እናት ልጇን በላች፡፡
ጥቅምት 01 2013ዓ.ም
በአንዱአለም ቦልጠና
ልጆቿን ቅርጥፍ አድርጋ እየበላች የምታነባ እናት እኮ ግን ትገርማለች፡፡ እንዳትተወው ርሃቡ እንዳትበላው ልጇ ሆኖባት ብትዘገይም የሆዷ ነገር አላስቻላትም፡፡ እናት ልጇን በላች፡፡ ይህ ነው፡፡ አማራ ክልል አፋር ሶማሌም ዎላይታም የሚሆነው ይኸው ነው፡፡
ቦዲቲ ላይ ንጹሃንን አስተኩሰህ አስገድለህ መልሰህ ስም አሰጥተህ በመሳደቢያ ሚዲያዎች ህዝብ አሰድበህ ቢቀርስ? ክብር ከከርስ የቀድማል፡፡ ህልውና ከገንዘብ የቀድማል፡፡ ፖለቲካዊ ነጻነት ከምንም ይቀድማል፡፡ ሼህ አላሙዲን ገንዘብ አለው፡፡ ፖለቲካዊ ነጻነት ስለሌለው ግን ገንዘቡ ሊያድነው አልቻለም፡፡ በትንንሽ ገንዘብ የክለብ ዝውውር የሚያደርጉ ሰዎች እኛ ብልጠት አጥተን ይመስላቸዋል፡፡ በአክሮባት ያገኟትን ገንዘብ የሌባ ዘር እየተባሉ ከመብላት ተከብሮ ሰርቶ መብላት ይሻላል፡፡ ሌባ አስብል ብሎ እንደሚሰጥህ ሰው አንተስ ሰጪ የምትሆነው መቼ ነው? እንደ ሙሉ ሰው ማሰብ መከወን እና መኖርስ የምትችለው መቼ ነው? በሰበሰብካቸው የአክቲቪስት ነን ባዮች የቃላት ጋጋታ በተጋነኑ አገላለጾች ይህ ክፍተትህ አይሸፈንም፡፡ መንግስት የሚያክል ትከሻህን መታ እያደረገ አይዞሀ አለሁልህ እያለህ የሸሸህ ሞገስ ምን ሲደረግ ሊመጣ ነው?
ለሞቱት ነፍስ ይማር! ላዘኑት መጽናናትን ይስጥ!