ነሐሴ 12 2012ዓ.ም
መንግስት እስከ 20/12/12 ዓ.ም ድረስ በወላይታ ንፁሐንን ያለአንዳች ሀዘነታ የገደሉ እና እንድገደሉ ትዕዛዝ በሰጡ አካላት ላይ እርምጃ ወስደው ህዝቡን በይፋ ይቅርታ የማይጠይቅ ከሆነ በወላይታ ውስጥ በሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የወላይታ አመራር ሙሉ በሙሉ ራሳቸውን ከብልፅግና ፓርቲ አባልነት እንደሚያገሉ አስታውቋል፡፡ በተጨማሪም መላው የወላይታ ህዝብ ከፓርቲው ጋር ላይታረቁ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንደሚጣሉም አሳስቧል፡፡
ድል ለወላይታ ህዝብ!