የወላይታ ሕዝብ ላይ ከፍላጎቱ ውጭ ሊጭኑበት የታሰበው የትኛውም ‘የጉያ አማራጭ’ አደረጃጀት ተቀባይነት የለውም !
በወርቅነህ ገበዬሁ
የወላይታ ሕዝብ ከነበረበት ስልታዊ ጭቆና ራሱን ነፃ የሚያደርገውን ትግል ላለፉት በርካታ አመታት ሲከውን ቆይቷል። ይህም መዋዕቅራዊ ምክኒያቶች በፈጠሩት ችግሮች በኢኮኖሚው የበይ ተመልካች እንዲሆን ፤ በፖለቲካዉ በአገር አቀፍ ደረጃ ሊጫወት የሚችልበትን ዕድል ነስቶታል፤ በማህበራዊ ትስስሩም በተለይም ከአጎራባች ሕዝቦች ጋር በፖለቲከኞቻችን የልህቀት ማነስ የተነሳ ይህም ባስከተለው አጎራባች ሕዝቦች ወላይታን በተለየ ጥርጣሬ ጭምር እንዲመለከቱ እና ለዘመናት የነበረው የወንድማማችነት መንፈስ እንዲላላ በሚያደርግ ሁኔታ ውስጥ አስገብቶ ቆይቷል።
ስለሆነም ወላይታ ከራሱ ከህዝቡ በፈለቀው ከእነዚህ መሰረታዊ ችግሮች ለመላቀቅ ራሱን ዳግም ለማደራጀት በተከተለው ‘የወላይታ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት’ ለመመስረት እያደረገ ያለውን ትግል በየትኛውም አማራጭ እንደማይቀይር ሊታወቅ ይገባል። ከዚህ ሙሉ የሕዝብ ፍቃድ እና ይሁንታ ካገኘው አደረጃጀት ውጭ የሚድረጉ ‘በጉያ የተያዙ’ አማራጮች ፈፅሞ ተቀባይነት የላቸውም። እነዚህ ‘የጉያ አማራጮች’ ሕዝብን ይባስ ጭቆና ውስጥ የሚከቱ መሆናቸው ሊታወቅ ይገባል። ስለሆነም የወላይታ ሕዝብ ላይ ከፍላጎቱ ውጭ ሊጭኑበት የታሰበው የትኛውም ‘የጉያ አማራጭ’ አደረጃጀት ይቀለበሳል !
ስለሆነም የሚከተሉት ሃሳቦችን ማንፀባረቅ ያስፈልጋል…
- በግልሰብም ሆነ በቡድን ደረጃ የሕዝብን ይሁንታ ያገኘውን ከ’ዎላይታ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት’ ውጭ ያሉ አደረጃጀቶችን ከሕዝብ ደብቀው ለማስፈፀም የነበሩ እና ወደ ፊትም ሊኖሩ የሚችሉ እንቅስቃሴዎች ሊገቱ ይገባል። በየትኛውም ደረጃ ያለ የመንግስት ባለስልጣን ሆነ በየትኛውም ደረጃ ላይ የሚገኝ ሕዘበኛ ለዚሁ ሃሳብ ሊቆም እና ሊገዛ ይገባል።
- በወላይታ ሕዝብ የሚደረግ የትኛውም እንቅስቃሴ ሆነ ውሳኔ የሕዝቡን ፍላጎት/ስምምነት/ ያማከለ እንደሆነ ማወቅ ያስፈልጋል። ለዚህም ሰለ ወላይታ ሕዝብ ይገደኛል የሚል የትኛውም ግለሰብ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል። ትክክለኛውን እና እውነተኛውን መረጃ በማድረስ ሕዝብ ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት የሚቀለብስ መስዋዕትነት ከእያንዳንዱ ግለሰብ የሚጠበቅ ይሆናል።
- የወላይታ ሕዝብ ከአጎራባች ሕዝቦች ጋር የሚኖረውን ለዘመናት የዘለቀው እንደነበረ የሚቀጥል እና የተሻለ የጋራ ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ ደረጃ ከፍ ወደ በሚልበት ሁኔታ ላይ በረዥም እና አጭር ጊዜ ዕቅድ አውጥቶ መከወን ያስፈልጋል። የበላይነት እና የበታችነት ፤ የመናናቅ እና የመከባበር ፤ የተማረ እና የሰለጠን እየተባለ በሕዝቦች ዘንድ የመደብ ልዩነት ለመፍጠር የሚደረጉ እና ሲደረጉ የነበሩ እንቅስቃሴዎች ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ሊቆሙ ይገባል። በሕዝቦች ዘንድ ጥል እና ጥላቻ የሚዘራ የትኛውም አካሄድ ተቀባይነት የሌለው እና የባዕድ ተንኮል መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል። የወላይታ ሕዝብ በራሱ ክልል ይደራጅ ተገንጥሎም ሐገር ይሁን ከጋሞ፣ ጎፋ፣ ዳውሮ፣ ከምባታ፣ ሲዳማ…ወዘተ ሕዝቦች ያለው የአስተዳደር ወሰን መጋራት እና ወንድማማችነት የሚቀጥል መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።
4.ድንግዝግዙ ነግቷል፤ መስመሮች በተሻለ ሁኔታ ጠርተዋል፤ ፓርቲ/ግለሰቦች ማን ምን አይነት ሚና ሲጫወት እንደነበረ ምን ሊጫወት እንደሚችል በተሻለ ሁኔታ ለማወቅ ተችሏል። ስለሆነም እስካሁን ከተፈፀሙ ሰህተቶች ትምህርት ወስደን እና በመታረም ትግሉን በተሻለ ሁኔታ ለማሳለጥ መልካም ዕድል መፍጠሩ ሊታወቅ ይገባል። የሲቪክ ተቋማት ፣ የተለያዩ አደረጃጀቶች እንዲሁም ግለሰቦች (ዲያስፖራን ጨምሮ) ከዚህ ቀደም እንደነበረው ሕዝብን የማንቀሳቀስ እና ትግሉን የማሻገር ስራ ውስጥ ተሳትፏቸውን ሊያጠናክሩ ይገባል።
- ሕዝቡ የሚያደርጋቸው ሰላማዊ እንቅስቃሴዎች በጎላ እንዲደመጡ ሊያደርጉ የሚያስችሉ ስልቶችን በመቀየስ በሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝቦች ዘንድ አዎንታዊ አረዳድ እንዲኖር ማድረግ ይገባል። ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄዎች ከመገንጠል ጋር ተያይዞ በአሀዳዊያኑ አድባር የሚወራው ስህተት እንደሆነ በማበከር ማስረዳት ይገባል። ወላይታ ክልል ስትሆን ሕዝብ ለሕዝብ ግኑኝነቶች ፤ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ትስስሮች ፤ የኢኮኖሚያዊ እድገቶች የተሻሉ እንደሚሆኑ መዘርዘር በሚያስፈልግበት መድረክ በዝርዝር መግለጥ ያስፈልጋል።
ክልላችን በትግላችን በእጃችን !
ዎላይታ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
Holozy 1896
Chozeh HaMedinah
Shenne minnin shempoyikka hayiqenna !