የወላይታ ዞን ህብር ኢትዮጵያ ዲሞክራስያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት መግለጫ

Wolaita Today

የወላይታ ዞን ህብር ኢትዮጵያ ዲሞክራስያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በዞንና በአከባቢው እየተፈጸመ ባለው በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ያወጣው ባለ አስር ነጥብ አቋም መግለጫ:-

 

መስከረም 05 2013ዓ.ም

የወላይታ ብሔር በክልል የመደራጀት ጥያቄ ያቀረበው ከረጅም ግዜ ጀምሮም እየጠየቀ መቆየቱ ይታወሳል ይሁን እንጂ መንግሥት የወላይታ ብሔር በክልል የመደራጀት ጥያቄ ለማዳከም ብሎም የወላይታ ዞን የፍት አመራሮች ከዞን እስከ ወረደ ድረስ በመቀየር የራሱን የሆኑትን የብልጽግና ፖርት አመራሮች ከዞን እስከ ወረዳ ድረስ ዋና አስተዳደር በማድረግ በከፍተኛ ሹመት እየሰጠ ይገኛል ስለዚህ ይህን ተከትሎ ፖርትያችን ከላይ እንዴ ገለፀው ባለ አስር ነጥበ አቋም መግለጫ አውጥቷል።

1 የወላይታ ህዝብ ራስ በራስ የማስተዳደር ጥያቄ የማይመስል ከሆነው የአመራር መሾም መቀየር ምንም ዋጋ እንዴ ማይሰጥ እና የወላይታ ህዝብ ፍላጎት የማይሟላ እንደሆነ በፅኑ ያምናል።

2 የወላይታ ህዝብ የጠየቀው ጥያቄ ህጋዊ ና ህገመንግስታዊ ሆነው እያለ የወላይታን ህዝብ ንፁሃን ዘጎች የሞቱት ነፍስ ጉዳይ መንግሥት እና የመንግሥት ተላላኪዎች መጠየቅና ለሟች ቤተሰብ መካስ እንዳለበት ፖርትያችን በአፅኖት ይገለጻል።

3 የወላይታ ህዝብ ጥያቄ በራስ በራስ የመደራጀት ጥያቄ እየጠየቀ እያለ መንግሥት የወላይታ ህዝብ ከአጎራባች ዞኖች ጋር በአንድ / ቅርጫት/ ክልል እያለ በማጣላት እና ለማጋጨት ሆን ብሎ ማሰቡ ሆነ ማቀዱን ብሆንም ይህንን ፖርቲያችን ያወግዛል።

4 በአሁኑ ስዓት በወላይታ ሶዶ እና በሃያ ሁለቱ ወረዳዎች የምገኙ የታጠቁ የመንግሥት ኃይሎች የወላይታ ህዝብ በነፃነት ወተው በነፃነት መግባት የከለከለ እንድሁም የወላይታ በስጋት ላይ እየጣለ ስለሆነ መንግሥት የታጠቁ ኃይሎችን ከወላይታ ህዝብ ዘንድ በአስቸኳይ እንድያወጣ ስል የወላይታ ህዝብ ስለምጠይቅ መንግሥት ህዝብ እንድያስፈፅም ፖርቲያችን ይጠይቃል።

5 ምንም እንኳን አሁንም ለግዜው የተረጋጋ ብመሲልም የወላይታ ህዝብ ጥያቄ ህግና ህገመንግስትን በተከተለ መልክ የማይመለስ ከሆነው ከባድና እልህ አስጨራሽ ትግል እንደሆነ ፖርቲያችን በአፅኖት ይገልጻል።

6 የወላይታ ህዝብ ጥያቄ ሳይመለስ በአሁኑ ሳዓት በወላይታ ዞንና ወረዳዎች የተቀመጡ/የተሾሙ አዲስ አመራሮች ሁሉም በወላይታ ህዝብ ዘንድ ምንም ተቀባይነት ምንም እንደሌላቸው የወላይታ ህዝብና ፖርቲያችን በፅኑ ያምናል።

7 መንግሥት በጳጉሜ አንድ ይቅርታ ቀን ነው ብሎ ካመነ በተለያዬ ምክንያት ስሸበር ስቀበዘበዝ የነበረው የኢትዮጵያ ህዝብን መካስና የታሰሩት የፖለቲካ ፖርቲዎችን መንግሥት በርሱ ግዜ ይቅርታ በማድረግ በነፃ መፍታት ስገልጽ ብቻ እንደሆነ ፖርቲያችን ያምናል።

8 መንግሥት በኮሮና ምክንያት በተለያዩ ክልሎች እና ዞኖች የተዘጉ ብሮች እንድከፈቱና ስብሳባ ማከሄድ እንዲያስችል ስለ ፖርቲያችን ያሳስባል።

9 በአሁኑ ስዓት በሽግግር ምክንያት ወደ ስልጣን የመጣው የብልጽግና ፖርቲ እንደ ሌሎች ፖርቲ በአዲስ መልክ እንድወዳደር በአፅኖት ፖርቲያችን ይገልጻል።

10 የወላይታ ታሪክ ባህል ቋንቋ እና የወላይታ የመፍት ተሟጋች እንድሁም ጋዘጠኛች መንግሥት በደከመ መንፈስ ማይቱን የወላይታ ህዝብ ሆነ ፖርቲያችን በፅኑ ያወግዛል።—– ስለዚህ

የተከበራችሁ የወላይታ ዞን ነዋሪዎች

የተከበራችሁ የወላይታ ዞን ምሁራኖች

የተከበራችሁ የወላይታ ዞን ዬላጋዎች

የተከበራችሁ የወላይታ ዞን የፖለቲካ ፖርቲዎች

የተከበራችሁ የወላይታ ዞን ባለሀብቶች

የተከበራችሁ የወላይታ ዞን ሀገር ሽማግሌዎች

የተከበራችሁ የወላይታ ዞን ሴቶች እና ህፃናት

የተከበራችሁ የወላይታ ዞን አርሶአደሮች

የተከበራችሁ የወላይታ ዞን ከተማና የገጠር ነዋሪዎች

የተከበራችሁ የወላይታ ዞን ክብር ተሰናባች ወታደረች እና ሰራዊቶች

የተከበራችሁ የወላይታ ዞን መምህራኖች

የተከበራችሁ ከተለያዩ ክልሎች የመጣችው የወላይታ ዞን ነዋሪዎች

የተከበራችሁ በወላይታ ዞን የምትንቀሳቀሶ ሀገር አቀፋዊ እና ክልላዊ ፖርቲዎች

የተከበራችሁ የፌደራልና የክልል ምክር ቤት አባላት

የተከበራችሁ አካል ጉዳተኞች እና አረጋዊያን ማህበራት በሙሉ

የተከበራችሁ የህብር ኢትዮጵያ አባላት እና ደጋዎች በሙሉ

የተከበራችሁ የህብር ኢትዮጵያ የወላይታ ሀያ ሁለቱ ስራ አስፈፃሚዎች

የተከበራችሁ የዞን አመራሮች እና አባላት በሰሞኑ የክልልና የፈደራል መንግሥት ባለድርሻ በወላይታ ዞን ምክር አባላትን በመከላከያ አፋሙዝ አስፈራርቶ ያለህዝብ ፍቃድ ስብሰባን አሰባስቦ በማስፈረሙ ይታወሳል ስለዚህ ከላይ የተጠቀሳችቱ ህዝቦች ሆይ በአሁኑ ስዓት በአዲስ መልክ የተመረጡ የወላይታ ዞን አመራሮች እና የወረዳ አስተዳደሮች የወላይታ ህዝብ ጥያቄ ሳይመለስ በወላይታ ህዝብ ዘንድ ምንም አይነት ተቀባይነት እንደሌላቸው ከወድሁ መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

ህብር ኢትዮጵያ ዲሞክራሳዊ ፓርቲ የወላይታ ዞን ጽ/ቤት ይገልጻል

ድል ለወላይታ ህዝብ ድል ለጭቁን ህዝብ።

አቶ ታድዮስ ጭናሾ

የፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ