ወላይታ የማንም የባለ ጊዜ መጠቀሚያ መሆኑ በኛ ይብቃ!!!

Wolaita Today

ብስራት ኤልያስ(ዶ/ር)

August 06, 2020

መንግሥት ህግ የማስከበር አቅም ስያጣ ወይም ስውር የወንጀለኛ አጋርነቱን በሽማግሌ የሃይማኖት አባትና ቤተ እምነቶችን በመጠቀም እርቅ እርቅ እያለ ስዘላብድ የዎላይታ ብሔር ጥቃትና ፍትህን እያዳፈነ ማለፉ ከ2010 ሰኔ ወር ጀምሮ የነበረው የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው።

የወንድሞቻችንን ሞት በእርቅ ሰበብ ፍትህ ተዳፍኖ ወንጀለኞች የአማራጭ ስልጣን ተበርክቶላቸዋል። የተቻለውን ያህል የማፈናቀልና ሞራላዊ ጥቃት በመዋቅር ተደግፎ ተፈጽሟል። ገሎ አስገድሎ ሲያበቃ እርቅ እርቅ ይቅርታ እየተባለ ያልተጻፈ ፍልስፍና በማውራት በእርቅ እያሳበበ ወንጀለኛን ነጻ ስለቀቅ ከርሟል።

አሁን ደግሞ ለውጥ ስም ይዞ ብቅ ያሉት አሮግቶች ማርሽን ቀይሮ ከትልቅ ደቡብ ትንሹን ደቡብ በመፍጠር እንንፈላሰስ ባዮች ለፖለቲካ አላማቸው በዎላይታና አጎራባች ህዝቦችን የማጣላትና ቀጠናው የፀጥታ ችግር ለማድረግ በርካታ የቃላትና የስድብ ሙከራዎች በመፈብረክ ብሎም በሰፊው ህዝብ አስተዋይነት በመክሸፉ የፈጠራ እርቅና የሰላም ኮንፌራንስ ድራማ ላይ ተወጥሯል።

የወከለውን የህዝብ ጥያቄ ከማክበር ይልቅ የህዝብ ክብርና ልዕልና በመሸጥ ስልጣን ላግኝ የሚል በደም የሚጫወት ሞራል የወደቀ ትውልድ በአገርቱ ላይ የነገሰበት ጊዜ ላይ መገኘታችን ያማል።

ሰፊው የዎላይታ ህዝብ ህገ መንግስታዊ ራስን በራስ ማስተዳደር ጥያቄን ለማዳፈን የሰላም ችግር በሌለበት ህዝቦች መካከል በመሠረተ ብስ እርቅና የሰላም ኮንፌረንስ የመፍጠር አካሄድ ተቀባይነት የለውም። የማታለያ አካሄድ አቁሙና የቤት ሥራችሁን በህግና በእውነት አድርጉት። ሽማግሌ፣ እርቅና ቤተእምነት ሰዎች እያላችሁ ህዝብን ከሚታስጨርሱት መንግስትም አያጭበረብር በህግ ይስራ አያስመስል። በህግ ይዳኝ። ህግ የማይገዛበት ህግ በእኩልነት የማይዳኝባት ኢትዮጵያን፣ በማንነት የሚሸማቀቅበት የሌላውን ማንነት ተሸካሚ የመፍጠር አባዜያችሁን አቁሙ።

ወላይታ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት!!!