ጠ/ሚ አብይ አህመድ (ዶ/ር) እንደ ኢትዮጵያ መሪ እንድቀበላቸው…

በአንዱአለም ታደሰ ቦልጠና

ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አብይ አህመድ (ዶ/ር) እንደ ኢትዮጵያ መሪ እንድቀበላቸው መንግስታቸው የሚቀጥሉትን መከወን አለበት!!!
1/ የደቡቢቷ ኢትዮጰያን ፖለቲካዊ ቀውስ መፍታት፣ በተለይ በወላይታ ትውልድ ተሻጋሪ ቀውሶችን ከምንጫቸው ማድረቅ

2/ ዎብን እንዲፈርስ በፌደራል በጀት ስሙን ከማልጠቅስ ዩኒቨርሲቲ ካዝና ወጪ የሚደረገውን ፋይናንስ አክሎም ለዚሁ እና ተያያዥ ለሆነ አላማ ዩኒቨርሲቲውን ጨምሮ ከዞን ከክልል እና ፌደራል የሚደረግ የሰው ሃይል ስምሪት ማስቆም

3/ ሃገሪቷ የምትመራባቸውን ፖሊሲዎች ግልጽ ማድረግ

4/ በዎላይታ ላይ የያዘውን በጠላትነት ላይ የተመሰረተ የትግበራ ፖሊሲ እና አቋም ማስቀየር

5/ ግለሰባዊ ጥቃት አድራሾችን እጅ እንዲሰበስቡ ግልጽ ትእዛዝ መስጠት

ይህ ካልሆነ እሳቸውንም ሆነ መንግስታቸውን የሃገረ ኢትዮጵያ የቀውስ ምክንያት አድርጌ ለማመን አገደዳለሁ፡፡ በእንዲህ ሁኔታ ያመንኩትን ማንንም ሆነ የትኛውንም አካል እስትንፋስ እስካለኝ ድረስ እፋለማለሁ፡፡ እውነቱን ሲረዱ ለሚፋለሙት ሁሉ እገዛ አደርጋለሁ፡፡ እውነትን ተፋልሞ ያሸነፈ የለም፡፡ የስልጣን ጉልበት እውነት ላይ ብቻ ነው ያረፈው፡፡ የስልጣን ሁሉ ምንጨ እና ባለቤት የሆነው ፈጣሪ ራሱ እውነት እና የእውነትም ምንጭ ነው፡፡ ዕውነትን የተጋፋ አይቆምም፡፡ እውነት ሃይል ናት፡፡ እውነት የፍጣሪ እስትንፋስ የትንፋሹም አካል ናት፡፡ ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም የሚኖራት ህዝቧም እርግት የሚለው እንደ ሃገር የምትጸናውም በሴራ ሳይሆን በእውነት እና በእውነት ብቻ ነው፡፡

እንከን በእንከን የሆነው አዲሱ የታሪክ ትምህርት መጽሐፍ ዝግጅት

በቴዎድሮስ

ከዚህ በፊት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይሰጥ የነበረው የታሪክ ትምህርት መቆሙና አሁን መንግስት በአዲስ መልክ እያዘጋጀ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ይህ ለትምህርት ተብሎ እየተዘጋጀ ያለው ሰነድ መሠረተዊ የታሪክ ስህተቶች ያሉበት ስለሆነ ታትሞ ከመሠረጨቱ አስቀድሞ ሊስተካከል ይገባል።
ከጽሁፉ ስህተቶች የመጀመሪያው የታሪኩ ባለቤት የሆነው ህዝብ እና የህዝቡን ባህልና ታሪክ እንዲያለማና እንዲያሳድግ ሥልጣን የተሰጠው ህዝብ የወላይታ ታሪክ ተመራማሪዎች ሃሣብ ያልተጠየቀበትና ያልተቸው መሆኑ ነው።
ሌለዉ መሠረተዊ ስህተት የህዝቡን ታሪክ በተዛባ መልኩ ያስቀመጠ መሆኑ ነው። ትናንት ህዝቦች ላይ የደረሰው የታርክ ዝርፊያ እና መበረዝ አሁን እየተዘጋጀ ባለው የታርክ ትምህርት መጽሐፍ ላይ መደገም ያሳዝናል፤ የታርክ ተመራማሪዎች ነገ የትውልድ ተወቃሽመሆናቸውንማወቅአለባቸው፡፡

የወላይታ ህዝብ መንግስታዊ አስተዳደር የጀመረው #ከ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ነው; የሚለው ሲሆን በርካታ በብሔሩ ታሪክ ላይ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚገልጹት ወላይታ በሦስት ስረወ መንግስታት በሃምሳ በራስ ነገስታ ይተዳደር የነበረ ህዝብ ነው። ይህንን በበርካታ በተጻፉ ማስረጃዎች ማረጋገጥ ይቻላል። ይህን መነሻ ስናደርግ የወላይታ ህዝብ እንደማንኛውም የአፍሪካ ህዝብ በተበታተነ መልኩና በጎሳ አስተዳደር ከክርስቶስ ልደት በፊትም ጀምሮ በአካባቢው የነበረ ህዝብ ሲሆን መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከ4ኛው ክ/ዘመን መጀመሪያ አካባቢ ጀምሮ ጠንካራ የመንግስት አስተዳደር መሥርቶ መኖር እንደጀመረ ነው። ነገር ግነ አዲሱ የታሪክ ትምህርት መጽሐፍ ዝግጅት ስለወላይታ ደቡብ በምለው ውስጥ ቁንፅል ነገር በማስቀመጥ ያለፋል፡፡
የኢትዮጵያ ታርክ የተወሰኑት ብሔር ብሔረሰብ ታርክ ሳይሆነ የሁሉም መሆን አለበት፤እስከ ኬንያ ሮዶልፍ ሃይቅ ድረስ የገዛውን ካዎ/ንጉስ ሞቶሎሚን/KAWO MOTOLOMI በኢትዮጵያ ታርክ ውስጥ ሳታካትት የኢትዮጵያን አንድነት አታመጣም፡፡

ልጆቻችን የሁሉም ኢትዮጲያዊያን ታርከ ሳይቀየር ሳይበረዝ ሳይዛነፍ መማር አለባቸው፡፡
በመንግስት እየተዘጋጀ ባለው የታርክ ትምህርት መጽሐፍ ላይ ከተለያዩ ህዝቦች የተወጣጡ የታርክ ተመራማሪዎች በማሳተፍ ግልፅ ውይይት በማድረግ፣ ልጆቻችን ነገ በኢትዮጲያዊነታቸው ኮርተው አንድነት ተስምቷቸው የሚማሩበት ሰነድ ቢያዘጋጅ መልካም ነው፤ ከትናንት ስህተት ሳንማር ነገ ልጆቻችን የሚሸማቀቁበት እና የሚጋጩበት የታሪክ ትምህርት ተዘጋጅቶ ሌላ የፖለቲካ ማህበራዊና ኢኮነኖሚያዊ ቀውስ ለኢትዮጵያ አይጠቅማትም!!!

 

 

 

COVID-19 Support in Wolaita, Ethiopia