ዉዥንብር ለመፈጠር የተከፈተውን የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ልብ እንዲሉት
በእንጉዷይ መስቀሌ
August 11, 2020
ይድረስ ለዉድ ጓደኞቼ
ይህንን ጽሁፍ እንድጽፍ ያስገደደኝ ዋነኛው ምክነያት የወቅቱ የወላይታ ሶዶና አከባቢዋ የነገሰውን ዉጥረት በሚመለከት በአንዳንድ ግለሰቦች እና የሚዲያ አካላት ለምሳሌ እንደ ESAT, Fana እና ሌሎች የመንግስት ሚድያዎች አማካኝነት እየተራገበ ያለዉን የተሳሳተ፣ መሬት ላይ ካለዉ እዉነታ የራቀ፣ በሌላ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ሆን ተብሎ ዉዥንብር ለመፈጠር የተከፈተውን የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ልብ እንዲሉት። በተለይም ደሞ ቀጥታ ተገጂ (direct victim) ስትሆን እንደ ደቡብ Tv ባሉት የሚናፈሰው ፕሮፓጋንዳን መስማት ያማል። ይህንን ውዥንብር ያጠራ ዘንድ ይህችን ማለት ወደድሁ
- የማን ጥያቄ (ፍላጎት) ነዉ?
በወላይታ በክልል ልደራጅ ጥያቄ የህዝቡ ሳይሆን የግለሰቦችና የሌላ ሀይል ነዉ says ESAT and co። ትልቅ ውሸት! ይህ ጥያቄ መቼና እንዴት ተጀመረ ወደሚለው ክርክር ማንሳት ሳያስፈልግ፣ ቆይ ለመሆኑ በክልል ልደራጅ ጥያቄ ህግ-መንግታዊ መሠረት ያለዉ ጥያቄ አይደልም ወይ? ጠያቂው አካል በእራሱ ወይስ በሌላ ተገፉፍቶ ጠየቀ የሚለዉ መከራከርያ ይሆናል ወይ? ስራ ላይ ያለዉ ህግ-መንግስት እስካልተሻሻለ ለሁሉም በተመሳሳይ ተግባራዊ መሆን የለበትም ወይ? ጥያቄው የሚሻዉ የችሮታ ምላሽ ሳይሆን የህግ አይደለም ወይ? (Remember: the Pandora box is opened the day you give it to one)
- የፍላጎቱ ነገር ከተነሳ አይቀር
የቀድሞቹን ትተን የቅርቡን ብናስታውስ እንኳ የወላይታ ተወላጅ በማንነቱ በ2008 ዓ.ም- 2009ዓ.ም በዝዋይ፣ በሻሸመኔና ሌሎች ኦሮሚያ ከተሞች ለዘመናት ከኖረበት ቀዬው አልተፈናቀለም፣ ሀብት ጥሪቱን አላጣም፣ አልተገፋም? በ2010 ዓ.ም ካለማትና ለዘመናት ከኖረባት ሀዋሳ በግፍ ተገሎ፣ ሀብት ንብረቱን አጥቶ፣ ፍትህ ተነፍጎ አልተሰደደም? ታደያ ይህ የተገፋ ህዝብ በደሉ ያበቃለት ዘንድ፣ ለደህንነቱ ዋስትና እንዲሆለት በመፈለግ ሌላ አማራጭ መዋቅር (በክልል ልደራጅን) ቢፈልግ ምኑጋ ነዉ ስህተቱ?
- በዕለተ እሁድ በደቡብ ፖሊስ የተያዙ 26 ሰዎች ሁከት ፈጣሪ፣ ከሌላ ቡድን ጋር (ማለትም ህወሓትና ኦነግ ሸኔ ጋር በማበር) በአከባቢው ጸብ ለመጫር ሲዘጋጁ የተያዙ የጥፋት ሀይል ናቸዉ claims some። እዉነታዉ፡ እኝህ ሰዎች በህጋዊና በሰላማዊ መልኩ ሲያካሂዱ ከነበረበት ስብሰባ ድንገት ተፋነዉ የተወሰዱ፣ ለየቤተሰቦቻቸዉ የት ይሆኑ?ምን ደርሶባቸው ይሆን የሚል የስጋትና ጭንቀት ሌትና ቀን ያተረፈ ክስተት ሰለባ ናቸዉ። በነገራችን ላይ ከህወሓትም ሆነ ኦነግ ሸኔ ጋር የሚሰሩ ግለሰቦች አሉ ቢባል እንኳን ድርጊቱ እንዴትና ለምን ወንጀል ሆነ? አብሮ መታየታቸው ብቻዉን ወንጀል ያረገዋል ወይ? (at least as far as my knowledge concerned those entities are not listed terrorist? so how is it crime per se? አይ ከእነዚህ አካላት ጋር ማበር ለዉጡን እንዳለመደገፍ ይቆጠራል ከተባለስ ለዉጡን አለመደገፍ ወንጀል ነዉ ወይ? በእርግጥ ብልጽግና በእራሷ አመራሮች ላይ ግምገማ አካሂዳ እርምጃ መዉሰድ ትችል ይሆናል ግን ደሞ የፖለቲካን ዉሳኔ ከህግ አቋም ጋር እያምታቱ የሀሰት ወሬ ማሰራጨቱ ምን ፋይዳ አለው? (ልብ ይበሉ፡ ከታሰሩት 26 ሰዎች ዉስጥ አብዛኞቹ ከብልጽግና ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌላቸው ለምሳሌ አክቲቪስት፣ ምሁራን፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የሌላ ሲቭል ማህበራት አባል ናቸዉ)
- ግለሰብ ከህዝብ እንለይ
አደረጉት ተብሎ የታሰበው ድርጊት ተቀባይነት የለዉም ብሎ ቢታመን እንኳን ፣ የግለሰብን ድርጊት የወላይታ ህዝብ በሙሉ እንዳደረገው በመሳል በአንዳንድ ግለሰቦች ለምሳሌ ስዩም ተሾመ እንዲሁም ሚዲያዎች ለምሳሌ እንደ ESAT ባሉ የሚናፈሰው የሀሰት ዘጋቦችም ሆነ የመንግስት መከላከያ ሰራዊትና የክልሉን ልዩ ሃይል በማዝመት እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች ለምሳሌ፦ መግደል፣ ያልተመጣጠነ ኃይል መጠቀም፣ ማሰርና ማፈን ወዘተ የቀጠናውን ሰላም ቢያደፈርስነና ነገሮችን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ቢመራ እንጅ ለህጋዊ ጥያቄ ምላሽ ይሆናል ወይ?
በአጭሩ አንፃራዊ ሰላም በሰፈነበት አከባቢ፣ ቁጥሩ በርከት ያለ የመከላከያ ሠራዊትና ልዩ ሃይል አዝምቶ ህዝቡን ማሸበር ዘላቂ መፍትሔ አያመጣም ። ሳይረፍድ መንግስት ለህጋዊ ጥያቄ ህጋዊ ምላሽ ይሰጥ ዘንድ እንጎትጉት።
እባካችሁ በክልል ጥያቄ ጉዳይ የሚገበረዉ የንጹሃን ዜጎቻችን ደም ይብቃ።