ቤተክርቲያንና ፖለቲካ

Wolaita Today

በራፍኤል አዲሱ

August 11, 2020

የኢትዮጵያ_ወንጌላዊያን_አማኞች እና የቤተክርቲያን መሪዎች የፖለቲካ አመራሮችን መፅሀፍ ቅዱሳዊ መሰረትም ሆነ የመለኮታዊ ምሪት እውነታ በሌለውና ከሀይማኖታዊ ቡድንተኝነት ብቻ በሚመነጭ አመክንዮ ላይ ቆማችሁ የግለሰቦችን ሀገር የመምራት ብቃትና የሀገሪቱ ህዝቦች ለሚተዳደሩበት የበላይ ህጎች ያላቸውን ታማኝነትና ተገዥነት ባላገናዘበ መልኩ እውቅና እና ድጋፍ (endorsment) እየሰጣችሁ ምዕመኖቻችሁን በማሳታችሁ እና በሀገሪቱ የተለያዩ አከባቢዎች ለሚፈሰው የንፁሀን ደም ምክንያት እየሆናችሁ በመሆናችሁ በከፊልም ቢሆን ተጠያቂ ናችሁ:: ምክንያቱም የምድሪቱ “አቤሎች” ደም ሁሌም ወደ አምላኳ ትጮሀለችና!!

ለእግዚአብሔር መንግስት ዘላለማዊ እና መለኮታዊ የዘመናት መንፈሳዊ አጀንዳ (eternal and devine spiritual agenda of the ages) ምድራዊና አለማዊ (earthly and secular) መልክ ሰጥታችሁ ህዝቡን ማሳታችሁ ከመሰረታዊው (fundamental) የትውልድ የወንጌል ተልዕኮአችሁ ያፈነገጠ አካሄድና የቤተክርስቲያንን ተልዕኮ በፖለቲካ ፍላጎቶች (political interests) የመበረዝ አካሄድ በመሆኑ ከስህተት መስመራችሁ ተመልሳችሁ ብትታረሙ ምዕመኑንም በእግዚአብሔር ቃል እውነት ብቻ ብታንፁና ሌላውን ጉዳይ ለሚመለከታቸው አካላት በመተው ለሀገርና ህዝብ ሀላፊነት እንዳለባት ቤተክርስቲያን በፀሎታችሁ ብትደግፉ ለሁሉም የሚበጅ መልካም ተግባር ነው የሚሆነው::

እግዚአብሔር ሁሌም ያያል፤ ጊዜውንም ጠብቆ በእውነት ይፈርዳል!!!