ዬላጋዎች በመንግስት ወታደሮች በግፍ የሞቱ ሰማዕታት ቤተሰቦችን አፅናኑ
መስከረም 16 2013ዓ.ም
ዛሬ በወላይታ ሶዶ ከተማ የወላይታ ዬላጋዎች በመንግስት ወታደሮች በግፍ የሞቱ ሰማዕታት ቤተሰቦችን አፅናኑ
የወላይታ ህዝብ ህገመንግስታዊ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት በሰላማዊ መንገድ የጠየቁና ከፊት ሆኖ የመሩ አመራሮችና አክቲቪስቶች እንድሁም የሀገር ሽማግሌዎች ያለምንም ወንጀል በወታደር ታፍኖ በመወሰዳቸው በባዶ እጃቸው መሪዎቻችን ይፈቱ ብሎ አደባባይ በወጣው ህዝብ ላይ ቀጥታ በተተኮሰ ጥይት 36 ንጹሐን ወላይታዎች በመንግስት ታጣቂዎች ያለርህራሄ መገደላቸው የሚታወስ ሲሆን የወላይታ የላጋዎች የወላይታ ህዝብ የዘመን መለዎጫ ግፋታ በዓልን የሚናከብረው በግፍ የተገደሉ ወገኖቻችን በማሰብ ነው የሚል መርህ ይዞ ዛሬ በወላይታ ሶዶ ከተማ የሟች ቤተሰቦችን በማፅናናት ቀናቸውን ከነሱ ጋር አሳልፈዋል፡፡
“ጊፋታ ማናዉ ኑ ቆሬ ኤኖ ጌና!! ምንም ጭፈራ ፈንጠዚያ የለም! የዘንድሮ ጊፋታ በሀዘን ይታሰባል!!” የክንዶ ኮይሻ ዬለጋዎች
መስከረም 16 2013ዓ.ም
የወላይታ የዘመን መለወጫ የሆነው ጊፋታ በተለያዩ የወላይታ ከተሞች በብልፅግና አመራሮች ትዕዛዝ ህይወታቸው ያጡ 36 እና ከ 171 በላይ ንፁሀን ዜጎችን ታሳቢ በማድረግ የተለያዩ ክንውኖች እየተፈፀሙ እንደሆነ ዬለጋዎች አስታወቁ፤ በተቃራኒው በወላይታ የተወሰኑ የብልግፅና ፓርቲ አመራሮችና አባላት ከፈዴራል መንግስት ጋር ካላቸው የጥቅም ትስስር ግኑኝነት ስጋት የተነሳ ብልግፅና በሚቆጣጠራቸው የመንግስት ሚዲያዎች የተጋነኑ የጊፋታ በዓል መረጃዎችን እያሰራጩ እንደሚገኙ ተገለፀ፡፡
ከወላይታው አዲስ ዓመት ጊፋታ ጋር በተያያዘ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ያለ ሲሆን የክንዶ ኮይሻ ወረዳ ዬለጋዎች በተመሳሳይ ሁኔታ ያዘኑትንና የተጎዱትን በመጎብኘት አሳልፈዋል፡፡