ህዳር 14 2013ዓ.ም
በዛሬው ዕለት በቀድሞ በዎላይታ ዞን አመራሮችና ሌሎች ግለሰቦች እና በደቡብ ክልል ፓሊስ መካከል በተካሄደው ፍርድ ሂደት ቀጠሮ ክርክር አምስት ሰዎች ክሳቸው ተቋርጦ እንዲለቀቁ ተወስኗል።
የቀድሞ የዞኑ አስተባባሪ አመራሮች በፌደራል ተዘዋዋሪ ችሎት ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ለ20/03/13 ዓ ም ተጨማሪ ተለዋጭ ቀጠሮው እንደተሰጣቸው ከጠበቆቻቸው ለማወቅ ችለናል።
ዛሬ ክሳቸው ተቋርጦ እንዲወጡ የተደረጉ ጨምሮ ባለፈው በዋስትና የወጡትም የዋስትና ተያዥነት ተነስቶ በነፃ እንዲለቀቁም ተወስኗል።
ዛሬ በነፃ ክሳቸው ተቋርጦ እንዲወጣ ከተወሰነላቸው መካከል የቀድሞ የዎላይታ ዞኑ አቃቤ ህግ መምሪያ ኃላፊ አቶ ምህረቱ ኩኬ፣ የዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ የህግ ዲፓርተመንት ዲን አቶ ተከተል ላቤና፣ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ም/ል ፕረዚዳንት እና ሌሎች ይገኙበታል።