የአይዳሚያ ሴቶች አስተባባሪዎች በወላይታ ታሰሩ፡፡
ጥቅምት 10 2013ዓ.ም
የወላይታን ህዝብ የክልል ጥያቄ ተከትሎ የመንግስት አስተዳደር የኮንትራት ዉሉ ያበቃው የኢህአደግ/ብልፅጋና መንግስት በወላይታ ህዘቡን በማሸበር ወጣቶችን በማሳደድ እንዲሁም የአይዳሚያ ሴቶች አስተባባሪዎች በመንግስት ወታደሮች ታፍነው መወሳዳቸው ቤተሰቦቻቸው አስታወቁ፡፡
ወጣት ትዝታና ኪያ በወላይታ የክልል ጥያቄ ላይ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ የሚገኙ ሲሆን የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ አባላት መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡
የወላይታ ህዝብ ላይ አገር አስተዳደርራለሁ የሚል የብልፅግና ፓርቲ እየፈፀመ ያለው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ህዝቡን የበለጠ ለቁጣ እያነሳሳ መሆኑን የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች አስታውቀዋል፡፡
የዛሬው የፍርድ ቤት ሂደት ውዝግብ ያስነሳ ሲሆን የክልል አቃቤ ህግ ከፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር የዞኑ ፍርድ ቤት እና አቃቤ ህግ ጋር በመተባበር የብልፅጋና ስልጠና እየተካሄደ መሆኑ የወላይታ ብልፅጋና ፓርቲ አመራርና አባለት ለአከባቢው አለመረጋጋት ትልቁን ድርሻ እንደሚወስዱ አስተያየት ሰጪዎች አስታውቀዋል።