በወላይታ የተከሰተውን ሁኔታ ለማርገብ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን አስመልክቶ ዎብን ያወጣው አስቸኳይ መግለጫ

Wolaita Today

August 11, 2020

  1. በሠላም ቀጠና በተሳሳተ መረጃ ላይ ተመስርቶ ሠራዊት በመላክ ሕዝቡን የሚያሸብረው፣ ንፁሐንን የሚያስገድለውና የሀገር ሽማግሌዎችንና ሌሎች የክልል ምሥረታ ሴክሬታሪያት አባላትንና የዞኑ አመራሮችን ክብር በሚነፍግ መልኩ ከበባ በማድረግ እንዲታሠሩ ያዘዘው ደቡብ ክልል መንግሥት በሕግ ይጠየቅ፣
  2. አስለቃሽ ጋዝ እንኳን ሊተኮስባቸው በማይገባ ሁኔታ ተመጣጣኝ ያልሆነ እርምጃ በመውሰድ ንፁሐንን ተኩሰው የገደሉና ያቆሰሉ ወታደሮች በሕግ ይጠየቁ፣
  3. የሟቾችና የተጎጂ ቤተሰቦች በሕግ ተወስኖ ካሣ ይከፈላቸው፤ መንግሥት ለጥፋቱ በይፋ ኦፊሴላዊ ይቅርታ ይጠይቅ፣
  4. የሞቱት ሰማዕታት የመታሰቢያ ሐውልት መሠረተ ድንጋይ ይቀመጥ፣
  5. የክልሉ መንግሥት ክብራቸውንና አጠቃላይ ስብዕናቸውን በማይመጥን ሁኔታ ከበባ አድርጎ ያሠራቸው ሁሉ በአስቸኳይ ይፈቱ ፤ መንግሥትም ይፋዊ ይቅርታ ይጠይቅ፣
  6. ከተለያዩ አካላት ጋር በማነካካት የወላይታ ሕዝብ ሠላማዊ ጥያቄ የሽብር እንቅስቃሴ ለማስመሰል ተቀናብሮ እየተሠራ ያለው በተለይ የደቡብ ክልል ቴሌቪዥንና በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን እንዲሁም በሌሎች ሀገራዊ ሚዲያዎች ኃላፊነት በጎደለው መልክ እየቀረበ ያለው የሐሰት ትርክት በሕግ ይታገድ፣
  7. የወላይታ ሕዝብ የክልል ጥያቄ አስመልክቶ መንግሥት ውሣኔውን ለሕዝብ ይፋ ያድርግ።
  8. መላው የዎላይታ ነዋሪ እንደ በፊቱ ሁሉ አከባቢውን በንቃት በመጠበቅ በዎላይታ ለሚኖሩ ለሁሉም ብሔረሰቦችና ብሔሮች የተለመደውን ጥበቃ በማድረግ የተወጠነውን ሴራ በአንድነት እንዲያከሽፍና በየትኛውም ሁኔታ ሠላማዊ አማራጮችን አሟጦ በመጠቀም እውነተኛ የሠላም አምባሳደሪነቱን ዳግም እንዲያረጋግጥ ከአደራ ጭምር እናሳስባለን፡፡

እነዚህ ሁኔታዎች ባልሟሉበት ሁኔታ እሥረኞችን ብቻ መፍታት በወላይታ ሠላምና ፀጥታ እንዲረጋገጥ ዋስትና የማይሰጥ መሆኑን መንግሥት ተገንዝቦ አስፈላጊውን እንዲያደርግ አበክረን አንጠይቃለን።

የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ

ነሐሴ 5 ቀን 2012

Wolaita Today
Wolaita Today
Wolaita Today