ህዝቤን ሰራዊት በመላክ አስገደልክ አካለ ጎዶሎ አስደረግህ!!!

wolaita today

ጥቅምት 10 2013ዓ.ም

 

ፓስተር በረከተአብ ኩማ

ይድረስ ለጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር አብይ አህመድ

በትክለኛ የፈስ ቡክ አካውንቴ ነው የምጽፍልህ። ላንተ ከሚፀልዩት ሰዎች አንዱ ነኝ። የወላይታ ልጅ የኢትዮጲያ ልጅ ነኝ። የወንጌል አገልጋይ ነኝ እውነቱን ነው የምነግርህ። የወላይታን ጉዳይ ለመፍታት እየወሰድክ ያለው እርምጃ በእግዚአብሔር ያስጠይቅሃል። ይህን የምልህ እግዚአብሔርን የምታመልክ ሰው ስለሆንክ ነው። የህዝብን ጥያቄ ያቀረቡትን መሪዎች በማሰር የተለያየ ክስ በማፈላለግና እግዚአብሔርን ታምኖ በኮሮና ወቅት እንኳን የጉባኤን አምልኮ ሳያቋርጥ ሰርቶ ለፍቶ የእለት ጉርሱን አፈላልጎ ጎርሶ የሚያድረውን ያልታጠቀውን ህዝቤን ሰራዊት በመላክ አስገደልክ አካለ ጎዶሎ አስደረክ። በዚህ ሁሉ ግን ለአንተ ከመፀለይ ውጭ ምንም አልፃፍኩኝም ነገር ግን ትላንት በፓርላማ ባደረከው ንግግርህ ወላይታን ከዳውሮ ጋር ለማጋጨት እና ህዝብን ለማስቆጣት መሞከርህ አሳዝኖኝ ይህችን ጽፈልኃለሁ። ኃይል የእግዚአብሔር ነው።

ጌታ ማስተዋልን ይስጥህ።

ምንጭ፡- Bereketeab Kuma