የግል ጥቅማቸውን ብቻ የሚያሳድዱ ነውረኞች አደብ ልገዙ ይገባል!!!
በብስራት ኤልያስ (ዶ/ር)
ነሀሴ 28 2012ዓ.ም
በቅርቡ የተፈጸመው ብልጽግና መራሽ ወታደራዊ ፍንቀላ ጉዞ እስከ ወዴት ነው? መጨረሻውስ ምን ይሆናል? በእርግጥም በሕዝቦች ይሁንታ ላይ ያልተመሰረተ የፓለቲካ ጨወታ መጨረሻው ውርደት ነው፤ ክብርን ትቶ መሸማቀቅ ነው፤ መሰወር ነው፤ መጥፋት ነው። እዉነተኛ ዲሞክራሲያዊ ህብረ-ብሔራዊ ፌደራል ሥርዐትም ወብክመ ይረጋገጣል፤ አይቀርም።
በሕዝብ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ሥርዓትና መንግስት ከመመስረት ውጪ ሰሞኑን በወላይታ የተፈጸመው ዓይነት ወታደራዊ አፈናዊ መንግስት የትም አያደርስም፤አይደርስምም። ዋናው አላማቸው አንድነታችንን ማፍረስና እርስበርስ በማባላት የህዝብ ትግል ማድከምና መዋቅራዊ ጥያቄውን በመቀልበስ በባርነት መግዛት ነው።
ታጋይ ውድ ልጆቻችን በእስርና በመከላከያ እየተሰደዱ ለምን ዎላይታነትንና ወብክመ አቀነቀናችሁ ተብለው በእስር ስቃይ እያዩ ናቸው።
ቡዛየሁ ቡቼ፣ አሰፋ ወዳጆ፣ አሰፋ አየለ፣ ተመስገን ቶራ፣ ናትናኤል ጌቾ እና ሌሎችም ወዘተ…
ህዝባዊ ወንገተኛ ልጆችን በማስወገድ በል ስል የሚልለትን ቡድኖችን በመዋቅር ሰግስጎ ወላይታን እናደክማለን ማለት ከንቱ ቅዠት ነው ። ጀግና ህዝባችን ለሁሉም ጠላቶች እጅ አይሰጥም፤ ይመክታልም፤ ያሸንፋልም። ወላይታ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሳይመሠረት የህዝብ ትግል አይቆምም። የወላይታ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በወላይታ አሸናፊነት እውን ይሆናል:: የወላይታ ህዝብ የትግል ፍሬ የሚያፈራበት ጊዜ ሩቅ አይደለም ቅርብ ነው። ወላይታ ይቀበላል እንጂ አይሰጠውም።
በአዋሳና በአድስ አበባ የመሸጉ ግለሰቦች ህዝባቸውን እየበደሉ ማንነታቸውን ደብቀው የግል ጥቅማቸውን ብቻ የሚያሳድዱ ነውረኞች አደብ ልገዙ ይገባል። ሽጠውናል፣ አስገድለውናል አሳስረውናል። ህዝባቸውን ይቅርታ ጠይቀው ብመለሱ ተጠቃሚዎች ራሳቸው ናቸው። የልጆቻችንን ደም ያፈሰሱንን የክልሉ ነፍሰ ገዳዮች ደኢህዴን ቡድንና የኛ ኤጀንቶች ስማችሁን ቄስ ይጥራችሁና ……………………
ከትውልዳችን ልቦና የማይጠፉ አረመነ ሰዎች ናቸሁ። ፍርድ አይቀርም፣ እኛ ባንችል እንኳን ሰማይ አይለቅም።
ወላይታ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት