ብዙ ጊዜ ተመዘናችሁ ግን ቀላችሁ ተገኛችሁ ሂዱልን!!!
በአሰፋ አየለ
August 04, 2020
የአንዳንድ ጊዜ ማህበረተሰብ በፖለቲካ መዳ ላይ በቀጥታ በእጁ ጣት በተመረጡ ተወካዮቻቸው ይወከላሉ። የሆነ ሆኖ እንደ እኛ ያላደጉ አገራት ላይ ህዝቦቹ ያለመታደል ሆኖ በቀጥታ በመረጧቸው ተወካዮቻቸው የመወከል እድልን የሚሰጥ ስርዓት እያላቸው ግን በህዝብ ሳይሆን በመሪ ፖለቲካ ፓርቲ (ብልጽግና) ተመርጧል፤ የስልጣን ጣሪያ በያዙት ራስ ወዳድና ከህዝብ ጥቅምና ክብር አስበልጦ የራሳተውን ዝናና ክብር በሚያስቀድሙ ካድሬዎች የመወከልና የመወያየት እድል ያገኛሉ። ይህ ችግር የሚፈጠረው ከሥርዓቱ ሳይሆን ግን ከመሪው ድርጅትና አመራሮች ከተወላገደ አቋም ይመነጫል። እንግዲያውስ ታላቁ የወላይታ ህዝብ በክልል የመደራጀት ህገ መንግስታዊ ጥያቄ በህዝብ በቀጥታ ሳይሆን ድርጅታቹሁ በተመረጣችሁ በእናንተ እጅ ባይገባና ይህንን ጥያቄ በቀጥታ ከሚመለከተው አካል ጋር የሚገናኝ ቀጥተኛ የሆነ የህዝብ ተወካይ ብኖር ኖሮ የት በደረሰ? አሁን ግን ራሳችሁ በሰጣቹት ውጤት ባለፈው ሳምንት 85% ደርሶ የነበረው ራሳችሁ በፈጠራቹት የፈጠራ እርቅ ሰበብ ያው አሁን 0% ገብቷል።
ስለዚህ አሁን ባላችሁ የህዝብ ውግንና አቋማችሁ ሲታይ በጭራሽ ወላይታን የማሻገርና ወዳለመው ክልል የማድረስ የሥነልቦና ይሁን የፖለቲካ አቋም ስለሌላችሁ ከወላይታ ህዝብ ጫንቃ ላይ ውረዱ። እናንተ ለስልጣን ካላቹ ጥማታቹ የተነሳ አሁንም የስልጣን ሹክቻ እያላቹ ታስወራላቹ ነገር ግን ይሄንን ያልኩት በዞናችን የመሰረታቹት መንግስት የህዝብን መሬት ከመሸጥና አንዱን ከሌላው እየነጣጠለ አንደኛውን ሌብነትን ማስተማር ቀሪውን ደግሞ “ሽብርተኛ ነው” እያላቹ ከማወጅና አንዳንድ ከህልናቸው ይልቅ እናንተ የሚትከፍሉላቸውን ልቂምቃም ገንዘብ እያሳደዱ በምትመሩት ህዝብ ላይ ሰላይ አድርጋቹ ከመቅጠር እንድሁም የሚናከብራቸውንና ለህዝብ ተብሎ የተቋቋመውም የአገር ሽማግለዎችን የእናንተ የፖለቲካ ዓላማ ማስፈጸምያ ተላላኪ ከማድረግ ውጭ ለወላይታ ህዝብ አንድም የሚታይና ወደፊት የሚወስድ ጠብ የሚል ሥራ ስላልሰራቹ ከእንግድህ የወላይታ ህዝብ ትከሻ ላይ ከዚህ በላይ ልሸከሟችሁ ስለማይችል ስልጣን የህዝብ ነውና የህዝብን ስልጣን ለባለቤቱ እንድታስረክቡ እያልኩ ይህ ካልሆነና የራሳቹን ማደነጋገርን በመቀጠል የዚህን ህዝብ ህልውና እናጠፋለን ካላቹ ልፈጠር ያለው ነገር ሁሉ ተጠያቂዎች መሆናችሁን እወቁ።