ከዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ዎሕዴግ) የተሰጠ የአቋም መግለጫ
ዎላይታ ህዝብ በርካታ አመታት ራስን በራስ የማስተዳደር ህገ መንግስታዊ መብት ተነፍጎ በደቡብ አቅጣጫ ክልል ጭቆና መዋቅር ውስጥ በመተዳደር በርካታ ፖለቲካዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚዊ በደል ቀማሽ መሆኑ እሙን ነው። ይህንን የመዋቅር በደል የተመለከተው የተለያዩ ህዝባዊ ተቋማት፣ ምሁራን፣ የላጋዎችና ተፎካካሪ የዎላይታ ፓርቲዎች ያላሰለሰ ትግልና ግፍት መነሻ ምክንያት የዎላይታ ዞን ምክር ቤት ህዝባዊ ግፍቱን መቋቋም ስላልቻለ ከቀበሌ ጀምሮ ባሉት መዋቅር ህዝቡን አወያይቶ ባገኘው ውጤት በብሔሩ ምክር ቤት በሙሉ ድምጽ
አስወስኖ በቀን 10/04/2011 ዓ.ም ለክልል ምክር ቤትድምጸ ውሳኔ እንዲደራጅ ደብዳቤ መጻፉ ይታወሳል።
የክልል መዋቅር ጥያቄ አስመልክቶ በቀን 09/11/11 ዓ.ም አለምን ያስደነቀው ሰላማዊ ሰልፍ የክልል ጥያቄውን ህዝባዊ መሠረት እንዳለው ሰላማዊ ህዝባዊ ሰልፍ የተደረገ ብሆንም የደቡብ ክልል ምክር ቤት የክልል ጥያቄውን ለድምጸ ውሳኔ ለማደራጀት በአንድ አመት ሙሉ
እምብተኝነት ስላሳዬ ይግባኝ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ተጠይቆ መልስ እየተጠበቀ ይገኛል።
ነገር ግን የደቡብ ክልል አሁን ባለው ሁኔታ እየፈረስ ስለሆነና የክልል ምክር ቤቱም ውክልናቸውን የለቀቁ ስለሆነ ዞኑ ህጋዊ ክልልነቱ እስኪረጋገጥ እንደ ክልል በህጋዊ መንገድ ህዝቡን ያስተዳድራል ብለን እናምናለን።
ይህንን አስመልክቶ የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ 39 የዎላይታ ምክር ቤት ተመራጮች የህዝብ ጥያቄውን አጀንዳ ለማስያዝ እምብተኝነትን ላሳየው ምክር ቤትን ራሳቸውን ማግለላቸውን የዘገየ ውሳኔ ብሆንም ዎሕዴግ በበጎ የሚመለከት መሆኑን እንገልጻለን። በተጨማርም የዎላይታ ዞን ም/ቤት 4ኛ ዙር 7ኛ የሥራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤ መርሀ ግብር ላይ ምክር ቤቱ የወሰናቸው ባለ ሰባት አጀንዳዎችንና የተላለፉ ውሳኔዎች ዎሕዴግ ይደግፈዋል።
ስለሆነም:-
1. የዎላይታ ህዝብ የክልልና የፌዴራል ሥራ አስፈጻሚዎችና በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዎላይታ ተመራጮችም ተመሳሳይ ህዝባዊ አቋም እንዲታሳዩን እንጠይቃለን።
- የማዕከላዊመንግስትናየፌዴረሽንምክርቤት በአስቸኳይየዎላይታንየክልልጥያቄበህገመንግስት መርህበአስቸኳይበመመለስናየክልሉንበጀቱንቀመር መድቦህጋዊእንዲያደርጉልንበአክብሮትእንጠይቃለን። ይሁንእንጂይህየማይሆንከሆነናበዚህምክንያት
ለሚፈጠረው የትኛውም ችግር መንግስት ኃላፊነት ይወስዳል። - በዎላይታየክልልመንግስትምስረታእናክልላዊ አስተዳደራዊመዋቀርዝርጋታለሚቋቋመውየሴክርታሪያት ጽ/ቤትየህዝብውክልናያላቸውሲብክድርጅቶችና አካላትእንዲሁምየዎላይታተፎካካሪፓርቲዎችንያማከለ ውክልናናእውቅናሊኖራቸውየሚገባውሚናናምን
በአደረጃጀቱ ልኖር እንደሚገባ፣ የህዝቡ ሚና በግልጽ ሊሰመርበት እና ሁሉም ባለቤትነት እና ኃላፊነት የመምራት የመቆጣጠር እና ውጤቱንም የማሳካት አደራውን ለመወጣት እንዲዘጋጅ እንጠይቃለን። - ህዝባዊትግሉበድልእስኪቋጭናየክልልህጋዊ እውቅናእስኪናገኝድረስሁሉምየመብትታጋዮች ሰላማዊትግላችንእንዲቀጥልእንጠይቃለን።ሰላማዊየነጻነትትግላችንንበድልይቋጫል።
ድልና ድምቀት ለዎላይታ ሕዝብ አንድነትና ዕድገት ለኢትዮጵያ፡፡
ዎሕዴግ
ዎላይታ ሶዶ
ሰኔ 20 2012 ዓ.ም