በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ግንቦት 17 2012 ዓ.ም ድረስ ብቻ በተደረገ የኮሮናቫይረስ ምርመራ 436 ነዋሪዎች በቫይረሱ መያዛቸው መረጋገጡ ተገለፀ።
የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው በከተማዋ የኮቪድ-19 መያዛቸው ከተረጋገጠ ሰዎች መካከል 174 የሚሆኑት ምንም አይነት የጉዞ ታሪክም ሆነ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ የላቸውም።
ከእነዚህ መካከል በልደታ ክፍለ ከተማ ብቻ 122 ሰዎች ሲገኙ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ደግሞ 69 ነዋሪዎች፣ በሶስተኛነት በቦሌ ክፍለከተማ 54 ሰዎች ተይዘው እንደሚገኙ አስታውቋል።