ለኢትዮጵያ ክብር በካራማራ በናቅፋና ባድመ ተራሮች የተሰዉ የወላይታ ህዝብ ጀግኖች ሰማዕታት አፅሞች በሰላም ማረፍ አልቻሉም!!
August 11, 2020
ይኼን መካናይዝድ ክፍለጦር ብቻ የሚታጠቀውን ከባድ መሳሪያና የሀገር ዳር ድንበር ከወራሪ ጠላትና አጠቃላይ የሀገሪቷንና የህዝቦቿን የግዛት ደህንነት ለመጠበቅ የሰለጠነ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ወታደር ወላይታ ልኰ ህፃናትን ከሚገድልና የነገ የሀገር ተረካቢ የወደፊት ተስፋ የሆነን ወጣት ከሚያስጨፈጭፍ ግድቡን እንዲጠብቁ ቢያሰማራ እውነተኛ የሀገር ተቆርቋሪ ያሰኘው ነበር:: የጀማሪ አምባገነን ነገር ሆነና ነገሩ እንደዚህ ሀገሪቱን በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ፊት አንገት ያስደፋና የሚያሳዝን ነገር ተፈፀመ!!
የሀገር መከላከያ ሰራዊትም ቢሆን ካለበት ሀገራዊ ተቋማዊ ሀላፊነትና mandate በዚህ ደረጃ ወርዶ በሰላማዊው የወላይታ ህዝብ ልጆች (ህፃናትና የነገ ሀገር ተረካቢ ወጣቶች) ላይ የጥይት ዝናብ በማዝነብ እንደ መንደር ሚሊሻ የግለሰቦች አጀንዳ ማስፈፀሚያና የህገወጥ የፖለቲካ ቡድኖች መጠቀሚያ መሆኑ በባድመ አውደ ውጊያ ለኢትዮጵያ ደህንነትና ክብር የተዋደቁና የተሰዉ ከ25,000 (ሀያ አምስት ሺህ) በላይ ከወላይታ ህዝብ አብራክ የወጡ ጀግኖች: በካራማራና ሌሎች ታላላቅ አውደ ውጊያዎች ለሀገር ክብርና አንድነት ለተዋደቁና ለተሰዉ በመቶዎች ሺዎች የሚቆጠሩ የወላይታ ህዝብ ጀግኖችና ሰማዕታት አፅማቸው በሰላም እንዳያርፍ የሚያደርግ ጀግኖች ልጆቿ ለሀገር የከፈሉትን ውለታ የበላ አሳዛኝ ተግባር ነው::
መንግስታዊ ሽብርተኝነት Ethiopia
State Terrorism