የሕዝብ ምጥ
በመ/አ ጳውሎስ ቦጋለ ዋሌሎ
ይህችን አርእስት እወዳታለሁ።ከዚህ በፊት በኢትዮ ሚዲያ በዚች አርእስት ሠፋ ያለ ጽሑፍ አቅርቤ ነበር ።እንደገና ያችኑ አርእስት በመጠቀም ልክ የዛሬ ሁለት ዓመት አቅርቤ የነበረውን ያኔ ያላነበባችሁ ዛሬ እንድታነቡ አቅርቤአታለሁ።
በ2016 በዚህ ረዕስ ሰፋ ያለ ጽሑፍ በኢትዮ ሚድያ አቅርቤ ነበረ።ዛሬ የአገራችን ፖለቲካ የደረሰበትን አዙሪት ስመለከት በዚይው ረዕስ ይህችን የዤ ለመቅረብ ተገደድኩ።የአንድ አገር ሕዝብ የእርሱ የሆነው የፖለቲካ ሥልጣኑ በጠብ መንጃ አፈሙዝ ተዘርፎ ሲገደል፣ሲገረፍ፣ሲታሰር፣እና ሲዋረድ አሁንስ በቃኝ ከረፋኝ ብሎ ይነሳል።
እዚያ ደረጃ ለመድረስ የተፈጥሮ ሕግ ባይሆንም ሕዝብ እምቢተኝነትን እንደማንኛውም ፍጡር ይጸንሳል።ያ የሕዝብ ጽንስ ግዜውን ጠብቆ ይወለዳል ካልቀና ይጨናገፋል።በሠላም የመገላገሉ ደረጃ ለመድረሰ ብዙ የሕይወት መስዋዕት ተከፍሏል።ያን ያህል መስዋዕት የተከፈለበት ሲጨናገፍ እንደገና መጸነስ አዙሪት ይመለሳል።
ከኢጣሊያን በኋላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህ የፀነሰው በተደጋጋሚ ተጨናግፎበታል።በ1953 ዓም የእነ መንግሥቱ ነዋይ ተጨናገፈ።በ1966 የተፀነሰው በደርግ በጠብ በመንጃ በመቀማቱ ተጨናገፈ።በ1983 የሕዝቡ ጽንስ በወያኔ አፈሙዝ ተጨናገፈ።
ይኸው ዛሬ ወያኔን ከሥር ከመሠረቱ ለመገንደስ የተከፈለበት የልጆች ደም ተረስቶ በሽግሽግ ተጨናገፈ።
የፓለቲካ ሥልጣን የሕዝብ የትገል ውጤት በመሆኑ ባለቤቱ እረሱ ነው። የዲሞክራሲ ምንነት ዲስኩር ሳይሆን የሕዝቡ ጥያቄ እኔ የሚታዘዘኝን ልሹም ልሻር ነው።የሚገድለኝን በማሸጋሸግ ሳይሆን ከሥር ከመሠረቱ ገንድሼ የማዘውን የመሾም መብቴን አትቀሙኝ እያለ ነው።ጥያቄው ካልተከበረ አገሪቱ እና ሕዝቧ ከማርገዝ ከመጨናገፍ አዙሪት አይወጡም።ታሪክም እራሱን ይደግማል።” አልሞትኩም ብዬ አልዋሽም”
ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እየገለፅን በኢሜይልና ፌስቡክ አድራሻቸው ማግኘት ይችላሉ፡፡
እባክህን የራስን የቤት ሥራ ሥራ! የእኛ ለእኛ ተው!!!
በአሰፋ አየለ
እንደምታወቀው አፈናዊ አገዛዝን የሚከተል የቀድሞ ደቡብ ክልል መንግስት የክልሉን ብሔሮችን እኩል የመልማትን መብት በመጋፈጥ ለሲዳማ ብቻ የተለየ የመልማት መብት በመስጠት ለሎችን ዞኖችን እንደ እንጀራ ልጅ በመቁጠሩ መነሳ ራሱ ሲዳማ ህዝብም ይሁን ወላይታ ጋሞ ዳውሮ ኮንታ ጎፋ እና ሌሎችም በክልሉ ውስጥ የነበሩት ዞኖች ባነሱት የተቃውሞ ድምጽ እና ራስን በራስ የማስተዳደር የክልል ክልል ጥያቀ በማንሳታችን ይህ አምባገነኑ ክልል ፈርሶ ይሄው በአድስ ለመዋቀር ሁሉ ነገር አልቆ መዋቅሩ ወደ መሬት መውረዱ ብቻ ቀርቷል።
በዚህ ሂደት መነሻ ከሁሉም ዞኖች በተለየ የወላይታ ዞን በምንም ምክንያት መንግስት አስጠንቶ ያመጣውን 1 ለ 55 የሚለውን መሪህ ባለመቀበልና የራሱን ክልል የመሆን ጥያቀውን ተጠናክሮ የመቀጠሉ ምክንያት ለሌሎችም አጎራባች ለዳውሮና ጋሞ ዞኖች ምቹ ሁኔታ ፈጥሮላቹ እናንተም በየዞን ምክር ቤቶች አስወስኖ ክልል ጥያቀው ተቀላቅለዋል። ይሁን እንጅ መንግስት ጥያቅያቸውን ባለመቀበል ያስቀመጠውንና የወላይታም ህዝብ የማይቀበለውን የማዕከል ወረን መነሻ በማድረግ አንዳንድ ጽንፈኖች ብሔርን ከብሔር ጋር ለማጋጨት ፈጽሞ ውሸት የሆነውን አጀንዳ በሶሻል ሚድያ እያራገቡ ይታያሉ።
አንድ እውነታ ባወራ እናንተ የጋሞም ሁነ የዳውሮ አክቲቪስቶች ምንም ለህዝባቹ አዝናቹ ሳይሆን ማወቅ ስገባቹ ያልተረዳቹት እውነታ ብኖር የወላይታ የጋሞ እና የዳውሮ ህዝቦች እናንተና እኔ ወደዝህ ምድር ከመምጣታችን አስቀድሞ ወንድማማቾች የነበሩ ለጋራ ትግል ለጋራ ነጻነት ለጋራ እድገት የጋራ የሆነውን ጠላታቸውን ምንም ልዩነት ሳይኖር ከመታገላቸው አልፎ ወላይታ በውጭ ጠላት ስወረር ጋሞና ዳውሮ ;ጋሞ በጠላት ስወረር ወላይታና ዳውሮ ; እንደዛውም ዳውሮ በውጭ ጠላት ስወረር ወላይታና ጋሞ አብሮ ከጎኑ ተሰልፎ የአንዳቸው ጠላት የሁሉ ጠላት በማድረግ በጋራ አንዱ በሌላኛው ጎን ቆሞ ተዋግቶ የሁላችንንም አሁን የምንጨፍርባቸውን ዳውሮ ወላይታ እና ጋሞ እያልን ከፋፍለን የሚንኖርባትን አከባቢያችንን ማቆየታቸውን አሁን የጋራ አንድነታችንንና የወንድማማችነት ፍቅራችንን የሚትጠሉ እናንተ ትክክለኛ ዳውሮ አልያም ጋሞ ተወላጆች ሳትሆኑ የነፍጠኛ ተወላጆች በመሆናቹ አታውቁምና በየአከባቢያችሁ ያሉትን አባቶችን ብትጠይቋችሁ ልክ አባተ የነገረኝን ያስረዳቿል። የሆነው ሆኖ ግን እኛ አንድ ሆነን እያለን ክልል ወይም ማዕከል ሆንክ አልሆንክ ዋናውንና አንኳሩን የብሔሮችን አንድነትና ፍቅራቸውን በመዘንጋት ዛሬ አንዱን ለሌላኛው ጠላት በማስመሰል የሀሰት ወረ ይዛችሁ መሮጣቹን ልታቆሙ ይገባችኋል።
እኛ ወላይታወች በእኛ መሪዎቻችን አመጽ የሚያስነሳንም ይሁን ልጆቻችን የበደሉን አንዳች ነገር የለም እንጅ ብኖር እንኳን የየራሳቹን የቤት ሥራቹን ትታቹ በማያስጨንቃችሁ በወላይታ ጉዳይ የሚትጨነቁና ቀንና ለሊት በፌክ አካውንት የሚትፖስቱት እውነት ለእኛ አዝናችሁ ነው? ወይስ አንዱን ከሌላው ጋር ለማጋጨት ፈልጋቹ እንደሆነ ለማንም ግልጽ ነው።
ስለዚህ እኛ እንደሆንን የጠየቅነውም ለብቻችን ክልል እንጅ ማዕከል አይደለም አሁንም የምንወስደው ለብቻችን ክልል እንጅ ፈጽሞ ማዕከል እንዳይደለ ተረድታቹ እባካቹን የእኛንና የአመራሮቻችንን ጉዳይ የራሳችን የውስጥ ጉዳይ በመሆኑ ተውንና በራሳቹ ጉዳይ ተጠመዱ ከእንግድህ ወላይታ በየትኛውም ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ግንኙነቶች የእናንተን እድገትን እንጅ ውድቀታቹን እንደማይፈልግና እንደማይመኝ አውቃቹ አርፋቹ እንድትቀመጡ እላለሁ።
ዛሬም ነገም እስከ ወድያውም ወላይታ ክልል እንጅ ማዕከል መሆንን አልጠየቀም፤ አይፈልግም፤ ደግሞም ክልል ይሆናል።
ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እየገለፅን በኢሜይልና ፌስቡክ አድራሻቸው ማግኘት ይችላሉ፡፡