GIFAATAA – የትውልድአደራ – ለቃቡራሳዊያንምክር!
ወዳጆች እንዴት ናችሁ? ጊፋታን እንዴት እያሳለፋችሁ ነው? የዘንድሮው አከባበር ጥቂት ግራ በተጋቡ እና የበታችነት ስሜት የተጠናወታቸው (የእግዜር ጠበቃ ነን ባዮች.. lol) ግለሰቦች (ቃቡራሶች) ከሚነዙት ቱልቱላ ካልሆነ በስተቀር ከየትኛውም ጊዜ በላይ በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ቀጥሏል። እነዚህ ግለሰቦች ራሳቸውን በመጥላት በሽታ (Self Hatred) ተጠቂ ስለሆኑ የእስራኤል አምላክ ፈውስ እንዲልክላቸው እንፀልይላችኋለን።
የወላይታ ሕዝብ ጊፋታን ሲያከብር ዘመን ሲቀየር ለመልካም ምኞት መግለጫው አደይ እና የሰላ አበባ ቀጥፎ YOO YOO GIFAATAA እያለ ዘመድ ወዳጁን የሚጠይቅበት እንጂ በሬ ቅቤ የሚቀባበት ወይም ግንድ የሚለቀልቅበት የጣዖት-ባዕድ አምልኮ አይደለም። ይህ ፈፅሞ በወላይታ የሌለ እና ያልነበረ እንዲሁም የማይኖር ነው። የሀይማኖት ተቋማት ለአማኒያን ምንም አይነት መልዕክት ቢያስተላልፉ እንደግለሰብ ተቃውሞ የለኝም። መልዕክቱን የመተግበር ያለመተግበርም ጉዳይም የሀይማኖቱ ተከታዮች ጉዳይ እንጂ የሌላ የማንም ሊሆን አይችልም። ስለዚህ በዚያ ላይ ብዙ አስተያየት የለኝም።
ባህል ደግሞ የሁሉም ስለሆነ እንደ ወላይታ ብሄር ተወላጅነቴ ስለዚሁ ለመፃፍ እገደዳለሁ። ይህንን ቱባ ባህልን ከባዕድ አምልኮ ጋር አያይዘው የሚፅፉ ሰዎች በግላቸው ምናልባትም ቤተሰቦቻቸው አያይዝው አክብረው ከሆነ እንጂ ሁሉን አካትቶ መተረኩ ተገቢ አይደለም። በወላይታ ወንጌል ከተሰበከ : ሕዝቡም ክርስቶስን ካወቀ አንድ ክፍለ ዘመን ተሻግሯል። ክርስቶስ ደግሞ የክርስትና መሰረት ነው። ክርስትና ደግሞ መነሻው ደግሞ እስራኤላውያን አይሁዳውያን ናቸው። መፅሐፍ ቅዱስ ለእስራኤል ህዝብ ብርሃንን ገልጦ የራሳቸውን ማንነት እና ባህላቸውን ጭምር እንዲጠብቁ የመንፍስ ጥንካሬ ሰጥቷቸል። ዛሬ በጉያችን እና ራስጌያችን ላይ ያለው ቅዱሱ መፅሐፍ የሰማይን ሚስጥር ብቻ ሳይሆን የምድሩን ሳይንስ የገለጠ መሆኑን መዘንጋት አያስፈልግም።
እንደ እስራኤል ሕዝብ በባርነት :በግዞት እና በስደት የተሰቃየ ሌላ ሕዝብ የለም። አነዚያን ሺህ አመታትን በስቃይ እና እንግልት ሲያሳልፉ የራሳቸውን ባህላዊ እሴቶች አልተውም። የራስ ቆብ ኪፓቸውን አልጣሉም ፤ ክታብ ቶራቸውን አልቀደዱም ፤ መቅደስ ሲናጎጋቸውን አላፈረሱም። ታድያ አሁን ላይ ጊፋታን የሚቃወሙ : መቶ አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ውዥንብር ውስጥ ሊገቡ እንዴት ቻሉ። የእስራኤል ሕዝብ ታሪኩን የሚያወሳበት የራሱ መንገድ ያለው ሕዝብ ነው። አይሁዳውያን ከወላይታ LEEKE -ሌኬ ጋር የሚመሳሰል እስካሁን የጥንታ አባቶቻቸው የሆነው ዣድ ታማኒ (Tza’ad Temani) እና ሁራህ (ሆራ) የተሰኘ ድንቅ መለያ አላቸው። ይህን የእስራኤልን ባህል አድንቀው ሲያበቁ የወላይታን ላለመቀበል የሚደረገው እንቅስቃሴ ራስን የመጥላት በሽታ ምልክት ነው። ይህ አካሄድ በወላይታ ምናልባትም ከፂዮናዊነት-Zionism ጋር የሚስተካከል አብዮትን ሊቀሰቅስ የሚችል ነው።
ጊፋታን እና መሰል የወላይታ ትውፊቶችን መጠበቅ ለትውልዱ አደራ የሚባል ነው። አለም ላይ ባህል የሌለው ሕዝብ የለም። ማንነት የሌለው ሕዝብ የለም። ስለዚህ የተለያዩ ምክንያቶችን አየጠቀሳችሁ ራስን የመጥላት በሽታችሁን ለማስታገስ ከምትሞክሩ ከቻላሁ ራሳችሁን ለመሆን ጣሩ ፤ ካልሆነም በመንፈስ እኛ እነሱ ነን የምትሏቸውን አይሁዶችን ተመልከቱ። ሕዝቡንን ለቀቅ አድርጉ።
የተከበሩ እና ለሕዝብ ብርሃንን ያስመለከቱ ባለውለታ ተቋማትን አታስነቅፉ : አትንቀፉ። ለራሱ ከቀዬው ድህነት ገፍቶት ወደ መሃል ሀገር እና ጠረፍ ላይ ሄዶ ከሰው በታች እንዲሆን የተደረገውን ሕዝብ ሌላ የማንነት ቀውስ ውስጥ አስገብታችሁ ስቃዩን አታብዙለት !
ጪሻ ማስቃይኖ
Yoo Yoo Gifaataa !
Holozy 1896 Chozeh HaMedinah