የወላይታ ገናና ታሪክ ያኮሰመነ የታሪክ መማሪያ መጽሐፍ

በአዳነ አይዛ (የታሪክ ተመራማሪ)

 

ይህ ለመማሪያ ተብሎ የተዘጋጀ ከሆነ መሠረተዊ የታሪክ ስህተቶች ያሉበት ስለሆነ ታትሞ ከመሠረጨቱ በፊት ሊስተካከል ግድ ይላል። ከጽሁፉ ስህተቶች የመጀመሪያው የታሪኩ ባለቤት የሆነው ህዝብ እና የህዝቡን ባህልና ታሪክ እንዲያለማና እንዲያሳድግ ሥልጣን የተሰጠው የባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሃሣብ ያልተጠየቀበትና ያልተቸው መሆኑ ነው።

ሌለዉ መሠረተዊ ስህተት የህዝቡን ታሪክ በተዛባ መልኩ ያስቀመጠ መሆኑ ነው። ከዚህም መካከል አንዱ የወላይታ መንግስታዊ አስተዳደር የጀመረው ከ13ኛው መቶ ክፍለዘመን ጀምሮ ነው የሚለው ሲሆን በርካታ በብሔሩ ታሪክ ላይ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚገልጹት ከሆነ ወላይታ በሦስት ስርወ መንግስታት በሃምሳ በራሱ ነገስታ የተዳደረ ህዝብ ነው። ይህንን በበርካታ በተጻፉ ማስረጃዎች ማረጋገጥ ይቻላል። ይህን መነሻ ስናደርግ የወላይታ ህዝብ እንደ ማንኛውም የአፍሪካ ህዝብ በተበታተነ መልኩና በጎሳ አስተዳደር ከክርስቶስ ልደት በፊትም ጀምሮ በአካባቢው የነበረ ህዝብ ሲሆን መረጃዎች እንደሚየሳዩ ከ4ኛው ክ/ዘመን መጀመሪያ አካባቢ ጀምሮ ጠንካራ የመንግስት አስተዳደር መሥርቶ መኖር እንደጀመረ ይታወቃል።

ሌላው የዚህ ጽሁፍ ስህተት አሩጂያ ከወላይታ ሰርወ መንግስታት አንዱ ሲሆን በቁጥር 10 ነገሥታት በቅደም ተከተል ነግሰዋል። ነገር ግን ጽሁፋ አሩጂያ፣ ባዳ፣በዲግላ የተባሉ ወላይታ ላይ መንግስት ከመመስረቱ በፊት በአካባቢው የነበሩ ህዝቦች አድርጎ ማቅረቡ ፍጹም የተሳሳተ ትርክት ነው። ምክንያቱም ባዳና ባዲግላ ከአሩጂያ አሥር ነገስታቶች ውስጥ የሚገኙ የነገስታቱ ስሞች ናቸው እንጂ በወላይታ መንግሥት ከመመሥረቱ በፊት በአካባቢው የነበሩ ህዝቦች ተደርገው ሊወሰዱ አይገበም። በህዝቡ ታሪክ ላይ የሚደረጉ ጥናች በቀጠሉ ቁጥር አዳዲስ ግኝቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ነገር ግን አሁን ባሉ የጥናት ውጤቶች ላይ ተመሥርቸን ስንመለከት አገላለጹ ስህተት ያለበት በብሔሩ ታሪክ ላይ ጥናት ካደረጉ ምሁራን ጋር የጋራ መግባባት ሳይደረግ ለመማሪያነት መዋል የለበትም፡፡
ጽሁፋ የወላይታ ገናናነት የጀመረው በ18ኛው ክ/ዘመን መጨረሻና በ19ኛው ክ/ዘመን መጀመሪያ ነው የሚለው የህዝቡን ገናና ታሪክ ያኮሰመነ ድርሰት ነው። ምክንያቱም የወላይታ ገናና ተሪክ ጫፍ የደረሰው በጥንት የዳሞት/የወላይታ/ መንግስት በተለይም በንጉስ ሞቶሎሚ ዘመን ሲሆን በ19ኛው መ/ክ/ዘመን የነበሩ የወላይታ ትግሬ ስርወ መንግስት ነገስታት ይህንን ገናና ታሪከ እስከ ዳግማዊ ምንሊክ ወረራ ድረስ አስቀጥለዋል።
ሌላው በጽሁፋ ላይ የተጠቀሰው ስህተት ወላይታ በ18ኛው ክ/ዘመን መጨረሻና በ19ኛው ክ/ዘመን መጀመሪያ አጎራበቾችን በመውረር ባደረገው የድንበር መስፋፋት እና በዚህም በተገኘ የማቴሪያል ጥቅም ነው በጊዜው ገናና የነበረው የሚል እንደምታ ያለው ሲሆን ይህም ቢሆን ከተሪካዊ እውነታ ያፈነገጠ አገላለጽ ነው። ምክንያቱም ወላይታ በአንድ ወቅት በአሁኗ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰፊ ግዛት የነበረው ህዝብ ሲሆን በተለይም ከገናናው ንጉስ ሞቶሎሚ በኋላ በተፈጠሩት መቀዛቀዞችና በአካባቢው በነበረው የህዝቦች ንቅናቄና ፍልሰት ምክንያት ቀደም ሲል የነበረውን ድንበሩን አጥቶ በ19ኛው መቶ ክ/ዘመን መጀመሪያ አሁን ባለበት ተወስኗል እንጂ በዘመኑ ለነበረው ገናናነት ከጎረቤት ወርሮ የያዘው ስንዝር መሬት እንዳልነበረ በብሔሩ ታሪክ ላይ የተደረጉ ጥናቾች ያሳያሉ።

መንግስት ቀደምሲል በሀገራች የነበረዉ የታሪክ ትምህርት ካሪኩለም የሁሉንም ብሔር ብሔረሰቦችን ታሪክ የማይወክል በመሆኑ እንዲሻሻል የወሰደው ቁርጠኝነት የሚደገፍ ተግባር ቢሆንም ማሻሻያው ከምሁራን በተጨመሪ የታሪኩ ባለቤት የሆነውን ህዝብ ካላሳተፈ ከድጡ ወደማጡ እንዳይሆን መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡

Create eBooks In 60 Seconds!

Sqribble