በአቢይ አህመድ የመከላከያ ሠራዊት የተገደለች ነፍሰጡር ወ/ሮ ብርቅነሽ አስክረን ሽኝት
ነሐሴ 10 2012ዓ.ም
በአቢይ አህመድ ቀጥታ ትዕዛዝ በወላይታ የተሰማራው የመከላከያ ሠራዊት ህፃናቶችን እንዲሁም ነፍሰጡር ሴቶችን በመግደል በወላይታ ታሪክ ፍጹም አረሜንያዊ ተግባር ፈጽሟል፡፡ በተላይም ወ/ሮ ብርቅነሽ ባሳ የሰባት ወር ነፍሰጡር ስትሆን ለልጆቿ አስቤዛ ለመግዛት በወጣችበት በመከላከያ ሠራዊት በቀጥታ በተተኮሰ ጥይት ህይወቷ ልያልፍ ችሏል፡፡ የወ/ሮ ብርቅነሽ ባሳ መገደል መንግስት ንፁሐን ወላይታ ላይ ያካሄደውን አስነዋሪና የዘር ማጥፋት ዘመቻና ፍጹም አረመኔያዊ ድርጊት ከመሆኑም ባሻገር ሀዘናችንም መሪሪ ያደርገዋል፡፡
ትናንትና ወ/ሮ ብርቅነሽ አስክረን ወዳጅ ዘመዶቿ እንድሁም የወላይታ የላጋዎችና የወላይታ ዞን ዋና አሰተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ በተገኙበት የቀብር ስነሥርዓት ተፈጽሟል፡፡ እኛም የወላይታ ህዝብ ንጹሐንን የገደሉና እንድገደሉ ትዕዛዝ የሰጡ አካላት ወደህግ ፊት ቀርቦ ፊትህ እስክገኝ ድረስ ትግላችንን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡
ፈጣሪ ነፍስሸን በገነት ያኑር!!