በጋሞ ዞን ሻራ ብሄረሰብ አባላት የሟቾች ቁጥር ከ25 በላይ ደረሰ
ነሐሴ 20 2015ዓም
“በጋሞ ዞን አስተዳደር አቶ ብርሀኑ ዘዉዴ እና በአዲሱ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ትዕዛዝ ትናንትና ማምሻዉን ጀምሮ በጭቁኑ የሻራ ህዝብ ላይ ጅምላ ጭፍጨፋ እየተካሄደ ይገኛል” ስሉ በጋሞ ዞን የሻራ ብሄረሰብ አባላት አስረድተዋል።
በጅምላ ግድያም ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስ ከሃያ አምስ (25) ንፁሃን ሰዎች በላይ በግፍ ተገድለዋል፤ የሟቾችም ቁጥ ሊያሻቅብ ይችላል። በሺዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን የሻራ ቀበሌ ዜጎችም ለከፍተኛ አካል ጉዳት መዳረጋቸዉም ተረጋግጧል።
በጋሞ ዞን አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ የሻራ ቀበሌ ነዋሪዎች ለዘመናት ከቅድመ አያቶቻቸዉ ጀምሮ ከሚኖሩበት የገዛ ቀዬያቸዉ በሀይል ለማፈናቀል የቀረበላቸዉን በከተማ መዋቅር የመካለል ጥያቄ ሲቃወሙ መቆየታቸዉ ይታወሳል።
ሆኖም ግን የተፈራዉ እልቂት አልቀረም የንፁሃን ሻራ ህዝብ ግፈኛ አመራሮች ባወጁት የእልቂት ነጋሪት ንፁሃኑ ሠላማዊ የሻራ ህዝብ እየተጨፈጨፈ ይገኛል። ትናትና ዕለተ ሐሙስ በነሃሴ 18/2015ዓ.ም ህዝቡ በተኛበት ከምሽቱ አራት (4:00)ሰዓት በታጠቁ ሀይሎች በተከፈተዉ የጅምላ ጭፍጨፋ ከሃያ አምስት(25) በላይ ንፁሃን ዜጎች በሻራ ቀበሌ ተገድለዋል።
የሟቾችም ቁጥር ከዚህ በላይ ሊያሻቅብ ይችላል። በሺዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ዜጎችም በከፍቸኛ ጉዳት በጣር ላይገኛሉ።
በሠላማዊ ህዝብ በቀላሉ በድርድር ሊፈታ በሚችል ችግር ባለጊዜ ነን በሚሉ ነፍጠኛ ተሿሚዎች በዞኑ አስተዳዳሪ ብርሃኑ ዘዉዴ እና የአዲሱ ክልል ተሿሚ በጥላሁን ከበደ ቀጥታ ትዕዛዝ በሠላማዊዉ የሻራ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ የሚገኘዉ እጅግ አስከፊ እና አሰቃቂ ጭፍጨፋ እየተካሄደ ይገኛል ስሉ ነዋሪዎች ይናገራሉ።
ከሰሞኑ አዲሱ የክልል መዋቅር ጥያቄ ተከትሎ አከባቢዉን ለማረጋጋት በአርባምንጭ የሚገኘዉ የታጠቀ ልዩ ሀይል፣ የጋሞ ዞን እና የከተማዉን የታጠቀ የፖሊስ ሀይል ሠላማዊን የሻራን ህዝብ በገፍ በማስጨፍጨፍ ላይ ይገኛሉ፨
በቀበሌዉ አሁንም እየተባባሰ በቀጠለዉ የዘር ማጥፋት በጭካኔ የተሞላ ጅምላ ግድያ በርካቶች ተገድለዋል ገሚሱ የህክምና እርዳታ ተከልክሎ በከፍተኛ ጉዳት ላይ ይገኛሉ። በርካቶች ቀበሌዉን ለቀዉ ተሰደዋል። በማሣቸዉ ላይ የሚገኘዉ ሙዝ እና ሌሎችም ሰብሎች በዚሁ ሀይል እየወደመ ይገኛል።
እንደ ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በጋሞ ዞን ወኪል በሥፈራዉ ተገኝቶ አረጋግጦ ባደረሰው ዘገባ ቀደም ሲል የሻራ ብሄረሰብ አገር ሽማግሌዎች መሰል የግፍ ጭፍጨፋ ከመድረሱ አሰቀድመዉ ለማዕከላዊ መንግስት ለጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት በተደጋጋሚ አቤት ሲሉ መቆየታቸዉን ተናግረዋል። ሆኖም በገዛ ወገናቸዉ ላይ ስልጣንን መከታ በማድረግ ከፍተኛ ኢሠብዓዊ ፤ እብሪት በተሞላ ጭካኔ የዘር ማጥፋት ዘመቻ የተገደሉ ወጣቶች፣ አባቶችን እና እናቶችንና ህፃናትን አስከሬን በመከልከል ይባስ ብለዉ የጅምላ መቃብር በማዘጋጀት ላይ መሆናቸዉ የመንግስት ባለስላጣናት የጭካኔ ጥጋቸዉ ወሰን ማጣቱን ያሳያል ሲል ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ዘግቦታል፨