የሰብዓዊነት ጥግ የኢትዮጵያዊነት ከፍታ!!
በራፍኤል አዲሱ
ነሐሴ 19 2012ዓ.ም
የሀገር ዳር ድንበርና ሉዓላዊነትን እንዲያስከብር በህዝብ ሀላፊነት የተጣለበት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ወታደር የህዝብን መብት ማክበር ለማይፈልጉ ፖለቲከኞችና የፖለቲካ ቡድኖ ርካሽ አጀንዳ መጠቀሚያ ላለመሆን “ህገመንግስታዊ መብቱን በጠየቀ ሰላማዊ ህዝብ ላይ አልተኩስም” በማለት እንደዚህ ባስታጠቁት መሳሪያ ራሱን እያጠፉ ነው:: ክብር ለእውነትና ለህሊናቸው ለቆሙ እንደነዚህ አይነት እውነተኛ የህዝብ ልጆች!!
ከስር በፎቶ የሚታየው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የልዩ ኮማንዶ ሀይል አባል የሆነና በኦሮሚያ ክልል ወለጋ አካባቢ ተወላጅ እንደሆነ የሚነገርለት ወታደር በትናንትናው እለት ምሽት ላይ ከሰሞኑ በዎላይታ ዞን ለግዳጅ ኦፐሬሽን በተመደበበት በታጠቀው መሳሪያ ራሱን ማጥፋቱ ታውቋል:: ጓዱ ራሱን ማጥፋቱ ከገሱባ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልም ተረጋግጧል::
ከሰሞኑ በዎላይታና ኦሮሚያ አካባቢዎች በመከላከያ ልዩ ሀይል አባላት የግዳጅ ዘመቻዎች የሞቱ ንፁሀን ሰላማዊ ዜጎች አስከፊ ሁኔታ ካደረሰበት የአዕምሮ ጭንቀት የተነሳ ራሱን ለማጥፋት የተገደደው ይኸው የሀገር መከላከያ ሰራዊትአባል ጓድ ቀደም ባሉት ቀናት “የኛ ተልዕኮ የሀገርቷን ዳር ድንበር መጠበቅና ከወራሪ ኃይል መከላከል ነው እንጂ ንጹሀንን መግደል አይደለም: ባንገድል ይሻላል” እያለ በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በዎላይታ ዞንና ኦሮሚያ ክልል የሚደረጉ ግድያዎችን በፅኑ ሲቃወም መቆየቱን ለእሱ ቅርብ ከሆኑ የሰራዊቱ አባላት መረዳት ተችሏል:: ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከአራት ቀናት በፊት በዎላይታ ዞን ግዳጅ ላይ የነበሩ ስድስት የታጠቁ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ከነትጥቃቸው መጥፋታቸውን የቡድኑ አዛዥ መግለፃቸው ይታወሳል፡፡
ለዚህ ጀግና ኢትዮጵያዊ ቤተሰቦች መፅናናትን እየተመኘን ነፍስ ይማር ብለናል!