ተለማምጠንና ለምነን ያስከበርነው መብት በታሪካችን የለም!!!
በብስራት ኤልያስ (ዶ/ር)
እኩልነት፣ ፍትህና ነጻነት ትግላችን ወደ ፍሬ የሚደርሰው ልክ እንደትናንቱ ተገፍተን ተፈናቅለን ተሰድደን በፖለቲከኞች በግፍ ተገድለን ፍትህ ስናጣ ትናንት በቁጭት እንደተነሳነው ሁሉ ነገውንም በሚሆነው ሁሉ በቁጭትና በአላማ መርህ ትኩረት ሰጥተን በጋራ ልንመክተው ይገባል።
አንዳንድ በማህበራዊ ሚዲያ የሚቃጡትን ገደብ የለሽ ጥላቻ መርጨትና ማስፈራሪያዎችን በየዋህነት ልንመለከተው አይገባም። ከዚህ በፊትም በተመሳሳይ ሁኔታ መኖሩን እናስታውሳለን። ማስፈራሪያ ከተራ ግለሰብ ጀምሮ መንግስታዊ ሰንሰለትም ሊኖር ስለሚችል በብልሃት ፣ በጥበብና በጥንቃቄ ልንመለከተው ይገባል።
ትግላችን ወቅቱን ጠብቆ በጠንካራ መሠረት ላይ ቆሞ ከመሄድ ውጪ በሚነፍሰው ነፋስ ሁሉ መወናበድ ሳይገባ በጥንቃቄ የነጻነት ትግላችንን ማድረግ ውጤቱንም መዝነን ለክተን እስኪንቋጭ ድረስ አላስፈላጊ ንትርክ አያስፈልግም። #መገፋት የማታ ማታ ያደርሳል ወደ ደህና ቦታ; እንደሚባለው መገፋት በሙሉ ኃይል ወደ ትግል ያነሳሳን ሲሆን ይህ ትግላችን ጣፋጭ ፍሬ እንዲያፈራ የህዝባችን ፖለቲካዊ ትግልና ንቃተ ሕሊና በምንም መልኩ ልሸረሸር በፍጹም አይገባም። ታግለን እንጂ ተለማምጠንና ለምነን ያስከበርንበት መብት በታርካችን የለም።
የወላይታን ህዝብ ከአጎራባች ህዝቦች ጋር ጥላቻ በመዝራት ለማጋጨት ብለው ብለው አልሳካ ያላቸው ድኩማን የደኢህዴን ካድሬዎችና ራሳቸውን ያላወቁ #አክቲቪስት; መሳይ የጨቅላዎችን የጥላቻ አጀንዳዎች ተመሳሳይ የጥላቻ መልስ መስጠት ጠቃሚ አይደለም፤ እናስተውል። ወላይታ የራሱ ስነ ልቦና ያለው ሕዝብ ነው። ደቡባዊ ማንነት አቀንቃኞች አሁን ወደ መጨረሻ የተከበሩ ብሔሮች መካከል የስድብና የጥላቻ መርዝ እየዘሩ ናቸው፤ ወላይታ ህግን ያከብራል። ህገ መንግስታዊ ራሱን በራሱ ለማስተዳደር በክልል የመደራጀት መብት ጠይቆ ህገ መንግስታዊ ምላሽ በመጠባበቅ ላይ የሚገኝና እውን ይሆናል ብሎ መጠበቁ ለድኩማን ካድሬዎች ራስ ምታት ሆኖባቸዋል።
የሆድ አደር ካድሬዎች በሀሳብ የመሟገት አቅም ሲያንስ፣ በእውነት የማሸነፍ መንገድ ሲጠፋ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ተሟጓቾችን ማሳደድ፣ ፖለቲካዊ ምህዳር ማጥበብ የአምባገነንነትና የመሽነፍ መገለጫ ነው።
በህዝባዊ ትግል ወደ ወላይታ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፡፡
ጉዟችን ወደ ፊት!!!
ወላይታ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት!!!