ወጣቱ ተጫዋች በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ አለፈ

ነሐሴ 04 2012ዓ.ም

በወላይታ የተፈጠረ ግርግርው የአረካ ከተማው አክሊሉ ዋናን ህይወት ቀጥፏል፡፡ በወላይታ ድቻ ከ17 ዓመት በታች ቡድን ለሁለት ተከታታይ ዓመታት ከተጫወተ በኋላ በ2011 ወደ አረካ ከተማ አምርቶ እየተጫወተ ይገኝ የነበረው የተከላካይ መስመር ተጫዋቹ በአንደኛ ሊጉ ጥሩ እንቅስቃሴ ሲያደርግ እንደነበር ሶከር ኢትዮጵያ ከክለቡ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል፡፡ ይሁንና በሀያዎቹ መግቢያ ዕድሜው እንደሆነ የሚነገርለት ወጣቱ ተጫዋች በትውልድ ከተማው ቦዲቲ በተነሳው ግርግር በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ ሊያልፍ መቻሉን ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡ ሶከር ኢትዮጵያ በዚህ ወጣት እና ተስፈኛ ተጫዋች ህይወት ማለፍ ምክንያት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቹ እና ለክለቡ አባላት መፅናናትን ይመኛል፡፡ (ሶከር ኢትዮጵያ)

 

Wolaita Today