የህዝብ ሃይል – በዎላይታ

ነሐሴ 07 2012ዓ.ም (ማለዳ ሚዲያ)

 

ከሶስት ቀናት በፊት በመንግስት የፀጥታ ሃይል በስብሰባ ላይ ሳሉ ታፍነው ተወስደው የነበሩት የዎላይታ የፖለቲካ አመራሮች ፣ የሃይማኖት አባቶች እና የማህበረሰብ አንቂዎች ከእስር ተፈተዋል።

ከእስር የተፈቱት ህዝቡ በተከታታይ ሰላማዊ ተቃዉሞ በማድረግ መንግስት ላይ ጫና በመፍጠሩ ነው።

የዎላይታ ህዝብ ያሳየው ቁርጠኝነት እና ለአመራሮቹ ያሳየው ከፍተኛ አጋርነት ለሌሎች አከባቢ ትግሎች አርዕያ ከመሆኑም በላይ የህዝብን ሃይል ያረጋገጠ ነው። ህዝብ በቆራጥነት በአንድ ላይ ከቆመ መሳሪያ እንዳማያቆመው ሌላዉ ማሳያ ነው።

ይሁን እንጂ አሁን ካለው መንግስት ባህሪ አንፃር አረጋግቶና አዘናግቶ ሌላ ጥቃት ሊፈፅም ስለሚችል ለጠቅላላ ለውጥ የሚደረግን ትግል መቀጠል ተገቢ እንደሆነ የሚናገሩ በርካቶች ናቸው።

ቀድሞውንም መታሰር የሌለባቸውን ሰዎች በመፍታት የሚቀዛቀዝ ትግል ሊኖር አይገባም። የዎላይታ ህዝብ ህገ-መንግስታዊ ጥያቄ በህገ-መንግስቱ መሰረት ሊመለስ ይገባል። መሪዎቹም በዋስ ሳይሆን ሙሉ ለሙሉ ነፃ መባል አለባቸው። ነገሩም የፖለቲካ መፍትሄ ሊበጅለት ይገባል የሚሉ የፖለቲካ ተንታኞች ጥቂት አይደሉም።

ሰላማዊ ህዝብ ላይ ተኩሰው ህይወት ያጠፉና አካል ያጎደሉ (ያዘዙ) በህግ ሊጠየቁ ይገባል።

የፀጥታው ሃይል በወሰደው ያልተመጣጠነ እርምጃ ነፍሰ ጡር እናትን እና ህፃናትን ጨምሮ ከ ሃያ አንድ ሰዎች በላይ መገደላቸው ይታወሳል።

Wolaita Today
Wolaita Today
Wolaita Today