ዎላይታ ህዝብ ላይ የተከፈተው የፌዴራል መንግስት ሽብር በአስቸኳይ ይቁም!!!
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከዎላይታ ተወላጆች ማህበር የተሰጠ አቋም መግለጫ
መስከረም 15 2013ዓ.ም
እኛ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዎላይታ ተወላጆች ማህበር የዎላይታ ህዝብ ሀገሪቷ ውስጥ እንደሚገኙ ሌሎች ብሔሮች እና ብሔረሰቦች ለሀገሪቷ ሉዓላዊነት ደሙን ያፈሰሰ፣ አጥንቱን የከሰከሰ፣ ህይወቱን የሰዋ፣ ሀብቱን እና ንብረቱን ያዋለ፣ የዛሬይቷ ኢትዮጵያ እውን እንዲትሆን ታሪክ የሚያወድሰውን ዋጋ የከፈለ ታላቅ ህዝብ መሆኑን ለዓለም ህዝብ በልበ መሉነት ሊናሳውቅለት እና ሊናውጅለት የሚገባ ታላቅ ባለታሪክ ህዝብ ነው።
ይህን ጀግና ህዝብ በኢኮኖሚ እና በፖለቲካ ሴራ በማዳከም፣ የህዝቡን ስነልቦና በመስበር፣ በፈጀ እና ባረጀ አስተዳደራዊ ጭቆና ውስጥ ለማስገባት የሚደረግ የማዕከላዊ እና የፌደራል መንግስት መርዛማ እና ረዢም እጅ ዛሬም በዚህ ጀግና ህዝብ ላይ እንደተዘረጋ ስንመለከት፣ እያቃጣ ያለውን ጦር ስናይ፣ በተግባር እየደረሰበት የሚገኘውን ግድያ፣ እስራት፣ ድብደባ፣ አፈና፣ ሰቆቃ፣ ስደት፣ ማሸማቀቅ እና ማንገላታት ስንመለከት እኛን መምህራንን በከፍተኛ ሀዘን ዘፍቆናል፣ አለ የሚባለው የሀገሪቷ መንግስት ላይ ሊኖር የሚችለው ተስፋ እንዲሟጠጥ አድርጎናል፣ ለህዝባችን አስፈላጊውን መስዋዕትነት ሁሉ ከፍለን ህዝባችንን ከዚህ ጭቆና ቀንበር ነፃ ለማውጣት ትጥቅ ትግል ውስጥ ሁሉ እንዲንገባ የሚያስገድደን እና የሚያንገበግበን እጅግ በጣም አስከፊ ወቅት ላይ መሆናችንን እኛ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዎላይታ ተወላጆች ማህበር እንገነዘባለን።
የፌደራል እና የክልል መንግስታት እንዲሁም እኔ አውቅልሃለሁ ባይ ዎላይታ ተወላጅ የፌዴራል እና የክልል ውስን ባለሥልጣናት ህዝባችን ላይ የከፈቱት ሽብር፣ የዘር ማጥፋት ዘመቻ፣ ጅምላ ጭፍጨፋ፣ ጅምላ እስራት፣ ጅምላ ድብደባ አስከአሁኗ ቅፅበት መቀጠሉን በአይን ስንመለከት ደግሞ የዜግነት ትርጉም ይጠፋንና በእርግጥ በዚህች ጨቋኝ ሀገር ዜጋ ሆነን ከሚንቀጥል እና ከሚንጨቆን፣ ህገመንግስታዊ የክልል ጥያቄያችንን ከፍ አድርገን አንቀፅ 39 ተጠቅመን ሀገር ወደ መሆን መሻገር እንዳለብን እኛ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዎላይታ ተወላጆች ይሰማናል።
እኛ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዎላይታ ተወላጆች ማህበር ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለመሆን እና ለመፍጠር ለተ ቀን ተግተን እየሰራን ባለንበት ወቅት እንደ እኛ እየተማሩ ያሉ ህፃናት እና ወጣቶችን መንግስት እሳት እና ብረት የለበሰ ወታደር አዞ ስያስገድል፣ ስያስጨፈጭፍ፣ ስያሳስር፣ ስያስደበደብ እና ስያሸማቅቅ ማየት ያመናል። በዚህም ህፃን እና ወጣት ተማሪዎቻችንን፣ ነፍሰ ጡር ሴቶችን ጨምሮ 38 ንፁሃን የዎላይታ ተወላጆች በመንግስት ታጣቂዎች በግፍ ተጨፍጭፈዋል። ደም አንበተን፣ አጥንተ ለቅመን ቀብረናቸዋል። ይህ ሳያንስ የህዝብ መሪዎችን፣ የሀገር ሽማግሌዎችን፣ የኃይማኖት አባቶችን፣ ምሁራንን፣ የህዝብ መብት ተሟጋቾችን እና ንፁሃንን የውሸት ክስ ከፍተውባቸው ዘብ ጥያ እንደወርዱ ተደርጓል። በዚህም የሀገራችን የፍትህ ሥርዓት ከስረ መሠረቱ የጠፋ መሆኑን ተረድተናል። በዚህም የመኖር ህሊውናችን አምባገነናዊ ሥርዓት አጣብቅኝ ውስጥ መግባቱን እኛ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዎላይታ ተወላጆች ማህበር በግልፅ ተረድተናል።
ይህ ሁሉ ጭቆና፣ ሀዘን፣ ሰቆቃ፣ እስራት፣ ድብደባ፣ ማሸማቀቅ እና ልብ ስብራት ውስጥ ባለንበት እጅግ በጣም አስቸጋሪ ወቅት ጠ/ሚ አብይ አህመድ እና ርስቱ ይርዳው የሾሟቸው የዎላይታ ብልፅግና ተልእኮ ፈጻሚ አምባገነን ካድሬዎች በአንድ ትንሽ አዳራሽ የጊፋታ በዓል ሊያከብሩ መዘጋታቸውን ስንሰማ እና ስናይ ሀዘናችን ጨምሯል፣ አፈናችን አይሏል፣ ሰቆቃችን እጥፍ ሆኗል።
ስለሆነም እኛ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዎላይታ ተወላጆች ማህበር ከዚህ በታች የሚገኙ የአቋም መግለጫዎችን አውጥተናል።
- አቶ ተስፋዬ ይገዙ እና ዶ/ር እንድሪያስ ጌታ “ከጊፋታ በዓል ቀድሞ የህዝቡ ህገመንግስታዊ የክልል አደረጃጀት ጥያቄ ምላሽ ያገኛል” ብለው ለህዝቡ ቃል በገቡት መሠረት ከጊፋታ እስድሞ እንዲሁም በጊፋታ እለትም ለህዝቡ ህገመንግስታዊ ጥያቄ ህገመንግስታዊ ምላሽ የሚሰጥበት አቅጣጫ ካላስቀመጡ እና ሚላሽ የሚሰጥ መሆኑን ሳያረጋግጡ ከአነሱ ጋር ተቀምጠን የሚናከብረው ምንም በዓል የለለ መሆኑን ለመላው ህዝባችን ሊንገልፅ እንወዳለን።
- በመንግሥት ወታደር በግፍ የተጨፈጨፉ 38 ንፁሃን ዎላይታ ተወላጆች ደም ሳይደርቅ እና ፍትህ ሳይሰጣቸው በትንሽ አዳራሽ ተሰብስበን የሚናከብረው ምንም አይነት የጊፋታ በዓል አለመኖሩን እና በልጆቻችን ደም ላይ ቆመን በዓል የማናከብር መሆኑን ለመላ መምህራን፣ ተማሪዎቻችን እና ቤተሰቦቻቸው እንገልፃለን።
- በውሸት የወሸት ክስ ተመስርቶባቸው የታሰሩ የህዝብ መሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ ምሁራን እና የመብት ተሟጋቾችን ጨምሮ ከ400 በላይ የዎላይታ ወላጆች ክሳቸው በአስቸኳይ ተቋርጦ ልጆቻቸውን፣ ቤተሰቦቻቸውን እና የሚወዷቸውን ማህበረሰብ ሳይቀላቀሉ እኛ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዎላይታ ተወላጆች ማህበር ምንም የአምባገነን ካድሬ በዓል የማናከብር መሆኑን እንገልፃለን።
- የፌደራል እና የክልል መንግስት የሾሟቸው የዎላይታ አምባገነን ካድሬዎች አሁንም ህዝባችን ላይ የዘረጉትን የበቀል እጅ ሳይሰበስቡ እና ወንድሞቻችን እና እህቾቻችን እንዲጨፈጨፉ የሀሰት መረጃ የሰጡ፣ ያስፈጨጨፉት እና የጨፈጨፉት ለህግ ሳይቀርቡ እና ለሟች ቤተሰቦች ፍትህ በአደባባይ ሳይሰጣቸው የሚናከብረው ምንም በዓል አለመኖሩን እኛ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዎላይታ ተወላጆች ማህበር ሊናረጋግጥላችሁ እንወዳለን።
- ለጎደለው አካል፣ ለወደመው ንብረት፣ ለጠፋው የሰው ህይወት እና ለደረሰው ስነልቦናዊ ጉዳት መንግስት ተጠያቂ መሆኑን ሳያምን እና ተገቢው ካሳ ሳይከፍል ትንሽ አዳራሽ ታጭቀን ምንም አይነት በዓል የማናከብር መሆኑን እኛ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዎላይታ ተወላጆች ማህበር ለመላ የወላይታ ህዝብ እና ለተማሪዎቻችን በታላቅ ሀዘን እና በልብ ስብራት ሊንገልፅላችሁ እንወዳለን።
ለመላው የዎላይታ ህዝብ
- ከዚህች ቅፅበት ጀምሮ ሁሉም በየአአባቢው ጥቁር የሀዘን ልብስ ለብሰው፣ ሻማ እና ጧፍ አብርተው በየመንገዱ ወጥተው ለሞቱት 38 ንፁሃን የተሰማንን ልብ የሰበረ ሀዘዘናችንን እንግለፅ።
- በጉታራ አዳራሽ ሊከበር የታቀደው የበዓል አከባበር ፍፁም የማይመጥን እና ካድሬዎች ለሳራቸው አበል ለማፃፍ፣ ጮማ ለመቁረጥ፣ ውስኪ ለመራጨት እና ሆዳቸውን ለመሙላት የተዘጋጀ ከመሆኑን በላይ በልጆቻችን ደም እና አጥንት ላይ የሚጨፈርበት በመሆኑ አንድም የዎላይታ ተወላጅ በዚህ ዝግጅት ላይ እንዳይገኝ ከወዲሁ እናሳስባለን።
- ሁሉም ዬላጋ ጥቁር ለብሰው ሻማና ጧፍ እያበሩ ሁሉም ሰማዕታት ቤት በመሄድ ከቤሰቦቻቸው ጋር እያዘንን የሚናሳልፍ ስለሆነ በየደረጀው የሚገኘው ዬላጋ ይህን አውቀው ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እንዲሰሩ እናሳስባለን።
ቀን 15/01/2013 ዓ.ም
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዎላይታ ወላጆች ማህበር