ነሐሴ 20 2012ዓ.ም
በህዝብ ላይ አልተኩስም ብሎ ራሱን የሰዋ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት አባል አስክሬን ዛሬ ወደ ትውልድ አከባቢው ተሸኝቷል
ሰሞኑን በወላይታ የፀጥታ ችግር አለ በሚል በውሸት ሪፖርት ለግዳጅ ወደ ወላይታ ከተላኩ መከላከያ ሠራዊት አባላቶች ውስጥ ግዳጁን ተቀብሎ የመጣውና በኦሮሚያ ክልል አምቦ ከተማ የተወለደው የሠራዊት አባል ግዳጄ የሀገርቷን ዳር ድምበር እንድሁም የሀገርቷን ደህንነት መጠበቅ እንጂ ንጹሀን ወላይታ ህዝብ ላይ መተኮስ አይደለም በማለት የራሱን ህይወት ለህዝብ መስዋዕት ማድረጉ ብዙሀንን ያሳዘነ ክስተት ቢሆንም ዛሬ አስክሬኑ ወደ ትውልድ አከባቢው የጀግና አሸኛኘት ተደርጓል፡፡
አንተ ጀግና የህዝብ ልጅ ለህዝብህ የከፈልከውን መስዋዕት መቼም የማይረሳ መሆኑን ሁሌም የወላይታ ህዝብ ይዘክራል፡፡
Rest in peace obbolessa!!!!