ከክቡር ዶ/ር ዘብዲዎስ ጫማ ጋር አቶ ጳዉሎስ ባልቻ ሰኔ 6 2007 ዓ.ም የተደረገ ቃለመጠይቅ

Wolaita Today

በዎላይታ ሶዶ ሰኔ 6 2007 ዓ.ም በክቡር ዶ/ር ዘብዲዎስ ጫማ በግል ጥረታቸዉ በተቋቋመዉ የቅርስ ጥበቃና ቱሪስት ማዕከል ዉስጥ ከአቶ ጳዉሎስ ባልቻ የተደረገ ቃለመጠይቅ፡፡ (መልካም ንባብ)

ጳዉሎስ ባልቻ፡- በሥራ ተወጥረዉ እያሉ ነዉ ያገኘሁት፤ይህንን ዉድ ጊዜዎን ሰዉተዉ ለቃለ መጠይቁ ከፍጹም ልብ ፈቃደኛ በመሆንዎ ላመሰግኖት እወዳለሁ፡፡

ዶ/ር ዘብዲዎስ ጫማ፡- እኔም አመሰግናለሁ (ትህትና በሞላበት ሁኔታ)

ጳዉሎስ ባልቻ፡- ተዝቀዉ ከማያልቀዉ ከእርስዎ የታሪክ ዉቅያኖስ ከመቅዳታችን በፊት የዚህ ታላቁ የዎላይታ የሕዝብ የታሪክ ቤተ-መጽሃፍት የሆኑትን እርስዎን ማን ልበል?

ዶ/ር ዘብዲዎስ ጫማ ፡- እኔ ዛባ ጫማ ገራሞ በሁዋላ ዘብዲዎስ የሚል ስያሜ ነበር የተሰጠኝ፡፤ ዕድሜዬ 76 ሲሆን በዳሞታ ጋሌ ወረዳ በዋሪተ-ኦሎንቾ ቀበሌ በ 1931 ዓ.ም ተወለድከኝ፡፡ ዕድሜዬ ለትምህርት እንደደረሰ ኦቶና ላይ Sudan Interior Mission(SIM) በከፈቱት Christian Academy ተብለዉ በሚታወቀዉ ትምህርት ቤት እስከ ስድስተኛ ክፍል ድረስ ተማርኩት፡፡ እስከ ስምንተኛ ክፍል ድረስ ያለዉን ደግሞ በአቶ ቦጋሌ ዋላሉ ታላቅ ጥረት በተከፈተዉ ሊጋባ በየነ አባሰብስብ ትምህርት ቤት እዚሁ ሶዶ ነበር የተማርኩት፡፡ ቀጥሎ ያሉ የክፍል ደረጃዎችን በይርጋለም ካጠናቀኩኝ በኋላ ወደ ዩኒቨረሲቲ ደረጃ የደረስኩት ሰዉ ነኝ፡፡

ጳዉሎስ ባልቻ፡- በብዙ ቦታ እርስዎ በኃላፊነት እንደሰሩ የእርስዎን ስም በእርስዎ የተገለገሉ በርካታ ሰዎች በመልካም ገጽታ ያነሳሉና በትንሹ በምን ዘርፍ ሰረተዋሉ?

ዶ/ር ዘብዲዎስ ጫማ ፡- እኔ መምህርነት፡በር/መምህርነት፤ በትምህርት ባለሙያነትነና በአዉራጃ አስተዳዳሪነት በተለያዩ ቦታዎች አገልግያለሁ፡፡

ጳዉሎስ ባልቻ፡- የት የት እንደሰሩ ብያብራሩልኝ ?

ዶ/ር ዘብዲዎስ ጫማ ፡- በመምህርነትና በር/መምህርነት ሶዶ Christian Academy ዉስጥ እንዲሁም በሲዳማ ውስጥ አላታ ወንዶ ላይ የጁኒዬር ትምህርት ቤት ለአንድ ዓመት በር/መምህርነት ከ1971-1979 ዓ.ም ሶዶ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምክትል ር/መምህር በመሆን ፤ከ1979 ዓ.ም ጀምሮ የኮንታ (ኤላ አዉራጃ) አስተዳዳሪ ሆኜ አገልግያለሁ፡፡ ቀጥሎም በትምህርት ሚ/ር ሥር ዎላይታ ሶዶ የፈተና ክፍል ሆኜ በመቀጠል ወደ ባህል ሚንስተር መምሪያ ተዛዉሬ የቅርስና የታሪክ ክፍል ኤክስፔርት በመሆን በ Ethnography ሙያ ሰርቺያለሁ፡፡በመጨረሻም ጡረታ ወጥቺያለሁ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ኑሮዬን USA አገር ከቤተሰቦቼ ጋር በማድረግ ወደ ዎላይታ ሶዶ እየተመላለስኩ የቅርስ ጥበቃና ቱሪስት መስህብ ቋሚ ኤግዝብሽን ማዕከል እየገነባሁ እገኛለሁ፡፡

ጳዉሎስ ባልቻ፡- ይህ ብዙ ጉልበትና ወይም አቅም የሚጠይቅ ፕሮጀክት ለእርስዎና ለቤተሰብዎ ገቢ ከማስገኘት ይልቅ ጠቀሜታዉ ለዎላይታ ሕዝብ እንደምጎላ ይሰማኛል፤እና ለዚህ ፕሮጀክት ስኬት ከእርስዎ በስተጀርባ ማን አለ?

ዶ/ር ዘብዲዎስ ጫማ ፡- በመጀመሪያ ደረጃ ከሁሉም በላይ የሆነዉ የእግዝአብሔር እርዳታ ሲሆን ቀጥሎ የቤተሰቦቼ ድጋፍና ክትትል ነዉ፤የበርካታ ሰዎች የሞራል ድጋፍ እንዳልተለየኝ ልዘነጋ አይገባም፡፡

ጳዉሎስ ባልቻ፡-ይህንን የዎላይታ ቅርስ ጥበቃ ማዕከል እንድገነቡና እንድያደራጁ ምንድነዉ ያነሳሳዎት?

ዶ/ር ዘብዲዎስ ጫማ ፡- አንተ የታሪክ ቤተሰብ ከሆንክ ታሪክ ይጥማል እና እኔ የታሪክ ቤተሰብ ነኝ፡፡ አያቴ ገራሞ ለዚህ ለዎላይታ ሕዝብ ሉኣላዊነት ከአጼ ምኒልክ ጋር ሲዋጋ 1887 ዓ.ም ተሰዉተዋል፡፡ ይህንን ገድል ሲሰማ ነዉ ያደኩት፤የጎረበቶቼ ሚና እንዲሁም በዎላይታ አከባቢ የሚኖሩ የታሪክ አዋቂዎችን ጠይቄ በመረዳት(inquiry learning) ነዉ፡፡

ጳዉሎስ ባልቻ፡- እርስዎ ካነጋገሩአቸዉ ከዎላይታ ታሪክ አዋቂ አባቶች መካከል ትልቅ አርአያና ግብኣት የሆኑት ማን ነበሩ ?

ዶ/ር ዘብዲዎስ ጫማ ፡- በወቅቱ ማለትም 1971 ዓ.ም ዕድሜያቸዉ 110 የሞላቸዉ አቶ ጋጃቦ ጋጋ (ያረፉት 1980ዎቹ ዉስጥ) በዳሞታ ጋሌ ወረዳ ሐርቶ ቆንጦላ ቀበሌ ዉስጥ በማነጋገር በተለይ ከአጼ ምንልክ ጋር ዎላይታ ሕዝብ ስላደረጉት ጦርነትና ከጦርነቱ በፊት ስለነበሩ ሁኔታዎችን የሚዳስስ ቀዳማይ የታሪክ ምንጭ (primary source) ማግኘት ችያለሁ፤ በተጨማሪ በተለያዩ ዎላይታ አከባቢ የሚገኙ በቁጥር ወደ 70                           የሚደርሱ   የዐይን እማኞችን አነጋግርያቸዋለሁ፡፡

ጳዉሎስ ባልቻ፡- እርስዎን ከቅርስ ጋር በተያያዘ ከሰሙት ቀዳማይ ታሪክ መካከል ምንድነዉ ማራኪ ወይም ልብ የነካ ታሪክ ብለዉ ያገኙት?

ዶ/ር ዘብዲዎስ ጫማ ፡- እጅግ በርካታ ከሆኑት መካከል ጥቅቶችን ለመግለጽ እሞክራለሁ፤በጣም ልብ የሚነካ ድርጊት በዎላይታ ሕዝብ ስብእና፤ንብረትና ቅርስ ላይ [ግዛት በምያስፋፉ ኃይሎች] አማካይነት በ1887 (1894) ጦርነት ተፈጽሟል፡፡ ከነዚህ መካከል ዳልቦ ላይ በካዎ ጦና ቤተመንግሰት ግቢ ዉስጥ የነበረዉ ታላቁ የዎላይታ ሕዝብ ሙስዬም ተቃጥሏል፤ለሦስት ቀን ያህል ነበር ቃጠሎ የዘለቀዉ፡፡መሰል ጥቃቶች በዚያዉ አላበቁም፡፡

የተገኘዉን ሥልጣንና አጋጣሚዎችንም በመጠቀም የዎላይታ ሕዝብ ታሪክ ተዳፍነዉ እንድቀር አድርገዋሉ፡፤ይህ ታሪክ ተዳፍነዉ እንዳይቀር የተገኙ አጋሚዎችን ሁሉ በመጠቀም በተለይ የዉጪ አገር የታሪክ ጸሀፊዎች የጻፉትን መጽሓፍትን ወደ እንግልዝኛ የማስተርጎም ሥራና የመሰብሰብ ተግባራት ትልቁን ጊዜ ይዘዉብኛል፤ለምሳሌ በG. Vadnreim [he was an eye-witness about the war between Wolaytta and Menelik in 1894 and wrote unbiased diary concerning socio-economic and political situation of the people in Little) አማካይነት በፈረንሰኛ ቋንቋ ስለተጻፉ በዎላይታና በዐጼ ምንሊክ መካከል ስለተደረገዉ tragedy ጦርነት በብዙ ወጪ ማስተርጎም ችያለሁ፡፡ ለወደፊቱም አንድ ትልቅና ሙሉ የሆነ የዎላይታ ሕዝብ ታሪክ ይዤ እመለሳለሁ እግዝአብሔር ከፈቀደ፡፡

ጳዉሎስ ባልቻ፡- ዛሬም ነገም ለወደፊቱም የሚመጡ የዎላይታ ትዉልድ እንዲሁም ምሁራንና የመንግስት ባለሥልጣናት ባህል፣ወግና አጠቃላይ የሚጨበጡም(material cultures) ሆኔ የማይጨበጡ (spiritual cultures) የባህል ዐይነቶች እንዳይጠፉ እርስዎ ምን ይመክራሉ?

ዶ/ር ዘብዲዎስ ጫማ ፡- ጎጂ ያልሆኑ ባህሎች ላይ ሕዝቡ ነቅቶ መሳተፍ አለባቸዉ። አባቶች ልጆቻቸዉን ስለታሪክ በተለያዩ ማስተማሪያ ዘዴዎች አማካይነት ዕውቀት ልያስጨብጧቸዉ ይገባል። ምሁራን መረጃ በመሰብሰብ አቅም በፈቀደዉ መልክ በማሳተም ለንባብ ማብቃት አለበት።

መንግስታዊ ተቋማት ገንዘብም ሆነ ሥልጣን በአንጻሩ ያላቸዉ ከመሆኑ አንጻር የታሪክ ባለሙያዎችን ያለጠልቃ ገብነት ማስጠናት አለባቸዉ። በተለያዩ መንግስት ተቋማት ዉስጥ የሚገኙ መዛገብት ነጌ የታሪክ ምንጮች             ናቸዉ። በመሆኑም ከማስወድ ይልቅ Archaival center በልዩነት ተሠርተዉ እንድቀመጡ ማድረግ ተገቢ ነዉ። Scanning technology በመጠቀም በsoftcopy መልክ መረጃዉን ማስቀመጥ ሌላኛዉ አማራጭ ነዉ። በአጠቃላይ ሁሉም የበኩሉን ብወጣ በራሱ ባህል እንድሸማቀቅ የተደረገዉን ትዉልድ በባህሉ እንድኮራ ማድረግ ይቻላል።

ጳዉሎስ ባልቻ፡- ዎላይታ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች የተክል ድንጋዮችን እናገኛለን፣ አንዳንድ ሰዎች ጦረኛዉ አህመድ ግራኝ ጉልበተኛ የሆነዉን ፈረሱን ለማሰር የተከለዉ ድንጋይ ይሉታል። እርስዎስ ምን ይላሉ?

ዶ/ር ዘብዲዎስ ጫማ ፡- ፣በፍጹም አይደሉም። አህመድ ግራኝ ከምስራቁ አገራችን ክፍል በመነሳት በወቅቱ ከዎላይታ መንግስት በስተሰሜን የሚገኙ ሕዝቦችን ከተቆጣጠረ በጏላ የዎላይታ መንግስትን ለመዉረር በአጎራባች ከንባታ በኩል ነበር የመጡት።የዎላይታ ጦር ኤጌዶ ጫሪያ ተብለዉ በሚጠራዉ ጨፈያማ ሥፍራ የዋዚር ሙጃህድ cavalary የጥቃት ሙከራ ተስፋ ቢስ በማድረግ መልሶአቿል። የተለያዩ archaelogists እነ Francis Hunfre, Francis Jhonson, Xavier እና Champolion ባደረጉት ጥናት መሠረት ይህ ጥንታዊ አፍርካዉያን ሟች ዘመዶቻቸዉ ዝነኛ፣ጦረኛ፣ባለጸጋና ታዋቂ አደንተኞችን ለመዘከርና ለማስታወስ መቃብሮቻቸዉ ላይ የሚያስቀምጡት ዘላቂ የድንጋይ ምልክት ነዉ። እንዲህ አይነት የተክል ድንጋዮች ከምዕራብ አፍሪካ ናይጀሪያ አከባቢ ተነስተዉ ከምድረ ወገብ በቅርብ ድግሪ ሰሜንና ደቡብን አካልለዉ ወደምስራቅ እስከ Cambodiaና Laos ድረስ ይዘልቃል።

ጳዉሎስ ባልቻ፡- እርስዎ በከፍተኛ ሁኔታ ስለእግዝአብሔር ወንጌል ይተጋሉ። በደርግ ጊዜ የProtestant Church በዎላይታና በተወሰኑ ደቡባዊ አገርቱ ክፍሎች ተዘግተዉ ነበር። ይህ በምን አይነት ሁኔታ በአጠቃላይ ተጀምሮ እንደተጠናቀቀ ብገልጹልኝ?

ዶ/ር ዘብዲዎስ ጫማ ፡- መስከረም 2 1967 ዓ.ም በይፋ የቀዳማዊ ጏይሌ ሥላሴን መንግስትን ጁንታዉ ከገረሰሰ በኋላ ቀስ-በቀስ ወደ Communist ideology ነበር ያዘነበለዉ። ቀደም ብሎ በ1967 ላይ መሬት ለአራሹ ሲያዉጅ ነበር። በተመሳሳይ ማንም ሰዉ የሚፈልገዉን ሀይማኖት የመከተልና የማምለክ መብት እንዳለዉ ታወጀ። አዋጁን ተከትሎ አንዳንድ የነቁ ኦቶና ከሚሲዮናዉያን ጋር የነበሩ ሰዎች በወቅቱ በዎላይታ ሥልጣን ላይ ለነበሩ አመራሮች ማመልከቻ አቅርበዉ ቤተክርስቲያን ለመክፈት ፈቃድ አገኙ። ሶዶ ከተማ ዉስጥ በቅደም ተከተል የStadium ቃለሕይወት፣Swidish Lutheran ቤተክርስቲያንና ሙሉ ወንገል ቤተክርስቲያናት ተከፈቱ። ብዙም ሳይቆይ ጥር 1976 ዓ.ም ጀምሮ የቤተክርስቲያናት መዘጋት ሆነ። ንብረታቸዉ ተወረሰ ስዴትና እስራት አየለ ለክርስቲያኑም የጨለማ ጊዜ ሆነ።

ጳዉሎስ ባልቻ፡-  ኢሕዴሪ እስከምታወጅ ዎላይታ በሲዳሞ ክፍለሀገር ሥር ነበረች። መዋቅራዉ የአስተዳደር

ለዉጥ መጣና ዎላይታ ከሲዳሞ ሰሜን ኦሞ ተፈናጠረች። በወቅቱ እነ አሊ ሙሳ ዋነኛ አሳዳጆች ነበሩ። ነገር ግን የዎላይታ ሕዝብ ልጆች የነበሩ እነ ስሞኦን ጋሎሬ (የፖለቲካ ርዮተ-ዐለም ክፍል ሀላፊ)ና የሰሜን ኦሞ አስተዳዳሪ    የሆኑት አቶ ጴጥሮስ ገበቶ ምን ዐይነት አመለካከት ነበራቸዉ?

አቶ ዘብዱዎሰ ጫማ፡- የሚገርመዉ በወቅቱ በሁለቱ መካከል የሀሳብ አለመግባባቶች ብዙዉን ጊዜ ይስተዋሉ ነበር።ነገር ግን የቤተክርስቲያን መዘጋቱን ሁለቱም በአንድ ሐሳብ ይቃወሙ ነበር፤ ምክንያቱም የመጡባቸዉ ቤተሰቦች ስለወንጌል ብዙ የታገሉና የለፉ ነበር።እነሱም ምንም እንኳን Religious is an opium of people ብለዉ የሚያምነዉን የኮሚዩኒስት ፖለቲካ አቀንቃኞች ቢሆኑም ልቦናቸዉ ስለክርስቶስ ያዉቅ ነበር። ለሕዝብ የአምልኮ ነጻነት ብኖራቸዉ ምኞታቸዉ ነበር። አንዳንድ ምክረ-ሐሳቦችንም የወቅቱ ጠቅላይ ሚንስተር ከነበሩ ፍቅሬ ሥላሴ ወግደረስ ጋር ይወያዩ ነበር። የቤተክርስቲያን መዘጋት ለደርግ በኋላ ትልቅ ፈተናና ተቃዉሞ እንደሚያመጣ ይናገሩ ነበር።

ጳዉሎስ ባልቻ፡- ፡- እርስዎ በዚያን ጊዜ ምን ዘርፍ ላይና የት ነበሩ?

አቶ ዘብዱዎሰ ጫማ፡- የደርግ መንግስት እንደተመሠረተ እኔ የIllitracy Campaign /የማይምህነት ዘመቻ የተባለዉ ሲጀመር የዎላይታ መሠረተ ትምህርት አዝማች ነበርኩ። ከ1979ዓ.ም ጀምሮ ወረዳ የሚባል መዋቅር ወደአዉራጃ እንደተቀየረ ኮንታ ዉስጥ ኤላ አዉራጃ አስተዳዳሪ በመሆን ተመድቤ እስከ ደርግ መንኮታኮት እዛዉ ነበርኩኝ።

ጳዉሎስ ባልቻ፡- ኮንታ ላይ ወይም እርስዎ ባስተዳደሩት አዉራጃ የሀይማኖት ስዴት ነበር? ምን ይመስል ነበር?

ዶ/ር ዘብዲዎስ ጫማ ፡- አዎን ነበር፡፡ ከመድረሴ በፊት ወደ 12 በተክርስቲያናት ተዘግተዉ እያሉ ነበር የደረስኩት፡፡ ብዙም ሳልቆይ አንድ ቀን የተወሰኑ ምዕመናኖች ተሰባስበዉ እየፈሩ “እኛጋ ቤተክርስቲያናት ተዘግተዋሉ፤ርዮተ-ዐለም የሆነዉ ሰዉ ከወደ—–የመጣ ሰዉ ሲሆን ከልክሎናል፤ድሮም ቢሆን እግዝአብሔር ከወደ ዎላይታ ነበር የመጣዉ በማለት አቶ አድኖ ደቤና የተባሉ ሰዉ በእጃቸዉ መጽሓፍ ቅዱስ ይዘዉ እርስዎ ምን ይላሉ ሲሉ ጠየቁኝ”፡፡ እኔም ማንኛዉም ትዕዛዝ የሚመጣ በኔ በከኩል ስለሆነ አምልኮአችሁን ቀጥሉ ብዬ ሸኘሁኣቸዉ፡፡ ልያምኑኝ ካለመቻላቸዉ የተነሳ በፍርሃት ቆይተዉ ሌላ ጊዜ በድጋሚ አምስት የሚሆኑ መጡና ጠየቁኝ፡፡ያንኑን በድጋሚ አስረገጡኩትና ተመልሰዉ በመሄድ አምልኮ ጀመሩ፡፡ ወደ አራት ቤተክርስቲናት ተከፍተዉ እያለ 1983 ዓ.ም የደርግ መንግስት መንኮታኮት ሆነ፡፡በመላ አገርቷ ሰላም አልበኝነት ተንሰራፍተዉ ነበር፡፡ በዚህ ስሜት እያለሁ አንድ ቀን 12 ሰዎች ከሩቅ ሲመጡ የተመለከቱት ለሎቹ ጉዳት እንዳያደርሱብኝ አስጠነቀቁኝ፡፡ ወዲያሁኑ 12ቱ ሰዎች ከበቡኝ፡፡ ለካስ የከበቡኝ ልያጠቁኝ ሳይሆን እንዳያጠቁኝ ከለላ ልሰጡኝ ነበር፡፡ ይህንን ነገር በሕይወት ዘመኔ መቼም አልረሳዉም፡፡ እና በመጨረሻም ከኮንታ እስከ ዎላይታ ድረስ የተወሰነ ርቀት እነዚህ ሰዎች ሸኝተዉኝ ስምንት ቀን በእግር ተጉዤ ዎላይታ ገባሁ፡፡

ጳዉሎስ ባልቻ፡- ጠለቅ ያለ የታሪክ ትንታኔ ስለሰጡኝ እግዚአብሔር ዕድሜ ከጤና ጋር  ይስጥልን፡፡ እግዚአብሔር ያክብርልን፡፡

ሰኔ 6 2007 ዓ.ም

Wolaita Today
Wolaita Today
Wolaita Today

በዎለይታ አገር በዳሞታ ጋሌ ወረዳ በቦድቴ ቦልዖ ቀበሌ ከ1550 ዓመታት በፊት በሐውልት ተከላ ዘመን ለታሪካዊነት ፋይዳ በአገሬው ሰው የተተከለው ወጥ ከሆነው ከግራናይት ድንጋይ የተጠረበው የጥንታዊ ዎለይታ ሰው ጥበብ አመልካች የሆነ ያገሩ ተጎበኝ ቅርስ።

Wolaita Today

Dr. Zebdewos Geramo with his Mother-in-Law

Wolaita Today
Wolaita Today

በክቡር ዶ/ር ዘብዲዮስ ጨማ የተፃፈ በamazon ሽያጭ ላይ ያለ መፅሐፍ ይግዙና አጋርነትዎን ይግለፁ