ሕወሃት ሲያደርግ አልነበረም? የሚል ኢ-አመክንዮአዊ

Wolaita Today

በአሰፋ ወዳጆ

ሕወሃት ሲያደርግ አልነበረም? የሚል ኢ-አመክንዮአዊ / politically poor/Zero Summpolitical game. በዘመነ ብልጽግና ሕገመንግሥት እየተጣሰ ነዉ። ሕወሃት ሕገመንግስቱን ይጥስ አልነበረም? በዘመነ ብልጽግና ሕብረብሔራዊ ፌዴራል ስርዓቱ አደጋ ዉስጥ ገብቷል። በዘመነ ሕወሐት ሕብረ ብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓቱ ጤናማ ነበር ወይ? ደቡብ በሚባል አሐዳዊ/Ethnic melting pot ከተጠፈሩ 56-1 ብሔሮች ጥቂቶች የራሳቸውን ዕድል በራሳቸዉ የመወሰን፣ የራሳቸዉን ክልል የመመስረት ሕገመንግስታዊና ታሪካዊ የፖለቲካ ነጻነት ጥያቄ እያነሱ ነዉ። ጥያቄያቸው በዘመነ ሕወሃት አያነሱም ነበር እንዴ? ምነው በአብይ ብልፅግና ዘመን? የወላይታ ሕዝብ የራሱን ዕድል በራስ የመወሰን inviolable and inalienable የፖለቲካ ነጻነት፣የራሱን Regional State የመመስረት ጥያቄ ጭምር የብልጽግና መንግስት ኢ-መደበኛ፣ኢ-ሕገመንግስታዊ ወታደራዊ ኮማንድፖስት አስተዳደር ዘርግቶ እያፈነ መሆኑን እንቃወማለን።ምነው ሕወሐት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ ሲያደርግ አልነበረም?

በዘመነ ብልጽግና ብሔርን መሠረት ያደረጉ የሰብኣዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶች፣ሰላማዊ ዜጎች በማንነታቸዉ ምክንያት በግፍ ተገድለዋል፣ የአካልና ስነልቦና ጉዳት ደርሶባቸዋል፣ ተዘርፈዋል፣ ከቄያቸው ተፈናቅለዋል።በዘመነ ወያኔ ተመሣሣይ ድርጊቶች ይፈጸሙ አልነበረም ወይ? የብልጽግና መንግስት ያሰማራቸው የመከላከያና ጸጥታ ኃይላት የሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ጥሰት እየፈጸሙ ይገኛሉ። በዘመነ ሕወሓት ከተፈጸመዉ አይበልጥም። የአብይ-ብልጽግና የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን እያሰረ፣እያዋከበ ነዉ፦ በዘመነ-ሕወሓት የነበረዉን አፈናና የፖለቲካ ምህዳር ጥበት አዳሜ ዘንግታለች። PP dominated የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ለብልጽግና ፓርቲ እየወገነ ነዉ። የሕወሓት -መራሹ ፓርላማስ ምን ያደርግ ነበር? ወዘተረፈ።

በዘመነ ሕወሓት -ኢሕአዴግ የነበረዉ አምባገንነት፣የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶች፣ ሙስና፣ ወዘተረፈ እንደምናወግዝ ሁሉ በዘመነ ብልጽግና የሚፈጸም አምባገንነት፣ የመብት ጥሰት፣ ሙስና ወዘተረፈ ልናወግዝ ይገባናል፣ በዘመነ አብይ-ብልጽግና ዘመን እየተፈጸመ ያለዉን አምባገንነት፣ የመብቶች ጥሰት፣ ሙስና ለመሸፋፈን/ለማድበስበስ በዘመነ ሕወሓት-ኢሕአዴግ ስለነበረዉ maladministration, poor political governance, የመብቶች ጥሰት፣ ሙስና ወዘተረፈ አጋንኖ ማዉራት በማንኛውም መስፈርት ተቀባይነት የሌለዉ የፖለቲካ ስካር ነዉ። ሕወሓት መራሹ መንግስት የፈጸማቸው ስህተቶች/በደሎችን መልሶ መላልሶ በማዉራት የአብይ ብልጽግና መንግስት የሚፈጽማቸዉን ስህተቶች/በደሎች ሌጅትማይዝ /sanctify ማድረግ ፈጽሞ አይቻልም። በአጠቃላይ are we (Ethiopians) under political change or political stagnation?Is Ethiopia evolving or devolving?

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እየገለፅን በኢሜይልና ፌስቡክ አድራሻቸው ማግኘት ይችላሉ፡፡