እንደ ሀገር ከታሪክ ስህተቶቻችን እንማር የተጠራቀሙ የቤት ስራዎቻችንም እንስራ!!

ራፍኤል አዲሱ     –  ጥቅምት 27 2013ዓ.ም

ኢትዮጵያ ውስጥ እስከአሁን ያልተሞከረ ስርዓተ መንግስት ያለ አይመስለኝም:: ሆኖም ይኸው ውጤታማ ከሆነበት የሌሎች የአለማችን አገሮች አተገባበር በተቃራኒ ስልጣን የያዘውን ቡድንና ተቀፅላዎቹን ብቻ በሚጠቅምና የሀገራችንን ህዝቦች በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ በሚጨቁን መልኩ ተግባራዊ ስለሚደረግ ብቻ ሁሌም fail እያደረገብን ከዜሮ ስንጀምር ኖረናል:: ከታሪክ የማንማርበት እውነት ሁሌም እዚያው አዙሪት ውስጥ መልሶ መላልሶ ሲከተንም እየተስተዋለ ነው:: ሞክረን አይተነው ያልሰራውን ነገር እ.ኤ.አ. ከ1974ም ሆነ ከ2018 እንዲያልፍ መፍቀድ ራሳችን እንደሀገር ለውድቀት ማዘጋጀት ነው::

በሌላ ጎኑ ኢትዮጵያ አሁን ከደረሰችበትና ከገባችበት ፖለቲካዊና ማህበራዊ እውነታ አንፃር ከፌዴራሊዝም ስርዓት ውጭ ሀገሪቱን ሳትፈራርስ አንድ ላይ ሊያቆይና ሊያቆም የሚችል አማራጭ ይኖራል ብሎ ማሰብ አስቸጋሪ ነው የሚሆነው:: የተሻለ የሚሆነው በአመት አንዴ “ብሔር ብሔረሰቦች” በአደባባይ ተሰብስበው የ”ብሔር ብሔረሰቦችን” ጭፈራ ከማሳየት የዘለለ እውነተኛ ፌዴራሊዝምን እውን በማድረግ የተሻለና እውነተኛ sub-national አስተዳደራዊ autonomy ያላቸው አከባቢዎችን true functionality ያረጋገጠ የፌዴራል ስርዓት መተግበር ነው::

ይህ ሊሆን የሚችለው ግን የተለያዩ ፅንፍ የያዙ “መጤ”: “ሰፋሪ” የሚሉ ዘመኑን የማይመጥኑ ስንኩል አስተሳሰቦችንም ሆነ አንድነትአንድ_አይነትነት አድርጎ በማሰብ በሌሎች ላይ የራስን hegemonic will በመጫን የመጨፍለቅ ዝንባሌ ያላቸውን የ19ኛው ክፍለ ዘመን ምኞታዊ የቅዠት አስተሳሰቦችን (wishful delusional thinkings) ማስወገድ የቻልን እንደሆነ ብቻ ነው:: አሁን በሀገሪቱ በሚገኙ ሁለቱም የፖለቲካ ጎራዎች ፅንፍ የያዙ አመለካከቶች unlearn መደረግ ያለባቸው ከመሆኑም በላይ የፖለቲካ ማህበረሰቡ ዘዋሪዎች በelite consensus ለሁሉም የሚሆን middle ground ለማግኘት ቢሞክሩ የተሻለ ነው::

በአለማችን ብዙ ህብረ ብሔራዊ ሀገራት እጅግ ውጤታማ የሆኑ የፌዴራሊዝም ስርዓት ገንብተው የተረጋጋ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ምህዳር ፈጥረዋል:: የህዝቦቻቸውን እኩልነት: ርትዕ: ፍትሀዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትና የፖለቲካ ውክልና አረጋግጠዋል:: የዜጎችን በሀገራቸው ከቦታ ቦታ በነፃነት ተንቀሳቅሰው የመኖር: ሀብት የማፍራትና በየትኛውም የሀገራቸው አከባቢዎች እኩል የማህበራዊ መብቶቻቸው ተጠቃሚ የመሆን የዜግነት መብቶቻቸው ተከብሮላቸው መኖር ያስቻሏቸውን ተቋማዊ ዴሞክራሲ ገንብተዋል:: ይህን ማድረግ በመቻላቸውም በዘላቂ ልማትና የእድገት ጎዳናዎች መመረሽ ስላስቻላቸው ዛሬ ላይ እኛ የእነሱ ተመፅዋች የመሆናችን ነገር የአደባባይ ሀቅ ነው::

ለሀገራችን በትክክል የሚሆናት ምን አይነት ፌዴራላዊ ስርዓት ነው የሚለው ጠለቅ ያሉ ጥናቶች ተደርገውበት ያሉ ስርዓታዊም ሆነ መዋቅራዊ (structural) የአፈፃፀም ማነቆዎች የሚቀረፉባቸውን መፍትሄዎች ከተለያዩ የሀገሪቱ የህብረተሰብ ክፍሎችም ሆነ ህዝቦች ጋር እስከታች ባሉ መዋቅሮች ወርዶ በመነጋገር መግባትን በመፍጠር ተግባራዊ ማድረግ የኛው የቤት ስራ ነው:: የቤት ስራችንን በአግባቡ ሳንሰራ በመቅረታችን በተፈጠሩ ችግሮች የተነሳ በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ባሉና በብዝሀነት በሚገለፁ ተመሳሳይ ሁኔታዎች effectively እየሰሩ ያሉ ውጤታማ የሆኑ ስርዓቶችን በደፈናው አይሆኑንም ብሎ ወደመደምደም መሄድ ውድቀትን አስቀድሞ መቀበል ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው::

አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የዴሞክራሲ ተቋማት አለመብቃታቸው: መሬት ላይ ያሉ ፅንፍ የያዙ አመለካከቶች: እንዲሁም ተቋማዊ የአፈፃፀም ችግሮች ደረጃ በደረጃ መቀረፍ የሚችሉ ናቸው:: ይህን ማድረግ የምንችለው ግን በተለያዩ የትምህርት ተቋማት በስርዓተ ትምህርቱና በሲቪል ሰርቪስ ተቋማት የስርፀት ተግባራዊ ስልጠናዎች (on the job indoctrinations) በተካተተ መልኩ ነባራዊ ሀገራዊ እውነታችን በውጤታማ አለም አቀፍ ልምዶችና በextensive ሀገራዊ ጥናቶች በመታገዝ እንዲሰጡ በማድረግ የአስተሳሰብ ችግሮችን በመቅረፍ የጀመርን እንደሆነ ነው::

ከአፈፃፀም ጋር በተያያዘ ስር የሰደዱ መዋቅራዊ ችግሮች ጠንካራና ገለልተኛ የዴሞክራሲ ተቋማትን በመገንባትና ህዝባዊ መሰረት እንዲኖራቸው በማድረግ መቅረፍ ይቻላል:: በተለይም አስፈፃሚ አካላትን በተመለከተ ተግባራዊ መመዘኛዎችን በማካተት እና ጠንካራና ተፈፃሚነት ያላቸውን ህጎች በማውጣትና ተጠያቂነትን በማረጋገጥ እንዲሁም የፍትህ ስርዓቱ completely independent and empowered እንዲሆን በማድረግ ወደ ጠንካራ የማስፈፀም አቅም መሸጋገር ይቻላል:: በዚህ መልኩም ተቋማዊ ህግ የማስፈፀም አቅማችንን በማጎልበት ፖሊሲዎችንና አዋጆችን ሳይሸራረፉ ወደመሬት ማውረድ ዋነኛው ግብ ነው የሚሆነው:: ይህን ማሳካት ስንችል ደግሞ እውነተኛና practical የሆነ ፌዴራላዊ ስርዓትን በማስፈን ተቻችሎ ተዛዝሎ የሚኖር (harmoniously coexisting) እና ሀገራዊ አንድነቱ የተጠበቀ አንድ ሀገራዊ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ማህበረሰብን መፍጠርም ይቻላል::

 

wolaita Today