የወላይታ ሕዝብ ጥያቄ በመመለስ እንጂ በመቀልበስ በፍፁም አይጠናቀቅም!!
በወርቅነህ ገበዬሁ
ዶ/ር አቢይ አህመድ በተለይም የሲዳማ ሕዝብ የራሱን መብት በልጆቹ ትግል ግቡን ከመታ ብኋላ አይኑን ሕወሀት በ1980’ቹ መጨረሻ በደቡብ ሕዝቦች ላይ የተከተለውን አይነት ስትራቴጂ በተቀሩት ሕዝቦች ላይ በሃሳብ ደረጃ መሞከሩ ይታወቃል። ይሁን እንጂ ይህ በየጊዜው ተቀባይነት እንደሌለው ሕዝብ በመድረክ እና ሰልፍ መግለጡ የቅርብ ወቅት ክስተት ሆኖ አልፏል።
የዶ/ር አቢይ አስተዳደር ከክልልነት ጋር ተያይዞ ለተነሱ ጥያቄዎች የተከተላቸው ስልቶች ተስፋ እና ስጋቶች ፦
- የወላይታ ሕዝብ በሕጉ መስረት የጠየቀውን ጥያቄ በአመቱ ምላሽ ሊሰጠው ሲገባ በመቆየቱ ይህንን ተከትሎ በታህሳስ 10 2012 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ የተጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ አስቸኳይ ጊዜ አሳውጆ አካባቢውን በወታደራዊ አስተዳደር ስር በማድረግ የሕዝቡን ዴሞክራሲያዊ መብቱን ነፍጓል።
- ጥቂት pitty bourgeoisie እና enslaved ellites በመሰብሰብ የhostage politics በመጫወት ለጊዜውም ቢሆን ሕዝባዊ እንቅስቃሴው እንዲቀንስ እና እንዲቀዘቅዝ በማድረጉ በኩል ተሳካቶለታል። የወላይታ ተወላጆች ከዚህ ቀደም በሃገር ደረጃ ሊጫወቱ የሚችሉበትን ሚና ክልል ቢሆኑ ሊያጡ እንደሚችሉ እና ይህንንም ሕዝባዊ መሰረት በሌላቸው ፖለቲከኛ ግለስቦች ላይ በማስረፅ ቤቱን (በግልፅ ባይሆንም) ለሁለት በመክፈል በኩል ተሳክቶለታል።
- የወላይታ ሕዝብ ጥያቄ በከፍተኛ ሁኔታ በመፋፋሙ እና ወደ ማይቀለበስበት ደረጃ መድረሱን ተከትሎ ከወላይታ ውጭ ላሉ ሕዝቦች Unprecedented Bonanza አምጥቶላቸዋል። ተደፍጥጠው የቆዩ የማንነት ጥያቄዎች የመሰማት ዕድላቸው ከፍ ብሏል ፤ ከወላይታ በኩል በማዕከላዊ መንግስት ላይ የደረስው ጫና አጎራባች ህዝቦች ለተሻለ ተጠቃሚነት በሚል በርካታ ትኩረት እየተሰጣቸውም ነው። ይህም የእንቅስቃሴው አንዱ ውጤት ነው።
- የወላይታ ሕዝብ በጠየቀው ጥያቄን በማጣመም ከአጎራባች ወንድም ሕዝቦች ጋር ጠላትነት የማቃባት ስራ በከፍተኛ ሁኔታ የታየበት ነው። የወላይታ ሕዝብ ጥያቄ አስተዳደራዊ እና የተሻለ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንጂ በጥላቻ የመሸሸ/የመኮብለል ተደርጎ መወሰዱ አንዱ ያስተዋልነው አሉታዊ ውጤት ነው። ይህን መረዳት የሚችል አዕምሮ ያስፈልጋል። ወላይታ፣ጋሞ፣ጎፋ፣ዳውሮ፣ ኮንታ …ወዘተ ጋር ያለው ጉርብትና ወንድማማችነት እንደነበረ የሚቀጥል ይሆናል። በተቀያያሪ ፖሊቲካ ጥላቻን መዝራት የዚሁ አሉታዊ ውጤት ነው።
- ሕዝባዊ ጥያቄ እንዳይመለስ ለማድረግ ‘የአገሬውን ሰርዶ…” አይነት ተረት ተከትሎ በርካቶችን በመርህ እና በሕገ መንግስቱ አንቀፆች ሳይሆን የግል ስብዕናውን እንዲያምኑ በማድረግ የማንሸራተት ስራ “በአገሬው በሬ” ሰርቷል። የOld Guards ክንፍ ይህን ስራ በመስራት ትግሉን እና ታጋዮችን ሊያሰናክል ሙከራ በማድርግ ተንቀሳቅሷል።
እነዚህ ከበርካቶች ጥቂቶች ቢሆንም ዶ/ር አቢይ ከአሁን ብኋላ በ1992 ዓ.ም እንደነበረው ሕዝባዊ ትቃውሞ ተከትሎ የወቅቱ ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ የወሰደው አይነት የተሳሳተ እርምጃ ይወስዳል ብዬ አልጠብቅም። ከወሰደም እጅግ የተሳሳተ እና ወላይታን እና ወላይታዊያንን ወደ ሌላ የትግል ምዕራፍ መሸጋገሪያ ድልድይ የሚሆን ይሆናል። የወላይታ ሕዝብ ጥያቄ በመመለስ እንጂ በመቀልበስ በፍፁም አይጠናቀቅም።
የወላይታ ሕዝብ ትግል እስከ ነፃነት!!
Holozy 1896
Chozeh HaMedinah
Shenne minnin shempoyikka hayiqenna!