አሳፋሪና ክስተቱን የማይመጥን የቦዲቲ ከተማ አስተዳደር መግለጫ በሚመለከት
ጥቅምት 01 2013ዓ.ም
ከያምባርሻ የላጋ ለህዝብ የተላለፈ መልዕክት
እኛ የቦዲቲ ያምባርሻ የላጋ በዎላይቱማቴታ የማንደራደር ያገኘውን የትኛውንም ሥራ ሳናማርጥ የምንሠራና መማር ባለብን ጊዜ ተምረን ራሳችንን ለመለወጥ የምንጥር የዚህ ትውልድ አባል እንጂ የቦዲቲ ከተማ አስተዳደር በቀን 22/02/2013 ዓ.ም እንዳወጣው መግለጫ ጫፍ እስከ ጫፍ ከተማውን አልፎ የሚሄዱ ተሽከርካሪዎችን የሚንዘርፍ ዘራፊ አይደለንም።
ትላንት ከመካከላችን በፈደራል ፖሊስ በጥይት ተተኩሶ የተገደለው በተመስጋኝ ባህሪይ የሚታወቀው መርሀዊ መርዴክዎስ በ2010 ዓ.ም ከወሎ ዩኒቨርስቲ በህግ የመጀመሪያ ዲግሪ ከተመረቀ ጀምሮ ሥራ አጥና ምንም የገቢ ምንጭ የለሌው ቢሆንም መንግሥትን በትዕግሥት እየተጠባበቀ በሚኖርበት ማህበረሰብ ዘንድ እጅግ የሚወደድ ሠላማዊ ወጣት ነው።
የቦዲቲ ከተማ አስተዳደር ከተማ አስተዳደር በሰጠው መግለጫ 6:30 ላይ እነዚህ ወጣቶች እውነትም የሚዘርፉ ከሆነ፡-
- ከመቼው ነው የፖሊስ ምርመራ ዉጤት ተጠናቀቆ የቦዲቲ ከተማ አስተዳደር ለህዝባዊ መግለጫ የበቃው?
- አንዱን ወጣት በተለምዶ ከኖክ ማደያ አከባቢ ይዞ ቴክኒክና ሙያ አከባቢ ዝርፊያን ለመከላከል ሲሄዱ አንድኛው ወጣት (በረከት) በተገለበጠው ፓትሮል መኪና ላይ እንዴት ወጥቶ ነው የሞተው?
- ለመሆኑ መኪናው ስገለበጥ የሞተው ፌዴራል ፖሊስ ማን የሚባል ነው? አስከሬን አሸኛኘት እንዴት ነው የተደረገው!? ወዘተ…
እና የመሳሰሉ ነገሮች ገና ከብዙ ምርመራ በኃላ የሚመለሱ ቢሆንም የቦዲቲ ከተማ አስተዳደር የከተማው ወጣት ስም ለማጥፋት ብቻ የተቻኮለና ህዝብ ላይ ያላገጠ መግለጫ በማህበራዊ ሚዲያዎች ሆን ተብሎ እንዲሰራጭ መደረጉን ያምባርሻ የላጋ በፅኑ ያወግዛል።
ስለዚህ የያምባርሻ የላጋ ስም የሚያጎድፍ መግለጫ የሰጠው የቦዲቲ ከተማ አስተዳደር ይሁን የሚዲያ አካል በአስቸኳይ ማስተካከያ እንዲያደርግ በሰፊው የዎላይታ ህዝብ ስም እንጠይቃለን።
በዚህ አጋጣሚ በየላጋዎች ድንገተኛ ሞት ሀዘን የተሰማቸውን ቤተሰብ፣ ዘመድ፣ ወዳጅ፣ ያምባርሻ የላጋና መላው የቦዲቲ ህዝብን ፈጣሪ እንዲያፅናና፤ ነፍሳቸውን በአፀደ ገነት እንዲያኖራቸው መላው ያምባርሻ የላጋ ልባዊ ምኞቱን ይገልፃል።
ሕዝብ ያሸንፋል!!!
ወላይታ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት!!!
ያምባርሻ የላጋ
ጥቅምት 01 2013ዓ.ም