የመልካም ምኞት መግለጫ
የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ ዎብን ለኢትዮጵያዊያን በሙሉ እንኳን ለአዲስ ዓመት አደረሰን በማለት መልካም ምኞቱን ይገልፃል።
አዲሱ ዓመት ፍትሕ፣ ሠላምና ዕኩልነት የሚሰፍንበት፣ የሕዝቦች ሠላማዊና ሕገ-መንግሥታዊ ጥያቄዎች በሕገ መንግሥታዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ምላሽ የሚያገኙበት፣ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ተፋጥኖ ሀገራችን በእውነተኛ የለውጥ፣ የሠላም፣ የዕድገት ጎዳና ላይ የምትገኝበት ዘመን እንዲሆንልን በመሻት ድርጅታችንም የበኩሉን ኃላፊነት ለመወጣት በትጋት የሚሠራ መሆኑን ጭምር ለአባላቱና ለደጋፊዎች ያረጋግጣል።
ጳጉሜ 5 2012ዓ.ም