ህገመንግስቱን እየናዱ ህግ እናስከብራለን ማለት የክፍለ ዘመናችን ታላቁ ተቃርኖ…
ነሐሴ 20 2012ዓ.ም
የህዝብ ህገመንገስታዊ የመዋቅራዊ አደረጃጀት ጥያቄ በሀይል አፍኖ ይዞ የፊት አመራሮቹን “ገንዘብ ዘርፈዋል ከእከሌ ጋር አሲረዋል” እያሉ በሌላቸው ስልጣን የህዝቡን አመራሮች በወታደር ሀይል እያስፈራሩ ማሰርና ማንገላታት፣ ይባስ ሲልም ከስልጣን ጭምር ለማንሳት መሞከር ፋይዳ ቢስ የከሰረ ፖለቲካ አመራር ውጤት ነው:: ይህን ማድረግ ካለበትም ማድረግ የሚችለውና ህገመንግስታዊ ስልጣን ያለው ብቸኛው አካል የህዝቡ የራሱ ልዕላይ ምክር ቤት ነው::
በዚህ የሴራ ፖለቲካ ጨዋታ የበለጠ አሳፋሪ የሆነው ነገር ደግሞ የሀገርን ዳር ድንበርና ሉዓላዊነት እንዲጠብቅ በህዝቡ በራሱ ስልጣን የተሰጠውን የመከላከያ ሰራዊት ሀይል የፖለቲካ መጠቀሚያ እያደረጉ ሰላማዊውን ህዝብ ለማሸበሪያነት የመጠቀማቸው ቅሌት ነው::
- በመጀመሪያ ለህዝቡ ህገመንግስታዊ የመዋቅራዊ አደረጃጀት ጥያቄ በሀገሪቱ ህገመንግስታዊ አሰራር/አካሄድ መሰረት በሚመለከተው የብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በኩል ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ በማድረግ ፈጣን ምላሽ ስጡት::
- በሰላማዊ ህዝብ መሀል ወታደር አስገብታችሁ በግፍ ያስገደላችኋቸውን ንፁሀን ዜጎች በሚመለከት ተጠያቅነት ይረጋገጥ! ለኦፐሬሽኑ ማስፈፀሚያ የውሸት መረጃዎች ያቀነባበሩ: ትዕዛዝ የሰጡ: በሚዲያ ወጥተው የህዝብን ክብር ያጠለሹ በሙሉ ተይዘው ወደ ህግ ፊት ይቅረቡ::
3. ሌሎች የህግ ማስከበር ጉዳዮች ከዚያ በኋላ የሚመጡ ናቸው…የሀገሪቱ መልህቅና የህጎች ሁሉ የበላይ የሆነውን ህገመንግስቱን ራሳችሁ በሀይል እየናዳችሁ ህግ እናስከብራለን ማለት የክፍለ ዘመናችን ታላቁ ተቃርኖ ነው::
“ተላላኪ” አዲስ “ጉዳይ-አስፈፃሚ” ባለስልጣናትን ሹመት…
በራፍኤል አዲሱ
ነሐሴ 21 2012ዓ.ም
በፈራሹ የቀድሞው ደቡብ ክልል ህገወጥ ባለስልጣናት በዎላይታ ህዝብ ላይ የተደረገ የሰሞኑ ኢ-ህገመንግስታዊ መፈንቅለ-አስተዳደር ጋር ተያይዞ በህዝቡ ልዕላይ ምክር ቤት ያልተመረጡ በብልፅግና ፓርቲ የደቡብ ቅርንጫፍ የተመደቡ “ተላላኪ” አዲስ “ጉዳይ-አስፈፃሚ” ባለስልጣናትን ሹመት ህጋዊ ለማስመሰል ሲባል የህዝቡ ልዕላይ ምክር ቤት አባላት ነገ እንዲሰበሰቡ ጥሪ /”ትዕዛዝ” ደርሷቸዋል::
ይኸን ተከትሎ እነዚህኑ የምክር ቤቱን አባላት በወታደራዊ ሀይል አስገድዶ ህገወጥ ሹመቱን የማስፀደቅ መዋቅራዊ ሴራ እንዳይከሽፍ ለማድረግ ዛሬ ከቀኑ 10:00 ሰዓት ጀምሮ በአከባቢው ኢንተርኔት እንዲጠፋ ተደርጓል:: የህዝብን ህገመንግስታዊ መብትና ስልጣን በወታደር ሀይል መንጠቅም ሆነ ድምፁን ማፈን እንደማይቻል እንኳ በማያውቁ መሪዎች ሀገሪቱ እየተመራች መሆኑ ከክፍለ ዘመኑ አደገኛና አሳዛኝ ክስተቶች አንዱና ዋነኛው ነው::