ሞቶ ማዳንን ያስተማረ ጀግና!!!

በአምሳሉ መሠኔ (ቃቆ)

ነሐሴ 19 2012ዓ.ም

የኢፌዴሪ ወታደሮች ከሕዝብ የወጡ በሕዝብ ፍቅር የፀኑ ለሕዝብ ፍቅር የኖሩ መሆናቸውን ይህ ጀግና ወታደር በዎላይታ ንፁሃን የመብት ጠያቂዎችና በሌሎች የኢትዮጵያ ልጆች ላይ በግፍ ጥይት አልተኩስም አልገድልም በማለት ወታደራዊ ግዴታውን በግፍ ላለመወጣት በራሱ ነፍስ ላይ ወስኗል ፤ ጨክኗል፤ ራሱን ሰውቷል፡፡

በክልል ደረጃ ለመዋቀር ሕጋዊና ሠላማዊ ጥያቄ ያነገቡ ባዶ እጅ ያሉ ዎላይታዊያንን መግደል በእርግጥም ኢ-ሞራል ነው፡፡ በዚህ መልኩ ንፁሃንን ከመግደል ይልቅ በራስ ላይ የሚያስወስን የንፁህ ሂሊና ባለቤት የሆኑ የሠራዊት አባላት ከፍ ያለ አክብሮት አለኝ፤ ኢትዮጵያዊነትን በተግባር አሳየን፡፡

በንፁሃን የዎላይታ ነዋሪዎች ላይ የታወጀውን ጦር በቃህ ባይ ጠፋ፤ ሕዝቡ መብቱ ተከብሮ ዎክመ ተመስርቶ ቤቱ እስኪገባ ድረስ ሠላማዊ ትግሉን ይቀጥላል፤ ሰው ገድሎ መጨረስ አይቻልምና፡፡

የዚህ ጀግና ወታደር ሞት በመንግሥት ተመጣጣኝ ያልሆነ ወታደራዊ እርምጃ ዎላይታዎች ላይ እየተወሰደብን ስለ መሆኑ በቂ ማሳያ ነው፡፡ ባዶ እጅ ለመብት ጥያቄ የወጣን ሕዝብ መበተን ቢያስፈልግ ለኢትዮጵያ አድማ በታኝ ጭምብል ለባሽ ወታደር የለምንህ? ስናይፔርና መትረየስ ከመጠቀም ስታዲየም ጭምር የሚጠቀሟቸውን አስለቃሽ ጭስ ወዘተ ተጠቅሞ ማረጋጋት አይቻልም ነበር? ፍርዱን ለህሊና ልተው፡፡

አቤቱ አምላኬ ሆይ ሟች ሊገድላቸው እየቻለ በተዋቸው በእነዚያ በንፁሃን ስም የምለምንህ ለነፍሱ ምህረት ስጥልን፡፡

ኖሮ በግፍ ወገንን ከማስገደል ሞቶ የንፁሃንን ሕይወት መታደግ የተሻለ ክብር አለው፡፡

ሞቶ ማዳንን ከፈጣሪ የተማረ ጀግና!!

አፈር ይቅለለው!!!

ሼምፑዋ ማሮ!!!

Wolaita Today