የወላይታ ህዝብ ላይ የዘር ጭፍጨፋ እንዲፈፅም ለአብይ አስተዳደር ህቡዕ ተልዕኮ የሰጠው ማነው?!
ነሐሴ 07 2012ዓ.ም
ወላይታዎች የዛሬ ሁለት አመት ሀዋሳ ላይ ‘ኢጄቶ’ ብሎ ራሱን በሚጠራው የሲዳማ የመንጋ ቡድን በግፍ ሲገደሉና ሲፈናቀሉ የፀጥታ ሀይሎች ምንም አይነት የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ የመከላከል እርምጃ እንዳይወስዱ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው የመከላከያና የክልሉ ልዩ ሀይል ከነሙሉ ትጥቁ የአገዳደሉን ሁኔታ እና ስልት ለመታዘብ እንደሄደ አካል ቆመው እያዩ ንፁሀን የወላይታ ልጆች ደም በመንጋ ቡድኖች በሀዋሳ ምድር እንደ ጎርፍ ፈሰሰ: ህፃናት በክብሪት ከነነፍሳቸው ተቃጠሉ: እንደ እባብ በአደባባይ በድንጋይ ተቀጥቅጠው ተገደሉ: በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ቤት ንብረታቸው ተዘርፎና ተቃጥሎ በክረምት ብርድና ዝናብ ከህፃናትና ነፍሰጡር እናቶች ጋር ሜዳ ላይ ተፈናቀሉ:: ጠ/ሚር አብይ አህመድ ግን ምንም እርምጃ አልወሰደም ነበር: ይባስ ብሎ የፀጥታ ሀይሎች እንኳ ህግ የማስከበርና ዜጎችን የመጠበቅ ሀላፊነታቸውን እንዳይወጡ በፀጥታ ሀይሎች ምንም እርምጃ እንዳይወሰድ ትዛዝ አስተላልፎ የብዙሀን ንፁህ ዜጎች ህይወት አስቀጠፈ::
አሁንም የዛሬ ሁለት አመት አካባቢ ደብረዘይት: ዝዋይ: ሻሸመኔ ላይ ንፁሀን የወላይታ ህፃናትና የነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑ ወጣቶች ሲገደሉ: ሲፈናቀሉ ለአመታት ጥረው ግረው ያፈሩት ቤት ንብረት በመንጋ ቡድኖች ሲቃጠልና ሲወድም አብይ ባላየ ባልሰማ ድምፁን አጥፍቶ የፀጥታ ሀይሎች እንኳ ህግ የማስከበርና ዜጎችን የመጠበቅ ሀላፊነታቸውን እንዳይወጡ በፀጥታ ሀይሎች ምንም እርምጃ እንዳይወሰድ ትዛዝ አስተላልፎ አስገደለ አፈናቀለ::
የዛሬ 5 ቀን (ሐምሌ 3, 2012) ሰላማዊው የወላይታ ህዝብ ምድር ላይ የፈረሰው የደቡብ ክልል ተላላኪ ሆድ-አደርና ህሊና ቢስ ባለስልጣናት ጋር አሲሮ የወላይታን የህዝብ እንደራሴዎች: የምክር ቤት አባላትና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የመብት ታጋዮች በወላይታ ሶዶ በህገወጥ መንገድ በፌዴራልና የመከላከያ ሀይሎች ከበባ አስደርጎ ወደ እስር ቤት በመውሰድ መላውን የወላይታ ህዝብ አስቆጣ:: በዚህ ህገወጥ ድርጊቱ የተቆጣው የወላይታ ወጣት ግልብጥ ብሎ አደባባይ ሲወጣ በዚህ ቀድሞ በወጠነው ሴራ በአከባቢው አዘጋጅቶ የነበረውን የመከላከያ ሰራዊት በደቂቃዎች ውስጥ አሰማርቶ ህፃናትን: ወጣቶችንና ነፍሰ ጡር እናቶችን ሳይቀር በጥይት አስገደለ ዛሬም እያስገደለ ነው!! እስከዛሬ ላለፉት አምስት ቀናት የቀጠለው የግድያና የወላይታን ምድር በደም ጎርፍ ለማጥለቅለቅ ያለመው ዘመቻው የህፃናትን ህይወት መቅጠፉን: ነፍሰጡር እናቶችን መግደሉን ቀጥሎበታል::
ልብ አድርጉ ወላይታዎች የዛሬ ሁለት አመትም ይሁን ከዚያ ወዲህ እንዲሁም ዛሬ ላይ ማንንም አልነኩም: አልገደሉም: የሌላውን ብሔር ተወላጅ አልነኩም: አላፈናቀሉም!! ያደረጉት ብቸኛ ወንጀል ቢኖር ሀገር ማልማት: የህይወትና የደም ዋጋ ከፍለው የሀገርን ደህንነትና ሉዓላዊነት ማስጠበቅ እንዲሁም ህገመንግስቱ በፈቀደላቸው መንገድ በክልል ተደራጅተው ራሳቸውን በራሳቸው ለማስተዳደርና: ያለ ሌላ አካል ይሁኝታ አከባቢያቸውን በራሳቸው የልማት ፕሮግራሞች ዕቅድ ለማልማት: እንደ ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ የራሳቸውን ቋንቋና ባህል ለማሳደግ የሚያስችላቸውን የክልል አደረጃጀት ጥያቄ ነው የጠየቁት:: ታዲያ የየትኛውን ቡድን ተልዕኮ ተቀብሎ ይሁን አብይ አህመድ ወላይታን በየሄደበት እየተከታተለና እያሳደደ የሚገድለው የሚያስገድለው?! ፈጣሪ በሰጠውና ጀግኖች አባቶቹ የደምና የህይወት ዋጋ ከፍለው የገዛ አጥንታቸውን ከስክሰው ባቆዩለት የገዛ ምድሩና ቤቱ ጭምር ሄዶ ወላይታን የሚገድለውስ የት ሄዶ እንዲኖር ነው?!
እስከዛሬም ይሁን ዛሬ ላይ የአብይ አህመድ አስተዳደር ሰላማዊውን የወላይታ ህዝብ የሀገር መከላከያ ጦር ልኮ የሚገድልበትና የሚያስገድልበት ተልዕኮ ምንም ይሁን ምን የወላይታ ህዝብ ከሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች ወንድሞቹ ጋር በፅናት አሸናፊ ሆኖ ይወጣል!! ታሪክና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ለዚህ አብይ አህመድ በወላይታ ላይ እያደረገ ላለው የዘር ጭፍጨፋ ዘለዓለማዊ ምስክር ይሆናሉ:: በታሪክም አብይ አህመድ ከሐምሌ 3, 2012 ጀምሮ ወደ ወላይታ ህዝብ ምድር የሀገር መከላከያ ሰራዊት ልኮ የወላይታ ህዝብ ላይ ያደረሰው የዘር ጭፍጨፋ በደም በተቀላቀሉ ደማቅ ቀለማት ተፅፎ በጥቁር የታሪክ አሻራነት ይመዘገባል::