ከወላይታው አዲስ ዓመት ጊፋታ ጋር በተያያዘ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ያለ ሲሆን የተወሰኑትን እናጋራችሁ፡-
መስከረም 16 2013ዓ.ም
“ከጊፋታ ትሩፋቶች ዋናው በዓሉ ሲመጣ የሚደረገው ይቅር መባባል ነው::ግን አሁን ያለው ነባራዊ ሀቅ ቱባውን ባህል ትቶ በሴራ ፖለቲካ ብቻ መጠለፍ ሆነ::ወንድም በወንድሙ ላይ ጨክኖ፤የሕዝብ ጥያቄን በአግባቡ የጠየቀውን አስሮ በዓሉን በዘብጢያ እንዲያሳልፍ የሚያደርግ ክፉ ጊዜ ላይ ደርሰናል::” ጋዜጠኛ ተመስገን ወ/ፃዲቅ
“በዎላይታ ማንነቱ የሚደርስበትን ጭቆና የሚቃወም ትውልድ አካል በመሆኔ እኮራለሁ። እውነተኛ የላጋ ሰላማዊ ንቅናቄውና ህዝባዊ ወገንተኝነቱ ለጭቁን ሕዝቦች የቆመ ፀረ-ጭቆና ትግሎች ውስጥ ግንባር ቀደም የሚጠቀስ ነው። እውነተኛ የላጋ የእውነት የሕዝብ ልጆች ናቸው።” ዶ/ር ብስራት ኤልያስ
“በመንግስት የመከላከያ ኃይል ጭካኔ እያዘንንም የእጅ አንጓዎቻችንን እና መንፈሳችንን ከፍ ከፍ ከፍ እናደርጋለን!” አንዱአለም ታ. ቦልተና
“የወላይታ ዘመን መለወጫ ግፋታ በዓል ስናከብር በመንግስት ወታደሮች በግፍ የተገደሉ ወገኖቻችን በማሰብ ነው፤Shemppuwa Maaro!” ጎበዜ ጎአ ዳዱ
“የኢህአዴግና የወራሹ ብልጽግና አመራሮች ሥልጣናችሁ ዛፍ ላይ መንቀላፋት እንደሆነ በማስተዋል በሥልጣን ዘመናችሁ ሕዝብን ማዳመጥና ለሕዝብ መልካም ነገር መስራት እንዳለባችሁ ይሰማኛል፤ አስቡበት።” አወል አለማየሁ ዳና
“እውነተኛ የሕዝብ ልጆች ናቸውና ክብር ይገባችሗል። በመንግሥት ሽብር የተጎዱትን ንጹሓንን በማሰብ ግፋታን አክብረዋል፤ እናመሠግናለን፡፡” Temesgen KachoBassa (ተመስገን)
“የዎላይታ የላጋ ካዘኑትና ከተጎዱት ጋር በመሆን ላሳያችሁ ህዝባዊነት እናመሠግናለን፡፡ ዎላይታነት ይሄ ነው!!” ናሆም አይማሌ (Nahom Aymale)
“ንገሩት ለዚህ … TV ጊፋታና የመስቀል በዓል የተለያዩ መሆናቸውን!” Tedda W. Ethiopia
“እዛጋ ነው ልዩነቱ…ሰዎች በፀጥታ ኀይል ታጅቦ ጮማ ስጋ ለመቁረጥ በጉተራ አደራሽ ስጨፍሩ የወላይታ ዬላጋዎች ግን ባለፈው በግፍ በመንግሥት ታጣቂዎች ለተገደሉት ቤተሰብ ቤት በመሄድ ሀዘናቸውን ተካፍለዋል፤ወላይታ ዬላጋዎች ሁለም ጀግኖች ናችሁ። አዳርያ ሂ!!!” A. TIMES
“የወላይታ የዘመን መለወጫ ጊፋታ የወላይታ በህዝብ ዘንድ በድምቀት በአደባባይ ህፃንና አዋቂ ዮዮ ጊፋታ እያለ እየተደሰተ የሚያከብረው ትልቅ በዓል ቢሆንም ሆዳም ተላላኪ ባለስልጣናትና አመራሮች ለወላይታ ህዝብ ክብርና ታላቅነት በታገሉ ጀግኖች ልጆች ላይ እና የመብት ጥያቄ በጠየቀ ህዝብ ላይ የሰራችሁትን ሴራና ተንኮል ስለምታውቁ ሊወርድባቹ ያለውን እሳት ሰለምታውቁ ለብቻቹ ተደብቃችሁ በጠባብ አደራሽ በስምፖዚየም ብቻ ማክበራችሁ የወላይታን ህዝብ እሴት ባህል ታሪክ እያጠፋችሁ እንጂ ለትወልዱ ይህንን መልካም እሴት ማስተላለፍ ይሁን ማስቀጠል አትችሉም።” ካካ የተባለ አስተያየት ሰጪ
“እኔ በጆሮዬ እየሰማሁ “እሰከ ጊፍታ የወላይታ ክልል ጥያቄ ይመለሳል” ብሎ በሚዲያ ለሕዝብ ተናግሯል እና አሁን የትአለ ክልል? እውነት ለመናገር ይህ ሰው ሙሉ በሙሉ አልተመቸኝም!! ደግሞ በዚህ እድሜ ውሸት ለምን? አንድ ወይም ሁለት ሰው በውሽት ማሳመን ትችላልህ ነገር ግን አስራ አምሰት ሚለዮን ሕዝብ ማታለል አትችልም፤ የተናገርከው ንግግር በእጄ አለኝ ሬኮርድ አድርጌያለሁ::” ደስታ ተክሌ
“አፍንጫ ሲመታ አይን ያለቅሳል፤ በዎላይታ ክልል ምክንያት አንዱ ቤት ሀዘን በሀዘን ተዎራለች፤ አንዱ ጋ ደሞ የእስራት ስቃይ ያለወንጀላቸው ማረምያ ሆኖ የምሞቀውን ቤቱን ልጆቹን ትቶ ለቤቱ ተጨማሪ ጭንቅ::” …”በሌላኛው ሆድ አደር ቤት ዳንክራው ጦፍዋል፤ ለሱ ደሞ ጥቂት አጨብጫቢና ተላላኪ ይኖራል፤ ማዕረግ ለማስጨመር ብሎ ደፋ ቀና እርምጃ ውስዳለው አስራለው ዋ የዱላ መዓት፤ ብቻ ያስተዛዝባል፡፡ ያም ሆነ የዘንድሮ ጊፍታ በግፍ ለማክበር ህልናዬ አይፈቀድም፤ ምቾትም አይሰማም፤ ለምን ብባል አይኔ እያለቀሰ ነው፤ አፍንጫው ተመቶ (ሾሩዋው ኬህበና)። ይህ ክፉ 2012 ዓ.ም እንኳን ተሸኘ። የምመጣው ዓመት የዎላይታ ከፍታ የጥያቄው ምላሽ በሁሉም የተሳካ እንድሆን እመኛለሁ።” ሙሉቀን የጋ