታ ትላንት፣ ዛሬም ነገም የሚጠይቀው ጥያቄ የምድር መዋቅር ወብክመ  ነው። የሰማይን የጠየቁ ስላሉ የሰማይን አደረጃጀት ላይ ጥያቄ የለንም። እሱን ለጠየቁት እንተወውና ከዛ ውጭ ኦሞትክ ቅርጫት፣ መቀመጫ ምናምን አልጠየቅንም፤ አንፈልገውም። የወንድማማችነትና የማህበራዊ ትስስር ጉዳይ መቼም ብሆን መዋቅር የፈጠረው ጉዳይ ስላልሆነ በምንም የሚፋታ ልሆን አይችልም። እሱስ ስለፈለግነው፣ ስለወደድነው፣ ስለተመቸን የሚሆን የሚመስለውም አለ።

ጥያቄያችን ወብክመ በህገ መንግስት መርህ ለብቻ ይሰጠን። ይህንን አታሟሉም የሚል መከራከሪያ ሃሳብ ማንም ጋር የለም፤ ካለ ህገ መንግስት ይነበብ። ሽማግሌዎችን እጅ ለእጅ በማያያዝ የሚሠራ የፎቶ ፖለቲካ ውስጥ የሚያስገባ እርቅም ስምምነትም የለም። ይህ ዳግሞ ሌላ የፎቶ ፖለቲካ ሽወዳ ድራማ ይኖራል ብለን አናስብም።

የህዝቡን ፍላጎት ወደ ጎን በማድረግ ካድሬዎችን እና ምናልባትም የተለየ እይታ ያላቸውን ሽማግሌዎችን በመሰብሰብ ለጥያቄዎቹ መልስ ለመስጠት የሚደረገው ጥረት እንደዎላይታ ምንም መፍትሄ አይሰጥም፡፡

መልስ ያለው 15 ሚሊዮን ህዝቡ ጋር ነው በአደባባይ በሰላማዊ ሰልፍ የገለፀውና በምክር ቤት አጽድቆ የላከው የህዝቡ ድምጽ ሊደመጥ ይገባል። ያለ ህዝብ ፈቃደኝነት ማንም ተነስቶ ጥናት አካሄድኩ ስላለ፣ የተጣሉ በማስመሰል እርቅ ሽማግሌ እጅ ለእጅ ተጨባበጡና እጅ አነሱ ማታለያ የዎላይታ ህዝብ ጥያቄ ሊዳፈን አይችልም።

አሁን የዎላይታ ባንድራዎች በብዛት በየአከባቢው ልውለበለብ ይገባል። ደቡብ ክልል አካላዊ አስተዳደር የለምና በኢትዮጵያ ባንድራ ጎን የዎላይታ ባንድራ ልሰቀል አለበት። የደቡብ ጎጆው ስለፈረሰ ባንድራው መውረድ አለበት።

ወላይታ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት!!!