የኢትዮጵያዊነት መገለጫ መታወቂያ ሰጪና ተቀባይ የለም!!!
በአወል አለማየሁ ዳና
እኔም በግለሰብ ደረጃ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ብሔሮችና ብሔረሰቦች ሁሉም በቁጥራቸውና በያዙት መልካምድር ሳይወሰኑ ሰው በመሆናቸው ብቻ ዕኩልነታቸውና ፍትሓዊ ተጠቃሚነታቸው ተረጋግጦላቸው የሚኖርባትን ኢትዮጵያን ማዬት ነው ሕልሜ፡፡ ለዚሁም ዓይነተኛው መፍትሄ ፌደራል ሥርዓት እንደሆነ አምናለው። የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ሕገመንግስት በአንቀጽ 46 ይህን የሕዝብ ፍላጎት ይፈቅዳል።
ስለሆነም በሀገራችን ከታወቂ ፖለትከኞች አንዱ ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና እንዳሉት አንዱ ብሔር/ብሔረሰብ የኢትዮጵያዊነት መገለጫ መታወቂያ ሰጪ ሌላው ተቀባይ ሳይሆን ሁሉም በብሔሮች/ብሔረሰቦች በማንነታቸው ሳይሸማቀቁ የበላይና የበታች የሚባልም ሳይኖር በዕኩልነት የሚታዩበት ኢትዮጵያዊነት እውን እንድሆን ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ትግል ያስፈልጋል። ለእኔ የብሔር/ብሔረሰብ ማንነትና ኢትዮጵያዊነት የአንድ ሳምንቲም ሁለት ገጽታዎች (የድሮ…አሁን ሳንትም የለም መሰለኝ) ወይንም የአንድ ሰው ሆድና ጀርባ (አንዱ ከጎደለ ሰው መሉ ስለማይሆን ማለቴ ነው) ናቸው፤ ካልሆነ ዋጋ የለም፡፡
የዎላይታ ሕዝብ የክልልነት ጥያቄ የሁለት ትውልዶች (since the maximum life expectancy of Ethiopians is 64 years) ጥያቄ ነው። ለ3ኛ ትዉልድ ማለፍ ያለበት ጥያቄ ነው ብዬ አላምንም፤ የልጆቻችን ጥያቄ ባይሆን ብዬ አሰብኩት።
አሁን ከመንግስት እያቀረበ ያለው አማራጭ በግልጽ ለዎላይታ ሕዝብ ቀርቦ ሕዝቡ በአብላጫ ድምፅ የሚያጸድቅ ከሆነ የተፈራው አይቀርምና የዎላይታ ሕዝብ የክልልነት ጥያቄ በዲሞክራሲያዊ አካሄድ ለ3ኛ ትውልዶች ጥያቄ መሆኑ አይቀርም። ነገር ግን ከሕዝብ ፍላጎት ውጪ በመንግስት ፍላጎት ብቻ በሀይል ለመጫንና ለማስፈጸም የሚደረግ ማንኛውን ውሳኔ በግሌ እቃወማለሁ።
ለማንኛውም ዲሞክራሲ ማለት በአብላጫ ሕዝብ ፍላጎት የመገዛት ባህል ስለሆነ የአብዘኛው የዚህ ትውልድ የዎላይታ ሕዝብ ውሳኔ እስከምታወቅ ድረስ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ትግል ብቻ ይዞ መቀጠል አማራጭ የሌለውና የመጨረሻ መፍትሄ መሆኑን ለማሳሰብ እውዳለሁ። ወላይታነቴን የማይቀበልና የማያከብር ኢትዮጽያዊነት ምኔ ነው? የዛሬ ጽሑፍ መደምደምያ ነ፤ ከዚህ ውጪ የዜግነት ፖለትካ የለም። ይህንን ለኢዜማ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት አድርሱልኝ። የዎላይታ ሕዝብ የክልልነት ጥያቄ በሕገመንግሥታዊ ሥርዓት የማይመልስ ከሆነ ብልጽግና ፓርቲ ከዚህ ወቀሳ ነፃ ስለማይሆን ዳግም ቢያስብበት ይሻላል። ሰላማዊና
ዲሞክራሲያዊ ትግል ለሕዝቦች ሰላምና ለኢትዮጵያ አንድነት፤ሰላም ለሁላችን፡፡
እግዚአብሔር ከ COVID-19 ያሻግረን!!!
ከአዘጋጁ፡– ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እየገለፅን በኢሜይልና ፌስቡክ አድራሻቸው ማግኘት ይችላሉ፡፡