ያልተሳካዉ የዎላይታ መፈንቅለአስተዳደርና የብልጽግና ቅሌት
ነሐሴ 20 2012ዓ.ም
ነሐሴ 3 2012 በዎላይታ ሕዝብ ላይ የተደረገዉ መፈንቅለ አስተዳደር መስመር ሳይዝ 17 ቀን አስቆጥሯል።
ገዥዉ መንግስት ነሐሴ 3 በጉታራ የተገኙ ተሰብሳቢዎችን ዱካቸዉ ሳይታወቅ በማጥፋት በምትካቸዉ በተስፋዬ ይገዙ የሚመሩ የቱቦ አመራሮችን ምድብ በማስያዝ ሕዝባዊ ትግልን ለማኮላሸት ነበር ዕቅዳቸዉ። ይሁን እንጅ አመራሮች፣የላጋን የወከሉ፣የዎሕዴግና የዎብን ተወካዮች የሕግ ባለሙያዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ታግቶ በድብቅ ሲወሰዱ በዎላይታ ሕዝብ ልታዩ ችለዋሉ። ይህም ሕዝባዊ አመጽ እንድፋፋምና የታሰሩ የዎላይታ ታጋዮች በስድስተኛዉ ቀን ከእገታ በዋስ ተለቀዋሉ።
በሌላ በኩል አሮጌ ባለሥልጣናት በሕዝብ ደም የአዱኛ ኑሮ የለመዱና በአቢይ አገዛዝ ዉስጥ ዳር የተገፉ ቡድኖች የሥልጣን ተስፋ ተሰጧቸዉ የዎላይታ ሕዝብ የተመረጡና የተወደዱ አመራሮችን ለመገልበጥ ሤራቸዉን ቀያይረዉ እየሞከሩ ይገኛል። ከዞን እስከ ወረዳ ድረስ ያሉ አመራሮችን ከፋፍለዉ ቢያወያዩም በተቃዉሞ ያለዉጤት ቀጥሏል።
አሮጌ ጸረ-ዎላይታ ኃይሎች አሁን ብቸኛ አማራጭ ያደረጉት ከፍተኛ የጦር ሠራዊት በዎላይታ በማሠማራት የክልል መዋቅር ጥያቄ ማጠፍና Omotic ክልል በመመሥርተዉ መቀመጫዉን አርባምንጭ ላይ ተክሎ ምስለኔዎቻቸዉን ሰይመዉ መግዛት ነዉ የሚል ሆኗል። በያዝነዉ ሳምንት ጉንዳን ሠራዊት ዎላይታሶዶ፣ቦዲቲ፣ሁምቦ፣ጋሱባ፣አረካ፣በዴሳ፣ሻንቶ፣ቡጌ፣ጋቼኖ፣ጉኑኖ፣በቁሎሰኞ፣ሆብቻ፣አባላ፣አባያ፣ቦምቤ፣ዲዳዬ፣ባሌ፣ዋሙራ፣ቢጣና፣ዲምቱና ለሎች ሥፍራዎች ላይ በማስፈር ላይ ይገኛል። የሠፈረዉ የመከላከያ ኃይል የመከፋፈል tendency ፣ተስፋ በመቁረጥ ራሱን ማጥፋትና የመኮብለል አደጋ ለአቢይ አህመድ ተጨማሪ ፈተና ከመሆን ባለፈ ፈገግታ የሞላበት አማላይ ግንባሩን ኮሶ የቀመሰ አስመስሎታል፤ልቡም በዎላይታ ሕዝብ ላይ በቀልን እንዳረገዘ ቀጥሏል።በሰባቱም ዎላይታ መግቢያ በሮች ላይ ፍርሃት በወለደዉ ጭንቀት ፍተሻ እንደበረታ ነዉ የሚገኘዉ። ዎላይታ የካሽምር ግዛት መስላ ብትገኝም ሕዝቡ የተለመደዉን ሠላማዊ ትግል ሳያወላወል እንደቀጠለ የሚገኝ ከዉስጥ ባንዳዎች ጋር የሚደረገዉን ትግል በልዩ strategy በማስደገፍ የሚቀጥል ስለሆነ ሁሉም ሕዝብ ትግሉን በተጠናከረ ሁኔታ ይቀጥላል።