ዎላይታ የጠየቀውን ይወስዳል እንጂ የተሰጠውን አይቀበልም!!
በተመስገን ወ/ፃድቅ
ነሐሴ 28 2012ዓ.ም
ሰሞኑን ምንጭ ሳይጠቀስ አንድ አንድ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች አዲስ አወቃቀርን በተመለከተ የየራሳቸውን ስጋት ሲገልፁ ቆይተዋል::በርግጥ በግድ ይጫንብናል ተብሎ የሚገመተውን የአዲሱን መዋቅር ስም እንኳን መጥራት ያስጠላኛል::ምክንያቱም ይህ
ሕዝቡን መናቅና ማዋረድ መስሎ ስለሚታየኝ::
የኦሞ በሽታ በጭራሽ ተከትሎ እንዲመጣ አንፈቅድም:: ያኔ አባቶቻችን የደሙበት፣የቆሰሉበት ፣የሞቱበትና ትልቅ መስዋዕትነት የከፈሉበት መዋቅር በኡማ ተቀብሯል::
ይሄን ዳግም ለማምጣት አሽሞንሙኖ እየጠሩ መከጀል ድንቁርና ነው::የዎላይታ ሕዝብ ድሮ ሲነቃ የሞተው ይህ መዋቅር በግፍ የታፈኑ መሪዎች በሕዝብ ማዕበልሲፈቱ ተቀብሯል:: በርግጥ መሪዎችንና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን መንግስት ሲያፍን ዓላማው የሕዝቡን የዘመናት ጥያቄ ለመቀልበስ መሆኑ ግልፅ ነው::ግን የተኛው አንበሳ ሲነሳ በጥፍሬ ውስጥ ደብቁኝ አለ:: ሕዝብ አሸነፈ፣ግን ንፁሃንን አቁስሎ፣ገድሎ ዓይኑን በጨው አጥቦ ዳግም ተመልሶ መጣ::ይቅርታ የለ፣ካሳ የለ፣የንፁሃን ነፍስ ደመ-ከልብ ሆነ(ግን ሆኖ አይቀርም)::
አሁን የዎላይታ ሕዝብ ሁሉንም እያወቀ ፀጥ ብሏል::እውነታው የቱ ጋር እንዳለ ጠንቅቆ ያውቃል:: ቲያትሩ ተመልካች በሌለበት መድረክ ቀጥሏል:: የሁሉም መጨረሻ ቅርብ ጊዜ ይሆናል:: በአሸዋ የተሰራ ቤት::
ለማንኛውም የዳጋቶ ካብኔ ሕጋዊዩንም ሆነ ፖለቲካዊ መንገድ አሟጦ ጨርሶ የሄደው የክልልነት ጥያቄ በፌዴሬሽን ም/ቤት ትልቁ ጠርጴዛ ውስጥ ነው::ብዙዎች ቅዳሜ ዕለት የሚደረገው የምክር ቤቱ ስብሰባ ምናልባት እልባት ሊሰጥ ይችላል ብሎ መላ ምታቸውን ያስቀምጣሉ:: ከሆነ እሰዬው::ግን ይህ መንግስት ችግሮችን እየቀረፈ ሳይሆን እየጨመረ የሚሄድ ስለሆነ ትልቅ ውሳኔን ለመጠበቅ ያዳግታል:: ግን አንድ ነገር እሙን ነው::ከዚህ ስርዓት ይልቅ ሕዝቡ ጥያቄውን ያስመልሳል::
ሕዝብ ያሸንፋል!!
የዎላይታ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት!!