ሞት ይብቃን.. ሰላም ለኢትዮጰያ!!

ነሐሴ 13 2012ዓ.ም

መንግስት የህግ የበላይነትን ማስጠበቅ ብቻ ሳይሆን ፣ የሰላማዊው ህዝብን ደህንነት ማስጠበቅም ተቀዳሚ ተግባሩ መሆኑን መዘንጋት የለበትም።

ኦሮሚያ አካባቢ የተፈጠረውን አለመረጋጋት ተከትሎ በመንግስት የፀጥታ አካላት እየተወሰደ ያለው ኢ— ሰብአዊ እርምጃ ልብን የሚያደማ ብቻ ሳይሆን ውድ ልጆቹን ገብሮ የስርአት ለውጥ በማምጥት ላይ ጉልህ ድርሻ ለነበረው የኦሮሞ ህዝብ አይመጥንም። የህዝብን ደም ያለ አግባብ ያፈሰሱ የመንግስት የፀጥታ አካላት ተጠያቂ ሆነው ማየት እንሻለን።

ግድያ ይቁም!! ክብር ለሰው ልጆች ነፍስ!!

” እነሆ እርሱ አንዲትን ነፍስ የገደለ የሰው ልጆቹን ሁሉ እንደገደለ ይቆጠራል …”ቁርአን

Ustaz Yassin Nuru / ياسين نورو

ገዳይ አስገዳይ ይፋ አንዲያደርግ!!!

Wolaita Today

በመብራቱ ደረሰ

ነሐሴ 13 2012ዓ.ም

ዎላይታ ላይ ከነሐሴ 03 – 05/2012 ዓ.ም በቁጥር 36 ሰዎች ለመሞታቸውና ከአንድ መቶ ሰላሳ አንድ (131) በላይ ህፃናት እስከ እናቶች ለመቁሰላቸው በሀገር መከላከያ ሠራዊት የተተኮሰ ጥይት ምክንያት መሆኑ ይታወሳል። ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ ከመንግሥት አካል በይፋ ኃላፊነት የወሰደ ወይንም ህዝብን ይቅርታ የጠየቀ መንግሥታዊ አካል የለም።

ይህም ሴረኞች ውሎ ሲያድሩ መዘው እንደሚሸርቡ ጥርጣሬ ገብቶናል። ገዳይና አስገዳይ አሁንም አሉ የሚሞተው የደሃው ልጅ ነው፤ ይህ ሊወገዝ ይገባል።

አሁንም ውሎ ሳያድር ገዳይ አስገዳይ ይፋ አንዲያደርግ አብክረን እንጠይቃለን።

ለመንግስታዊ ሥራ ጉዳይ ገንዘብ እንዳያንቀሳቅሱ መከልከላቸው ተገልፇል

ነሐሴ 13 2012ዓ.ም

በደቡብ ክልል ባለስልጣናት ትዕዛዝ በወላይታ ዞን የመንግስት ፋይናንስ ተቋማት ለመንግስታዊ ሥራ ጉዳይ ገንዘብ እንዳያንቀሳቅሱ መከልከላቸው ተገልፇል፡፡ አንድ የወላይታ ዞን ከፍተኛ ባለስልጣን እንደገለፀልን የወላይታ ህዝብ የጠየቀውን ህገመንግስታዊ በክልል የመደራጀት ጥያቄ አጠቃላይ የወላይታ አመራር ስለሚደግፍ ያንን ድጋፍ ለማስቆም የመንግስት ፋይናንስ ምንጭ ካገድን ሳይወዱ በግድ ይተዋሉ የሚል ደካማ አቋም የደቡብ ክልል ሹማምንት እንደያዙና በወላይታ ዞን የመንግስት ወጪዎች ከመንግስት ፋይናንስ ወጪ ሆኖ አገልግሎት እንዳይሰጥ መዋቅራዊ ጫና እያሳደሩ ይገኛሉ በማለት የህዝብ ጥያቄ በእንደዚህ ዓይነት ህገወጥ ተግባር ለመቀልበስ መሞከር በክልሉ ምን ዓይነት ህገወጥነት እንደተንሰራፋ ማሳያ ነውም ብለውናል፡፡ አያይዘውም ከእንደዚህ ዓይነት ህዝበ-ጠል ከሆኑ አስተሳሰቦች የደቡብ ክልል ባለስልጣናት እንድቆጠቡም አሳስቧል፡፡

☞ህገመንግስታዊ የህዝብ ጥያቄ በመዋቅራዊ ጫና አይቀለበስም፡፡