የተላለፈ አድስ አመት መግለጫ እንኳን በሰላም አደረሰን።

Wolaita Today

ከዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ዎሕዴግ/

የተላለፈ አድስ አመት መግለጫ እንኳን በሰላም አደረሰን።

ጳጉሜን 05 2012ዓ.ም

የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ብሔር ብሐረሰቦችና ሕዝቦች እንኳን ለ2013 አ.ም በሰላም አደረሳችሁ።

ዎሕዴግ መልካም አድስ አመት ለሁሉም እየተመኘ፥ ዎሕዴግ የሚታገልለት ስልጡንና ጨዋ ለዎላይታ ህዝብ ባለፈው በ2012 አ.ም ተስፋ ባለመቁረጥ በአንድነት መንፈስ ህገ መንግስታዊ የክልል መዋቅር ጥያቄ ባደረገው ሰላማዊ ትግል አድናቆት ወደር የለውም።

የዎላይታ ህዝብ የደም መስዋዕትነት እስከመክፈል እየሞተ በሰላማዊ መንገድ እየታገለ ሌሎች ብሔሮችን ሳይነካ፣  የሰውና የመንግስት ንብረት ሳይነካ የአመራሮች ጥያቄ ነው ላሉት እውነቱ የሕዝብ ጥያቄ መሆኑን አጉልቶ ላሳየው ለታላቁ የዎላይታ ሕዝብ ምስጋናችን የላቀ ነው።

የክልል ጥያቄያችን በሚገባ ሰላማዊና ሕዝባዊ መሠረት እንዲኖር ያላሰለሰ ጥረት ያደረጉት፥ በውጭ እና ሀገር ውስጥ ያሉ የዎላይታ መብት ታጋዬች ፣ የፓለቲካ ፖርቲዎች ሚና ፣ የዎላይታ ዲያስፖራ ያደረገውን ንቅናቄ ወዘተ የሚደነቅ ነው።

ነገር ግን፦

በሰላማዊ መደበኛ ሥራና አገልግሎት ላይ በነበሩት የወላይታ ዞን አመራር ከማህበረሰብ ተወካዮች ጋር በነሐሰ 3 2012 አ.ም በጉተራ አደራሽ በስብሰባ እያሉ በተፈጸመው መንግስታዊ ሽብርና አላስፈላጊ የኃይል እርምጃ ጋር በተያያዘ 36 የንጹሃን ሞትና ከ150 በላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ሃላፊነት የሚወስድ አካል እስካሁን አለመኖር፣ ለቤተሰቦቻቸው የሚደረግ ካሳ ጉዳይ

ምንም አለመባል፣ የዎላይታ ክልል ጉዳይ በመወያየት ላይ በነበሩት የህዝብ ልጆች ላይ የውሸት ክስ አለመቋረጥ ፣ በየጊዜው ያለወንጀል በኮማንድ ፖስት እየተያዙ የሚታሰሩ የክልል ተሟጋች የላጋዎች ለዚህ ሁሉ ምክንያት የሆነው የክልል ጥያቄ ከተለመደው ማታለያ ውጪ ምንም ተጨባጭ መልስ አልተሰጠም።

ስለሆነም፦

  1. መንግስት በአድሱ አመት ራሱን በራሱ ለማስተዳደር እንደ ህዝብ ይህ ሁሉ መስዋእትነት የከፈለ የዎላይታ ህዝብ የሚፈልገው ዎላይታ ክልል አደረጃጀት እንደተባለው ባጠረ ጊዜ መፍትሔ በመስጠት መዋቅራዊ ችግር እንዲፈታ እንጠይቃለን።
  2. ሁሉም የዎላይታ ህዝብ በአንድ መንፈስ የመዋቅር ጥያቄ፣ የልጆቻችን ፍትህ ጉዳይ፣ ለሞቱት የካሳ ጉዳይ፣ የተወካዮቻችን የውሸት ክስ ማሰረዝ ጉዳይ ተጠናክረን እንዲንሟገትና የተለመደው ዎላይታዊ አንድነት እንዳይለየን ዎሕዴግ ይጠይቃል።

መልካም አዲስ አመት

ጳጉሜ 5 2012