የፖለቲካ ዳተኝነት በወላይታ ሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የለዉም!!!
በአሰፋ ወዳጆ
ከኒኦሊቲክ ኤራ ጀምሮ በራሱ ጠንካራ ማዕከላዊ መንግስት ይተዳደር የነበረዉ የወላይታ ሕዝብ፣ ብረት አቅልጦ የሠራዉ ማርጮ የሚባል የጋራ መገበያያ የነበረዉ ታላቁ የወላይታ ሕዝብ፣እኤአ በ1894 ዓ/ም በአጼ ምኒሊክ ወታደራዊ የበላይነት ወደ ኢትዮጵያ ኤምፓዬር ለመቀላቀል የተገደደው የወላይታ ሕዝብ እስከ ዛሬ ድረስ የራሱን ዕድል በራሱ የመወሰን የፖለቲካ ነጻነት ተነፍጎ Stateless ሆኖ ለመቆየት ተገድዷል።
ይሁንና በአሁኑ ሰዓት ከስድስት ሚሊዮን ይበልጣል ተብሎ የሚታመነዉ የወላይታ ሕዝብ ይህንን intergenerational structural political domination and oppression በጫንቃው ተሸክሞ የመቆየት ትዕግስቱ ተሟጧል። በሌላ አነጋገር አዲሱ የወላይታ ትዉልድ ከimplicit structural political domination and subordination ሙሉ በሙሉ መላቀቅ እና በኢፌዴሪ ሕገመንግሥት አንቀጽ 39፣ እና 47 የተረጋገጠው የፖለቲካ መብትና ነጻነት እንዲረጋገጥለት አጥብቆ ይሻል።
በመሆኑም እዉነተኛ ሕብረብሔራዊ ፌዴራሊዝም ስርዓት እዉን አደርጋለሁ የሚል የተስፋ ቃል የገባው የጠ/ሚ አብይ አሕመድ መንግስት ከስድስት ሚሊዮን የሚበልጠዉ የወላይታ ሕዝብ በም/ቤቱ አማካኝነት ላቀረበዉ ሕገመንግስታዊ ጥያቄ ሕገመንግስታዊ ምላሽ ላለመስጠት የሚያደርገዉ የፖለቲካ ዳተኝነት በመላዉ ወላይታ ሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የለዉም። ስለሆነም መጪዉ ማክሰኞ በሚደረገዉ የፖለቲካ ዉይይት ጥያቄአችንን ከሕገመንግስታዊ ብሎም based on our ታሪካዊ፣ ፖለቲካዊ፣ማህበራዊ እና ዲሞግራፊክ landscape አንጻር በተናጠል ታይቶ ተገቢ ሕገመንግስታዊ ዉሳኔ እንዲሰጠን አበክረን እንጠይቃለን።
የወላይታ ሕዝብ የሚበጀውን ያውቃል፡፡
ወላይታ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት!!!