ከዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ዎሕዴግ) የተሰጠ የአቋም መግለጫ

የዎላይታ ሕዝብ በኢትዮጲያ ዉስጥ ከ1983 ዓ.ም ወዲህ የተጀመረዉ የይስሙላ ዴሞክራሲ ወደ እዉነተኛ መስመር ይመጣል በሚል ተስፋ ኢትዮጵያዊትን ለድርድር ሳያቀርብ እንደዎላይታ የሚያስፈልጉ ሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ በሁሉም ረገድ አስፈላግ የሆኑ ትግሎችን ሲያካህድ ቆይቷል፡፡

ይሁን እንጂ ሲደርስበት የነበረዉ ስዴትና መከራ እንዲሁም መገፋት ኢትዮጵያዊነትን እንዲንጠረጥር የሚያደረግ ከመሆኑም በላይ በዎላይታነትም እንዲናፍር ከመጋረጃ በስተጃርባ የሚቀመሩ ሴራዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ መለዮቻቸዉን እየቀያየሩ አንድነትን የኢትዮጵያዊነት ሴም እንዲሁም ወርቁን ሌላ አድርጎ ቀጥሏል፡፡

ከማሳያዎች አንዱ ሰሞኑ በፌዴሬሸን ም/ቤት የፀደቀዉ የምርጫና በስልጣን ላይ ያለዉን የብልጽግና ፓርቲ ዕድሜ ማራዘም አንዱ ነዉ፡፡ ይህ በዎሕዴግ ዕይታ ሕገ-መንግስታዊ መሰረት የሌለዉ የአምባገነናዊ መንግስት ዋነኛ መለዮ መሆኑን እንረዳለን፡፡
ሌላዉ የክልል ጉዳይ በተመለከተ ራስን በራስ ከማስተዳደር መብት ጋር ተያይዞ ዎላይታ ከዚህ ቀደም በሕገ-መንግስት አንቀጽ 47 መሰረት ታህሳስ 10፣2011 ዓ/ም ያቀረበዉ ጥያቄ አሁንም ሆነ ለወደፊት ብቻዉን ክልል ለመሆን የቀረበ ጥያቄ ነዉ እንጂ ከማንም ጋር ለመጣመር አልነበረም፤ ለወደፊትም አይሆንም፡፡

ዎላይታ ሕዝብ የኢትዮጵያዊነት ሴምም ሆነ ወርቁ አንድነት ነዉ ብሎ ኢትዮጵያዊነትን ለድርድር ሳያቀርብ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት እየተከራከረ ባለበት ወቅት ኢትዮጵያዊነትና እኛነት (ብሔረሰቦች) ተቀላቅሎበት አያወቅም ከሚሉት ወገን እና አይደለም ከዎላይታ ከመላዉ ኢትዮጵያ ብሔር-ብሔረሰቦች ጋር በአንድነት እንዘልቃለን ከሚል ጎረቤት/ቶች ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ጥያቄ ከማቅረብ ባለፈ ከዎላይታ ብሔር ጋር በሰማይም ሆነ በምድር አንገናኝም የሚያስብል ጥላቻ ንግግር ሤራዉ ለኢትዮጵያ አንድነት የማይበጅ ስለሆነ መታረም እንዳለበት ዎሕዴግ ያምናል፡፡ ይህ ጉዳይ በአደባባይ ጎልቶ የወጣዉ በማህበራዊ ሚዲያ ከዚህ ቀደም የብሔረሰቦችን ስም በመጠቀም ስሳደቡና ሲያንቋሽሹ ከነበሩበት ሞልቶ የተረፈ የያለማወቅ ዉጤት ነዉ ብለን ስለሚናምን አይደለም በድንበር በደም ከተሳስርን ማህበረሰብ ዉስጥ ያልነበረ ጥላቻ መዝራት አላስፈላጊ ስለሆነ እንዲታረሙ በድጋም በአጽኖት እናሳስባለን፡፡

አጎራባች ብሔረ-ብሔረሰቦች በተለይም ጋሞ፤ ጎፋና ዳዉሮ ከዎላይታ ጋር በብዙ ነገራችን እንመሳሰላለን፡፡ ይሁን እንጂ ከሚመሳሰሉት ብሔረሰቦች ጋር ሆነን አንድ አስተዳደር ክልል እንሁን ብሎ ዎላይታ እንዳልጠየቀ ዎሕዴግ ሕያዉ ምስክር ነዉ፡፡ ምናልባት የዴህዴን ካድሬዎቻችን ሴራ ልሆን ስለምችል ሕዝቦቻችን ማረጋጋት ይኖርብናል፡፡በዎጋጎዳ ጊዜም ሕዝብ ያልፈቀደዉን ሥራ ሰርቶ ሕዝቡን ለእልቂትና ንብረትን ለወድመት ያዳረጉ እነዚህ የዴሕዴን ካድሬዎች መሆናቸዉ ለአሁኑ ጥላቻም የካድሬዎች እጅ የለም ማለት አይቻልም፡፡ በሌላ አገላለጽ በትክክል በሕዝብ ዘንድ ያለዉ እዉነታ (የክልል እንሁን ጥያቄ) በ80ዎቹ ዉሳኔ ሃሳብ ዉስጥ ተካቷል ማለት አይቻልም፡፡ ስለዚህ አሸናፊዉ ማን ይሆናል ሕዝብ ወይስ ካድሬዎች?ታሪክ ራሱን ይደግማል እያለ ዎሕዴግ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሚከተለዉን አቋም መግለጫ አዉጥቷል፡፡

ከመስከረም 30 2012 ዓ.ም በኋላ ምርጫ እስኪደረግና ሕጋዊ ቅቡልነት ያለዉ መንግስት ስልጣን እስኪረከብ ድረስ ብልጽግና ፓርቲ ህጋዊ እዉቅና የሌለዉ ስለሆነ የህዝባችንና የአገራችን ፀጥታ ያሳስበናል፡፡ ስለሆነም ዎሕዴግ የህዝባችንና የአገራችን ፀጥታ በተመለከተ የስልጣን ባለቤት ለሆነዉ ሕዝብና ከሕዝቡ አብራክ ለወጣዉ የሀገር መከላከያና ፀጥታ ሃይሎች ከወትሮ በተለየ አቋም የዉስጥንና የዉጭ ፀጥታዉን እንዲትከታተሉ ዎሕዴግ ጥሪ ያቀርባል፡፡
የዎላይታ ሕዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር ህገ-መንግስታዊ መብት ጥያቄ ያለምንም ቅደመ-ሁኔታ ለብቻዉ ክልል እንዲፈቀድ እየጠየቅን ምንም ዓይነት ተለጣፊ የማያስፈልግ መሆኑን መንግስት እንድረዳ እናሳስባለን፡፡

በዎላይታ ክልል እንሁን ጥያቄ ዙሪያ ከዚህ በኋላ ምንም ዓይነት ሕዝባዊ ዉይይት ማድረግ ፋይዳ-ቢስ መሆኑን እያሳወቅን ሆኖም ከተገኘ ሕዝባችን ለእንዲዚህ ዓይነት ንቀት ተገቢዉን ምላሽ እንዲያገኙ እንዲታደርጉ እንጠይቃለን፡፡

ዎላይታ ሕዝብ አብረን ክልል እንሁን ብሎ ባልጠየቀበት የዎላይታ ህዝብ ክብር በሚነካ መልኩ ከዎላይታ ጋር አብራችሁ ሁኑ እያሉ የዎላይታን ሕዝብ የሚያሳድቡት ራሳቸዉ የብልጽግና ፓርቲ ፊት አመራሮች (ከፌዴራል እስከ ዞን) ያሉ መሆናቸዉን ስለደረስንበት ሕዝብን በአስቸኳይ ይቅርታ እንዲጠይቁ እንጠይቃለን፡፡

የዎላይታ ብልጽግና ፓርቲ ፊት አመራሮች አንተ ግፋ እኔ ልዉደቅልህ (በዎላይተኛ Neeni Suga-taani Kundana) የሚባለዉን ዜዴ በመጠቀም ያሴራችሁት ሴራ ያስመሰላችሁበት የአቋም መግለጫ እና በፈጸማችሁት ክህዴት በጣም ያዘንን መሆናችን እየገለጽን የዎላይታ ሕዝብ በእነሱ ላይ ያለዉን እምነት እንዲፈትሽና የራሱን ትግል ራሱ ሕዝብ እንዲከታተል እያሳሰብን ይህ ካልሆነ በስተቀር በብልጽግና ካድሬዎች የዎጋጎዳ ጊዜ ዓይነት ክህዴት ልፈጸም እንደምችል እንጠቁማለን፡፡

ብልጽግና ፓርቲ የደቡብ ህዝቦች ክልል እንሁን ጥያቄ በህገ-መንግስቱ መሰረት እንዲያስፈጽም አሁንም በድጋሚ እያሳሰብን ይህ ካልሆነ በስተቀርና በፖለቲካ ዉሳኔ መሰረት የሚፈጠሩ አዲሱ የክልል መዋቅሮች ዕድሜያቸዉ ከብልጽግና ፓርቲ የስልጣን ዘመን የማይዘል መሆኑን ከወዲሁ እናሳዉቃለን፡፡
የታሪክ አስተማሪና የታርክ ባለቤት የሆናችሁ ስልጡንና ታታሪ የዎላይታ ሕዝብ ሆይ ብልጽግና ፓርቲ ዳቦ ለጠየቀዉ ልጅ ድንጋይ እንደምትሰጥ ክፉ የእንጀራ እናት ሕገ-መንግስታዊ ጥያቄ ላቀረበዉ ታላቅ ለሆነዉ የዎላይታ ሕዝብ Covid-19 ምክንያት ዴሞክራሲያዊ መብቶችን መጠቀም በምከለክልበት ወቅት ዉስጥ የእልቂት ድግስ ደግሷል፡፡ ስለሆነም የሚያዋጣዉንና ትክክለኛ የሆነዉን የትግል ስለቶቹን ታወቁታላችሁና አስቡበት፡፡

በመጨረሻም የተከበራችሁ ዬላጋዎች፤ምሁራን፤የአገር ሽማግሌዎች፤የኅይማኖት አባቶች፤ ነጋዴዎች፤ አርሶ አደሮች፤ የመንግስት ሠራተኞች፤ እና የግል ባለሀብቶች ሕገ-መንግስታዊ የሆነዉ ጥያቅያችሁ በአትዮጵያ ዉስጥ ያለዉን ሕልዉናችሁን በሚፈታተን መልኩ አደጋ ላይ ወድቋል፡፡ ስለሆነም ከዎሕዴግ ጎን በመሆን ከመቼዉም ጊዜ በተጠናከረ አንድነትና ሕብረት መራራዉንና ፍሬ-ጣፋጩን ትግል እንዲትገፉ ዎሕዴግ ታሪካዊ ጥሪ ያቀርባል፡፡

ዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር

ሰኔ 05/ 2012 ዓ/ም

wolaitatoday
wolaitatoday
wolaitatoday
wolaitatoday
wolaitatoday
wolaitatoday