ወቅታዊ የዎላይታ ፖለቲካዊ ዳሰሳ እና የትግል ምክረ-ሀሳብ
መስከረም 15 2013ዓ.ም
የዎላይታ ሕዝብ ከመቶ አመታት ወዲህ ለየት ያሉ የጭቆና ቀንበር ሕዝባችን ላይ ስጫንብን ከቅድመ አባቶቻችን እስከ ዛሬ ዬላጋ ድረስ እየተፈራርቀ መጥቷል።በአጼው፤በወታደራዊ አገዛዝ እንዲሁም በኢሕአዴግና በብልጽግና የይስሙላ ዲሞክራሲያዊ አገዛዝ ዘመንም በአገሩ ባይተዋር ከመሆን በዘለለ ሰብአዊ መብት ተገፍፎ ነዳጅ ተጨምሮበት በኢሳት እስከመቃጠል ደርሶል፡፡ይባስ ብሎ ከ2010 ዓ ም ጀምሮ የመጣዉ አገዛዝ የምስራች ሳይሆን መርዶ፣ብርሃን ሳይሆን ጨለማ ፣አርነት ሳይሆን ባርነት ፣ነጻነት ሳይሆን እሥራት ይዞ የመጣ በመሆኑ ለራሱ በቀይ ምንጣፍ እየተረማመደ ዎላይታዊያንን በደም ምንጣፍ እንድረማመዱና በቀያቸዉም ሆነ በመላ ኢትዮጵያ የሚኖሩ እንድሸማቀቁ፤ በላባቸዉ ያፈሩት ሀብት እንድዘረፍና እንድቃጠል አድራጊና የኋላ ተዋናይ ሆኖ ተገኝቷል። ከብዙሃኑ በጥቅቱ ለማስታወስ ይረዳ ዘንድ የ”ለዉጥ መንግስት” ተብየዉ ሥልጣን ላይ ለመምጣት ሲያምጥ በትረ-ሥልጣን ከያዙ ክፍሎች ለማስጣል በሚደረገው ፍልሚያ ኦሮሚያና አከባቢዉ ላይ በሚኖሩ የዎላይታ ተወላጆች ላይ በተወሰደው ኢ-ሰብአዊ ድርጊት መሪዎች ማን እንደሆኑ ሕዝባችን ጠንቅቆ ይረዳል።በዚህ ብቻ አላበቃም በአዋሳና አከባቢዉም የተፈጸመዉ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ብያንስ ከለውጥ አመራር ነን ባዮች የተሰወረ አልነበረም። በዚህ ድርጊት የተሳተፉ አካላቶች ተገቢ ቅጣት ስለመቀጣታቸዉ የዎላይታ ሕዝብ የሚያወቀዉ አንዳች ነገር የለም።ይልቁንስ መስካሪዎች ላይ ጥቃት በማድረስ ፍርድ ቤት እንዳይቀርቡ የማድረግ ድርጊቶች ታይቷል። ተጠርጣሪ ወንጀለኞችም ሲሾሙና ሲሸለሙ አስተውለናችኋል። በሰው-ሀገር በሚኖሩ ዜጎች ላይ የሚደርሰው ዓይነት መገፋቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍ እያለ መጥቷል፡፡ ይህንን ሁሉ ጫና ተሸክመን የሞተዉን አስከረን ተረክበን አልቅሰን ቀብረናል፤ንብረቱን ያጡ ሁሉ ነፍሳቸዉን ማትረፍ እንደትልቅ ትርፍ ይዘዉ ከዜሮ እየቆጠሩ ይገኛሉ። የአራት ኪሎ ብልጽግና እንደሆነ በተ-መንግስቱንና የአሃዳዊ ፍላጎት ተሸካሚዎች ካልሆነ በስተቀር ለዎላይታዊያንና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የህልም እንጀራ ሆነዋል፡፡
በዎላይታ ለተፈጠረው ሁሉ ቀዉስ ትልቁ ምክንያት የሆነዉ የዎላይታ ሕዝብ የለጠፍ አስተዳደር ተቀብሎ በመኖሩ እንደሆነ ይታመናል። ዎላይታ እንደማንኛዉም ኢትዮጵያዊ ክልላዊ መስተዳድሮች በራሱ ክልል ለመተዳደር አንዳች ነገር አልጎደለዉም። ስለሆነም ሕገ-መንግስታዊ ጥያቄ ሥልጣን ላይ ላለዉ መንግስት አቅርቧል። በዞን ደረጃ የተቀመጡ የዎላይታ ዞን አስተዳደርም ሆነ በአስተዳደራዊ ሰንሰለት የተቀመጡ አካላቶች የሕዝብን ድምጽ በሠላማዊ መንገድ አስተጋብተዋሉ። ይህንን በመጠየቃቸዉ ነዉ እንግዲህ የዎላይታ ቀድሞ አመራሮች፣የላጋዎች፣የሀገር ሽማግለዎች፣የዎሕዴግ ፓርቲ ተወካይ፣ የዎብን ፓርቲ ተወካይ፣ የሕግ ባለሙያዎችና የነጋዴ ማህበረሰብ ተወካዮች ነሐሴ 3 /2012 ዓም በሠላማዊ መንገድ ከሚያደርጉት ስብሰባ Gutaraa ታግተዉ የታሰሩት ፤ በዋስትና ከተፈቱም በኃላ አሁንም በፍትህ እጦት እስካሁን የሚንከራተቱት። ገዥዉ መንግስት ከወታደራዊ ኃይል ባሻገር የብዙሃን መገናኛ በመጠቀም የሕዝብ ጀግና የሆኑ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የማይገባ ስም ሰጥተዉ ጥላሸት ብቀባም ሰፊዉ የዎላይታ ሕዝብ አደባባይ ወጥተዉ ከ36 የሚበልጡ የንጹሃንን ሕይወት ገብሮ ከእስር በዋስ እንድፈቱ አድርጓል። ይሁን እንጂ በቀን 12 /2013 ዓ/ም ሓዋሳ ከተማ በዋለዉ ችሎት የተገኙ የሕዝብ ተወካዮቻችን የዋስ መብት ባልተነሳበት ሁኔታ በፖለቲካዊ ጠልቃ ገብነት አንድ ቀን አሰረዉ ካሳደሩ በኋላ በቀን 13/2013 ዓ/ም ችሎት ላይ ተገኝተዉ ፍርደ ገምድል ዉሳኔ ተሰጥቷቸዉ የዋስትና መብት እንድነሳና እስከ 19/01/13 ዓ/ም ማረሚያ እንድወርዱ ተወስኗል።ይህ በጣም አሳዛኝ በዎላይታ አድስ ዓመት-ጊፉታ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ የብልጽግና አገዛዝ ትሩፋት ከመሆኑም ባሻገር የብልጽግና መዳረሻ ሳይሆን አይቀርም ተብሏል፡፡ይህም የተጣሉ በሚታረቁበት፤የተራራቁ በሚሰበሰቡበት፤የሰው ልጆች በሙሉ ከፍጡራን ጋር ሆነው ፈጣሪን በሚያመሰግኑበት የ2013 የጊፋታ/መስቀል በዓል የዎላይታ ሕዝብ ግማሹን በሞት አጥተው ፤ግማሹ በማረሚያ ቤት አድርገው፤ መላው ዎላይታም ጥቁር ለብሰው በጥልቅ ሀዘን እንዲያሳልፉ የተደረገ የብልጽግና ድራማ ሆነዋል፡፡
የተከበራችሁ የሕዝባችን ድምጽ የሆናችሁ ጀግና የነጻነት ታጋዮች፤ የዛሬ እስረኞች የነገ ማንዴላዎችና ኪንግ ማርቲን ሉተሮች የታሰራችሁት ብቻችሁን ሳይሆን መላ ከዎላይታ ሕዝብና ወዳጆች ጋር እንደሆናችሁ ልሰማችሁ ይገባል ። የተወደዳችሁ የዎላይታም ሕዝቦች ሆይ በብልጽግና የተጀመረዉ ዘመቻ ዎላይታን ባሪያ አድርጎ ለመግዛት አልያም ከምድር ገጽ ለማጥፋት የተወጠነ ዳግማዊ ነፍጠኛ ዘመቻ በመሆኑ ቆርጠን የማንታገልና የዳር ተመልካች ከሆንን ይህ እጣ በቀን ምድር የሚደርስና የደረሰ መሆኑን በመገንዘብ ጊዜ፣ሁኔታና ዉጤቱን ያገናዘበ የትግል ስልት በማስላት ከአገር ዉስጥ እስከ መላ አለም ድረስ እጅ-ለእጅ በመያያዝ በርትታችሁ በመታገል ከጎናችን ተሰልፋችሁ አቅምና ጉልበት እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናቀርባለን። የሠለጠኑ አለማት የሚያደርጉት ሠላማዊ ትግል በዎላይታ እየተገበረ ቢሆንም ዋጋ እያስከፈለን ይገኛል ምክንያቱም የብልጽግና አገዛዝ ደም የማፍሰስ አደጋና ግድያ እያበረታታ በመሆኑ ሕዝቡ ያልታጠቀ በመሆኑ ይህንን የሕዝባችን እልቅት ለመታደግ ስባል ወደ አለም አቀፍ ተቋማት ዘንድ በመቅረብ ውጭ አገር ያላችሁ ሰቆቃዉን የማጋለጥ ጥረታችሁ እጅግ በጣም የሚደነቅ ስለሆነ ዉለታችሁ መቼም ቢሆን በዎላይታ ዘንድ የማይረሳ ነውና ትግላችሁን ያለመታከት ወደፊት እንድትገፉ ምክረ-ሀሳባችን እናቀርባለን፡፡
ኢትዮጵያ ዉስጥ ሕግ አዉጪዉ፣ተርጓሚዉና አስፈጻሚዉም የብልጽግና መንግስት ስለሆነ ሕገ-መንግስቱም ሆነ ፍርድ/ፍትህ በብልጽግና ፊት አመራሮች በጎ-ፈቃድ መሆኑ ጉዳዩን አሳሳቢ ከማድረጉም ባለፈ ከትላንት የማይሻል እንዲሁም የባስ የሚመስል የዲሞክራሲ ምህዳር መሆኑን እያረጋገጠ መጥቷል። ከዚህ በኋላ ዎላይታን መምራት ያለባቸዉ የፍሬዉ አልታዬ ዓይነት ራዕይ ያላቸው፣ለሕዝብ መብት ነብስን ለመስጠት ወደኃላ የማይሉ፤የሕዝብን ጥያቄ በቀኝ እጅ አዳባባይ ላይ ይዞ የሚጋፈጡ፤ ከላይ የመጣውን ብቻ ወደ ሕዝብ የሚያወርዱ ሳይሆኑ የሕዝብንም ሀሳብ ላይኞች በግድ እንዲቀበሉ የሚያደርጉ በፓለቲካዊናሞራላዊ ብቃት የተካኑ ጎሳዊ የመሳሳብ ሰንሰለት የማይነካካቸው ልሆን እንደሚገባ አሁናዊ መላው የዎላይታ ሕዝብና ወዳጆችም አቋም እንደሆነ ዎሕዴግ ይገነዘባል፡፡ በመጨረሻም የዎላይታ ሕዝብ ጥያቄ ሳይመለስ ዛሬ ላይ ሥልጣን ይዞ መክረም የዛፍ ላይ እንቅልፍ ነው፡፡ ስለሆነም ገዥው መንግሰት የባከነ ሰዓትም ቢሆን ተጠቅሞ ዕድሉን ብጠቀም መልካም ነው እያልን ሕዝቡ ግን ከቶም ቢሆን የትግል ግለቱን ሳያቀዘቅዝ ማስቀጠል እንዳለበት ይመከራል፡፡የ2013 ዓ/ም ጊፋታን በተመለከተ መላው የዎላይታ ሕዝብ በሕዝብ ጥያቄ ምክንያት በብልጽግና መንግሰት ፀጥታ ኃይሎች በተወሰደው የሃይል እርምጃ በሞት የተለዩትንና በማረሚያ ሆነው የሚያሳለፉትን በማሰብ በተለያዩ የሀዘን ትዕይንቶች በማሳየት እንዲናከብር የመጨረሻ ምክረ-ሀሳባችን ነው፡፡
በሌላ ወቅታዊ ዳሳሳ እስኪንገናኝ መልካም ቆይታ
ዎላይታ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት!
ዎላይታ ያለምክንያት በመንግስት ላይ አይነሳም ከተነሳም ምላሽ ሳያገኝ አይመለስም!
መስከረም 15 /2012