ካሊሳና ካታይ ከሪያን ኤረተስ ግዮጋዳን – ህዝብን ማሻገር ይቅርና እናንተም…

በአሰፋ አየለ/ጠበቃ

ነሐሴ 29 2012ዓ.ም

የወላይታ ዞን ሰሞኑን በነበረው ውዥንብር መነሻ ወደ ወንበረ ስልጣን ማማ ላይ የመጡት አድሱ የደኢህደን ተጿሚ አስተዳደሪ የራሱን ካቢነ ዛሬ ሰብስቦ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ስለማድረጋቸው በማህበራዊ ሚድያ ስራገብ አይቼ የተሰማኝንና እነሱን የተቃወምነውም ይሁን ለወደፍቱም እየተቃወምናቸው መዝለቃችን አግባብ ስለመሆኑና ይህ በወላይታ የተጠየቀውን የክልል ጥያቄን የሚያመጣ ሳይሆን የእውነትም በጉልበት ያለ ህዝብ ቅቡልነት እንደመጣ ነገረ ሥራቸውም በሙሉ ከህዝብ ፍላጎት ውጪ ስለመሆኑ የተወሰኑ ነገሮችን ጠቆም ለማድረግ ወድጅያለሁ፡፡

በዞኑ መንግስት ኮምንከሽን ድህረ ገጽ በተለቀቀው መረጃ መሠረት ከሆነ ካድሬዎቹ ተሰብስበው የተወያዩት ነጥቦች 1ኛ/ ወቅታዊ የዞኑን ወቅታዊ ሁኔታ መገምገም 2ኛ/ ለድቻ ስፖርት ክለብ ደሞዝ ክፍያ ድጎማ በጀት 3ኛ/ ለ2013 ዓ/ም ለተቋማት የተደለደለ በጀት ረቂቅ ዕቅድ 4ኛ/ በቅርቡ በዞኑ በተፈጠረው የፀጥታ ሁኔታ ለተጎዱና ለሞቱ ወገኖች ድጋፍ ልደረግ ይገባል የሚሉ ጉዳዮች ስለመሆናቸው ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ የሆነ ሆኖ ግን እነሱ ተወያይተናል ካሏቸው አጀንዳዎች መካከል በ4ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሰችውን በተመለከተ ብቻ ትኩረት ለማድረግ ወድጅያለሁ፡፡

የወላይታ ህዝብ ራሱን በራሱ የማስተዳደር የዘመናት ጥያቄን ምላሽ ለማግኘት ፍጹም ሰላማዊና ደሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ጥያቄውን እያቀረበ በነበረበት ወቅት ጉልበትንና ስልጣንን ተጠቅማችሁ የንጹሐን ነፍስ እንዲጠፋና ብዙዎች አካል ጉዳት እንዲደርሳቸው እንዲሁም መሪዎቻችን አላግባብ እንድታሰሩ በማድረግ የተቆናጠጣችሁ ስልጣን መሆኑን መላው የወላይታ ህዝብ፣ የሰማዩ አምላክ እና ታሪክ የማይረሳው እውነታ መሆኑን እናንተም ታውቁታላችሁ፡፡ አሁን የእኔ ሀሳብ ያንን ለማውራትና እናንተን በዛው ለመውቀስ ባይሆንም አሁንም በተመኛችሁት ስልጣን ተቀምጣችሁም ይህንን የበደላችሁን ህዝብን ለማገልገልና ለመካስ ከማሰብ ይልቅ ዳግም ለመበደልና ጥያቀውንም ለማኮላሸት የሚትሄዱበትን መንገድ ስመለከት እጅጉን አሳዝኖኛል፡፡ ነፍስ ለጠፋባቸው ሰዎች ስንት ብር ካሳ ለመክፈል ነበር ያሰባችሁ? ለአንድ ሟች ነፊስ ስንት ሚሊዮን ብር ብትከፍሉለት ነው ልጁን ያጣውን ቤተሰብን፣ ወላጅ ያጡ ህጻናትን ፤ሚስቱን ወይም ባሏን ያጡ ባለትዳሮችን አዕምሮ ለመፈወስና ለመካስ ያሰባችሁት? አንድ ነፍስን በስንት ብር ሂሳብ ብትተምኑ ነው ካሳ ለመክፈል ብላችሁ ውይይት ስትቀመጡ ከሟቾቹ አንዱ የእናንተ ቤተሰብ ብሆን ኖሮ ሊሰማችሁ የነበረው ስሜትስ አስባችሁ ይሁን? ምላሹን ለእናንተው ሊተወው፡፡

ወደ ጉዳዩ ልመለስና እናንተ ለተጎዱቱ ካሳ ገንዘብ ለመክፈል ከመወያየታችሁ አስቀድሞ ማድረግ የነበረባችሁና የሟች እና ተጎጅ በተሰቦችን ልቦና ሊፈውስ የሚችል ነገር ነበረ፤ ግን አላያችሁም ወይም እያወቃችሁ ለማድረግ አልወደዳችሁም፤የትኛውንም ገንዘብ ጭነህ ወስደህ ብትከፍልለት መካስ የማትችለውን ቤተሰብ፣ የደማውን ውስጥ ቁስሉን ለመፈወስ ብታስቡ ኖሮ፡-

1ኛ/ ከሁሉም ውይይትና መድረክ አስቀድማችሁ በብሄሩ ባህል መሠረት ለቅሶ መድረስ ነበረባችሁ

2ኛ/ የሞቱትና የተጎዱትም ሊጎዱ የቻሉት እናንተን ወደ ስልጣን ለማምጣት ከመጠን በላይ በእናንተ ወታደር በተወሰደ አግባቢ ባልሆነ እርምጃ መሆኑ የንጹሐን ሞት ምክንያት የሆናችሁ እናንተና የእናንተ ድርጅት በመሆኑ የመሞታቸውን ሀላፊነት መቀበል ነበረባችሁ

3ኛ/ ሀላፊነት ከተቀበላችሁ በኋላ እናንተም ሆነ የእናንተ ላኪው ለሞቱትና አካላቸው የተጎዱና ያጡትን ቤተሰቦችን በሚድያ ቀርባችሁ ይቅርታ መጠየቅ ነበረባችሁ ግን አላደረጋችሁም፡፡

እናንተ እውነትም የተጎዳውን ቤተሰብንና መላውን የወላይታን ህዝብ ልቦና መፈወስ የሚትፈልጉ ሰዎች ብትሆኑ ገንዘብ ለመክፈል ከማውራታችሁ አስቀድማችሁ እነዚህን ማድረግ ሲገባችሁ ይህንን ሳታደርጉ ጭራሽ ነፍስ በገንዘብ ለመተመን አስባችሁ መወያየታችሁ “ ጎይሮርፔ ጎቾ ፓላ“ እንደምባለው ዓይንት ተረት ሆኗል፡፡

እንደ አጀንዳ ያልያዛችሁትና የህዝቡ የህሊውና ጉዳይ የሆኑ ነጥቦች፡-

ሀ/ ይህ ሁሉ ጣጣ የደረሰብን ዋነኛው ምክንያት የወላይታን የክልል ጥያቀን መንግስታችሁ ላለመመለስ በሚያደርገው ጥረት መሆኑን ከማናችንም በላይ ታውቁታላችሁ፡፡ የወላይታ ህዝብ ደግሞ በደም የሚገዛውን ራሱን ችሎ ለብቻውን በክልል የመደራጀት መዋቅር ጥያቄ በአሁን ወቅት ለህዝቡ ከየትኛውም አጀንዳ የበላይ መሆኑን ብታውቁም እናንተ የመጣችሁት የወላይታን ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትን ለማብሰር ሳይሆን ዳ-ኦሞትክን ለማምጣት በመሆኑ ይህንን ጥያቄ እንደ አጀንዳ ያለመያዛችሁ ትዝብት ውስጥ ይከታል፡፡

ለ/ እናንተ በወታደር ሀይል የያዛችሁት ሥልጣን በደም የተጨማለቀ መሆኑን ዘንግታችሁ ትናንትና ለህዝብ ራሳቸውን ሰውተው ለራሳቸው እንደ ሻማ እየቀለጡ ለወላይታ ህዝብ የክልል መብራትን ያበሩ አመራሮቻችን አላግባብ የተከሰሱበት ክስን በተመለከተ ከክልል ጋር በመነጋገር ክሱ የሚቋረጥበትን መንገድ እንደ አጀንዳ መያዝ ሲገባችሁ ያለመያዛችሁ አሁንም የእናንተን ወደፊት ከህዝቡ ጋር ተግባብታችሁ የመስራት እድላችሁን ጥያቄ ምልክት ውስጥ ያስገባችሁዋል፡፡

ሐ/ የወላይታ ህዝብ ምንም እንኳን እናንተ ወደ ስልጣን የመጣችሁበትን በደም የተጨማለቀውን መንገድና እናንተም የህዝብ መሪዎች ሳትሆኑ የደኢህደን መሆናችሁን ብናውቅም እኔን ጨምሮ ብዙዎቻችን እንያቸው ብንልም እናንተ ግን ፈጽሞ ለህዝብ ሳይሆን ከህዝብም ጋር ተባብራችሁ የመስራትና ጥያቄንም ምላሽ ለማስገኘት ፍላጎት ያለመኖራችሁን ሰሞኑን እያደረጋችሁ ባላችሁት ነገሮች ገምግመን በእናንተ የነበረንን ተስፋ ሙሉ በሙሉ ለመቁረጥ ተገደናል፡፡ አሁን ለእናንተ ከባዱና ዋና ሥራ መሆን የሚገባው አሁን እናንተን እየተቃወመ ያለውን ማህበረሰብን በጉልበት ሳይሆን በውይይት በማሳመን የያዛችሁትን ዓላማ ለህዝብ በማብራራት በዞኑ የታጣውን ሰላምና ፀጥታ ለማስፈን በመወያየት ፈንታ ይህንን እንደ አጀንዳ ያለመያዛችሁና እኛን ካልደገፍክ አሳስርሀለሁ አስገድልሀለሁ እያላችሁ አላስፈላጊ የላጋን እያሳደዳችሁ መገኘታችሁን ስመለከት ህዝብን ማሻገር ይቅርና ለእናንተም የማትሻገሩ መሪዎች መሆናችሁን ለመደምደም እየተገደድኩ እገኛለሁ፡፡

ብዙዎቻች እናንተን እየተቃወምን የምንገኘው በሀሳብ የበላይነት በአስተሳሰብ እንጂ በሰራዊትና በጦር ባልሆነበት እናንተ ከደርግ መንግስት የባሰ በወታደርና በጦር ሀይል ለመግዛት ስታስቡ የእውነት በዘመኑ ታሪክ በፍቅር እንጂ በጉልበት ለማንም ተንበርክኮ የማያውቀውን የወላይታን ህዝብ ይታዘዘናል ብላችሁ ካሰባችሁ እናንተም ካድሬ ሳትሆኑ ወንገልን ይዛችሁ ስበኩ፡፡

በአጠቃላይ ከተቀበላችሁኝ አንድ ወንድማዊ ምክር ብጤ ልምከራችሁ፡- የተወያያችሁበት ነጥቦች ህዝቡን ጥያቄ የሚመልሱና ህዝቡን የሚያረጋጉ ህዝቡም የሚፈልጋቸው ስላይደሉ አደራ መንግስት በዞናችን እየፈጠረ የሚገኘውን ሽብርተኝነትን በማቆም ህዝቡን በማወያየት የአገርና የሀይማኖት አባቶቻችን በማክበርና በመስማት ለእነሱም በመታዘዝ በአንድነት የመስራት ግደታችሁን እንድትወጡ እያልኩኝ ይህ ካይደለ ግን መጨረሻችሁን ፈጣሪ አያሳየኝ፡፡

ይህንን የህዝብ ጥያቄ የምታስመልሱና ሥራዎችን ሁሉ ከህዝቡ ጋር ተግባብታችሁ ከሰራችሁ ለዛው እንኳ የታደላችሁ አትመስሉኝም እንጂ እንደ ዳጋቶ የማትወደሱበት ምክንያት ለእኔ ስለማይታየኝ አስቡበት፡፡

ደግሞ ተቃወመኝ ብለህ ተንጫጫ ካልተለወጥክ መቃወም ብቻ ሳይሆን ለመታገልም ተዘጋጅችያለሁ፤ ከቻልክ ለመስተካከልና የህዝብን ጥያቄ አብረሄን ለመስራት ራስህንና ካብነህን አዘጋጅ፡፡

ከወላይታ ህዝብ አፈንግጠህ ወደየትም መሄጃ እንደለለህ እወቅ!!!