አብረን ገዳይን ድል እናድርግ!!!
August 12, 2020
የወላይታ ህዝብ ሰቆቃ በቃላት ከምንገልጽበት እጅግ ልቋል። ገና ቃላት ስንደረድር እንባ ይቀድመናል ምክንያቱም ጨዋ የወላይታ ልጆች ደም በየሜዳው በአውሬው መንግስት አውሬ ወታደሮች እየፈሰሰ ይገኛል። ከዚህ በላይ ምን ህመም አለ???
‘Aydaamiyaa’ የሴቶች ንቅናቄ ነው። ሴት እናት ናት ልጇ በየሜዳው የወደቀባት፡ ሴት እህት ናት የወንድሟን አስከሬን ለመቅበር የተከለከለች፡ ሴት ሚስት ናት ባሏ እንደወጣ የቀረባት፡ ሴት ሴት ናት ከነእርግዝናዋ በጥይት እሩምታ በህጻን ልጇ ፊት ተደፍታ የቀረች፡
ታዲያ አሁንስ የወላይታ ሴቶች ሆይ ለወላይታ ልዕልና ለራሳችሁ ህልዉና አትታገሉምን??? ይሄ ከፖለቲካ ትግል በላይ ነው፡ ይሄ የሰብኣዊነት ትግል ነው።
አይመለከተኝም ብንል አይቀርልንም ምክንያቱም እየሞቱ ካሉ ሰዎች አብዛኛዎቹ (ህጻናትንና እርጉዝ እናትን ጭምሮ) የትግል ሜዳ ላይ ሳይሆን በገዛ ሀገራቸው የግል እንቅስቃሴ ላይ ሳሉ ወላይታ በመሆናቸው ብቻ ነው የተገደሉብን።
ስለዚህ በራችን ላይ ደርሷል የግድ ሳሎናችን እስኪገባ አንጠብቅ የጎረቤቶቻችንም ህመም ሊያመን ይገባል።
ከሀገር ውጪም ሆነ ሀገር ውስጥ ያላችሁ የወላይታ ተወላጆችና የወላይታ ህዝብን ትግል የምትደግፉ ማንኛውም አካላት “ኑ አብረን በአንድነት እንቁም” ገዳይን እናሸንፍ በማለት “Aydaamiyaa” የወላይታ ሴቶች ንቅናቄ ህዝባዊ ጥሪውን ያቀርባል።
Aydaamiyaa Maaccaa Asaa Qaattaa